Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4380
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

BBC:-ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የምትገኘው አሊ ዶሮ እና አካባቢዋ የእገታ ማዕከል !በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የሚፈፀም እገታ!

Post by Za-Ilmaknun » 04 Jun 2025, 12:30

https://www.bbc.com/amharic/articles/cqj784jzkq8o

አሊ ዶሮ ከአዲስ አበባ በስተ ሰሜን 142 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ትንሽ ቀበሌ ስትሆን፣ የምትገኘው መዲናዋን ከአማራ ክልል ጋር ከሚያገናኙ ዋና ጎዳናዎች አንዱን ተከትሎ ነው።

በአካባቢው የፌደራል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እና የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ቢኖሩም ብዙውን ጊዜ የሚደርሱት እገታ ከተፈፀመ በኋላ መሆኑ ጥያቄ እንደሚፈጥርበትም መረጃው ይጠቅሳል።

"ኢስት ሲሚንቶ ፋብሪካ አካባቢ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ነበሩ። ወንጀሉ በጠራራ ፀሐይ ሲፈፀም በቅርብ ርቀት ላይ ሆነው እያዩ እና እየተኮሱ ነበር። ሆኖም ታጣቂዎቹ ሕዝቡን አሰልፈው ይዘው ሲሄዱ በአፋጣኝ የደረሰ አካል የለም" በዚያ መስመር ለመጓዝ መንግሥት ቀድሞ የፀጥታ ቅኝት ያደርጋል የሚሉት አቶ ታረቀኝ፣ ሰላም ነው ተብለው መንገድ ቢጀምሩም ከዚህ ጥቃት እና እገታ አላመለጡም።

ይህም የመንግሥት ኃይሎች የሚሳተፉበት የተቀነባበረ ሴራ እንዳለ እንዲጠረጥሩ አስገድዷቸዋል።

ተሽከርካሪዎች አዲስ አበባ መውጫ ላይ በጫንጮ እና በፍቼ ከተሞች በሚገኙ ኬላዎች ላይ ለረዥም ሰዓታት እንዲቆሙ ተደርጎ የመንገዱ ደኅንነት ይጣራል።ከፍቼ እስከ ሙከጡሪ፤ ከገርበ ጉራቻ እስከ ጎሃ ጽዮን ባሉት አካባቢዎች በመንገደኞች እና በአሽከርካሪዎች ላይ በርካታ ወንጀሎች ተፈፅመዋል።

ከእነዚህ ልዩ ቦታዎች መካከልም አሊ ዶሮ፣ ገርበ ጉራቻ፣ ሙከጡሪ፣ ቱሉ ሚልኪ፣ ጎርፉ ገብርኤል እና ዱበር የተባሉ አካባቢዎች እንደሚገኙበት አሽከርካሪው ይጠቅሳል።በተደጋጋሚ የአውቶብስ ተሳፋሪዎች በታጣቂዎች ታግተው የመወሰዳቸው ዜና እየተለመደ እንደመጣ የሚናገረው አሽከርካሪው፣ "እኛም ተራችንን ነው የምንጠብቀው" ይላል።