By Finfinne Press
* ከአንድ ሚሊዮን ሰው በላይ ያለቀበት ጦርነት አካሂደን ??
* ህገመንግስት ተሽሮ አንዱ የሌላውን መሬት በሃይል እንዲይዝ አድርገን ??
* ከአምስት ሚሊዮን ህዝብ በላይ ከመኖሪያው የተፈናቀለበት ቀውስ አዋልደን ??
* የጎረቤት ሀገርን በመጋበዝ የገዛ ህዝብን አስወርረን ??
* የመሳሪያ አፈሙዝን አማራጭ አድርገን ?? ወይስ ...
* ለIMF የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፈን ሰጥተን ??
* ከ29 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ከድህንነት ወለል በታች እንዲኖር አድርገን ??
* ሀገርን በከፍተኛ ብድር ጭማድ አስይዘን ??
* የህግ የበላይነት የተሻረበት ስርዓት ፈጥረን ?? ወይስ ..
* በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች ስራ አጥተው ተስፋ በመቆረጥ በባህር እንዲሰደዱ አድርገን ??
* ሀኪሞች ፣ መምህራን በደሞዝ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች በቀን አንዴ ለመብላት ያልቻሉበት ሀገር ገንብተን ??
* በኑሮ ውድነት የሚሰቃይ ፣ በዋጋ ንረት የሚታመስ ህዝብ እንዲኖር ሰርተን ??
* ከሁሉም ጎረቤት ሀገራት ጋር ቅራኔ ውስጥ ገብተን ??
* የዲፕሎማሲ ክሽፈት ፈጥረን ፣ ከአለም አቀፉ አለመተማመን እንዲኖር ሰርተን ??
* ወዳጆችን የሚያርቅ የውጭ ፖሊሲ ተከትለን ?? ወይስ
* ወጥቶ መግባት የማይቻልበት ፣ ሰርቶ መግባት አዳጋች የሆነበት የስጋት ምህዳር ፈጥረን ??
* የትጥቅ ትግል በየአካባቢው እንዲቀጣጠል በር ከፍተን ??
* ክልሎች እርስ በርስ እንዳይተማመኑ አድርገን ??
ወይስ ምን ሰርተን እንሞግት ??? ...
* ጥቂት ባለሃብቶች የሚዝናኑበት ሪዞርቶችና ፓርኮችን በከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ አድርገን የኢትዮጵያ ገፅታ ይህ ነው እንበል ?
* ለሀገር የሚጠቅሙ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ሳንገነባ ለብልጭልጭና ለመብራት ትኩረት እንስጥ ?? ... ወይስ
* ብሔራዊ መግባባት እያልን ከእራስ ጋር የሚደረግ ምክክር እያካሄድን እራሳችንን እንሸውድ ?? ....
በእርግጥም ብልፅግና ሰርቶ የሚቀናበት በሙግት የምናሳይበት ወይም ጥሩ ስራ ነው ተብሎ የሚደነቅበት አንዳች ነገር የለም !!
.
.
.
.