Page 1 of 1

ለናሙና ያህለ፥ ባለፉት መቶ ዐመታት አባ ገዳዎች ብያንስ አስሬ ኣልተሰባሰቡም?

Posted: 07 Jun 2025, 01:29
by Naga Tuma
ካልተሳሳትኩኝ በገዳ ስርዓት አባ ገዳዎች በስምንት ዐመታት ኣንድ ግዜ ይሰበሰባሉ።

እንደ ገባኝ ከሆነ የመሰብሰባቸዉ ዋና አላማ የነበረን መተዳደርያ ሕግ ወይ ለማሻሻል፣ ወይ ኣያስፈልግም ብሎ ለመጣል፣ እና ኣዲስ ሕግ ካስፈለገ ገምግሞ ለማጽደቅ ነዉ።

ይህ ስህተት ነዉ?

ስህተት ካልሆነ የቦረና ምሁራን ነን የሚሉት ብያንስ ባለፉት መቶ ዐመታት ዉስጥ የተጣሉትን፣ የተሻሻሉትን፣ እና አዲስ የወጡትን ሕግጋት ማጥናት ኣይችሉም?

ሕግጋቱ በጽሑፍ ያልተቀመጡ ከሆነ እንደ አፈ ታሪክ የሚታወቁ ኣይዴለም?

ይህን የምያስጠይቀኝ በየግዜዉ የምሰማዉ ትልቅ ወቀሳ ነዉ። ወቀሳዉ አባ ገዳ ብልት ቆራጭ ነዉ ይላል።

ይህ ትልቅ ወቀሳ ለናሙና ያህል በአፈ ታሪክም ይሁን ባለፉት መቶ ዐመታት ዉስጥ የሚታወቁ የገዳ ሕግጋት ዉስጥ መሠረት እንደሌለዉ ማስገንዘብ ኣይቻልም?

ይህን ማስገንዘብ የሚችሉ የቦረና ምሁራን ዬሉም? የቦረና ዩኒቨርዚቲ ይህን ኣጥንቶ ማስገንዘብ ኣይችልም?

እኔ የኢትዮጵያ እዴሰ ወይም ህዳሴ የምለዉ ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶች ሁሉ ጥናት ነዉ። ስለ አክሱም ብቻ ኣይዴለም።

Re: ለናሙና ያህለ፥ ባለፉት መቶ ዐመታት አባ ገዳዎች ብያንስ አስሬ ኣልተሰባሰቡም?

Posted: 10 Jun 2025, 17:18
by Naga Tuma
የገዳ ስርዓትን በኣንድ ተግባሩ ብቻ መመዘን ይቻላል።

በየ ስምንት ዓመታት የነበረ ሕግን የሚሽር ወይም የምያሻሽል እና አዲስ ሕግን የምያጸድቅ ነዉ።

ይህ ብቻ ስልጣኔን የምያንጸባርቅ ኣይዴለም?

በእጅ ላይ ያለ ወርቅ ነሃስ ነዉ ኣሉ?

ስርዓቱን ያደነቁትን ሁለት ምሁራንን መጥቀስ በቂ ነዉ።

ኣንዱ ዶክተር ጌታቸዉ ዴሌቦ ነዉ።

ኣንድ ግዜ በአጋጣሚ ያነበብኩኝ የገዳ ስርዓት ስልጣኔ ከአክሱም ስልጣኔ በላይ ነዉ ብሎ ነበር ኣሉ። ያለዉን ቃል በቃል ባላስታዉስም አስተያየቱን ኣስታዉሳለሁ።

ሁለተኛዉ ፕሮፌሰር ዶናልድ ኤን ለቪን ነበር። እሱም የሚከተለዉን ዐይነት አስተሳሰብ ጽፏል።

The Gada system represents the most complex social organization ever devised by the human imagination (paraphrased.)

እነዚህ አስተያየቶች ብቻ ይህ የኢትዮጵያ የሆነ ታሪካዊ ቅርስ በጥልቁ ተጠንቶ ኣስፈላጊ ማሻሻያዎችን እያወጣ፣ የሃገር ሕግን ሳይጻጸር፣ ለፈለገዉ ማህበረሰብ ስራ ላይ ይዋል ማለት ከባድ ነዉ?

Re: ለናሙና ያህለ፥ ባለፉት መቶ ዐመታት አባ ገዳዎች ብያንስ አስሬ ኣልተሰባሰቡም?

Posted: 10 Jun 2025, 17:56
by Misraq
Naga Tuna 🐟

ገዳ ሰው የሚታረድበት ቁላ የሚቆረጥበት ባዕድና ጣኦት አምልኮ ዛፍ በቂቤ ተቅምብቶ ደም ተረጭቶ ሰይጣን የሚጠራበት የክፉ መንፈስ ባህል ነው። ቀባብታችሁ ዲሞክራሲ ነው ብላችሁ ልትሸጡት ብትሞክሩም በገዳ ስርዓት የተፈጠረውን ወንጀል ምድሪቱ ራስዋ መስክራለች ትመሰክራለችም።