Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12461
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

አዲስ ድሮ ና ዘንድሮ፣ በአይን እማኝ እይታ!

Post by DefendTheTruth » 04 Jun 2025, 08:38

አዲስ ድሮ ና ዘንድሮ፣ በአይን እማኝ እይታ!

ከአመታት በፊት (in fact before decades) አዲስ ዉስጥ ስራ ይዤ ለተወሰነ ጊዜ ኖሬያለሁ። ትዝ ከምሉኝ ነገሮች ዉስጥ፣ አንደኛ የኑሮ ክብደቱ ነዉ። እንደ አዲስ ስራ ጀማሪ፣ ላጤ ና የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ሆኜ ደሞዙ አይበቃም ነበር፣ ግማሹን ወር ከዘለቅን፣ የተቀረዉን ግማሽ ደግሞ እንዲሁ መታገል ነበር፣ አንዳንዴም ምሳን ወይም ቁርስን መዝለል አዲስ ነገር አልነበረም። መናፈሻ የምባል ቦታ ይህን ያህል ስላልነበረ፣ ኪስ ዉስጥ ያለችንን ይዘን ያዉ ወደ የሆነ ሻዪ ቤት ወይም ደግሞ ሻል ያለ ቀን ድራፍት ቤት ነበር፣ መዝናኛችን የነበረዉ። የዛሬዉ ትዉልድ በዚህ ረገድ እድለኛ ነዉ፣ ብዙ መናፈሻዎች ተሰርቶለታል ና። የግድ መጠጥ ቤት ብቻ አይደለም ለመዝናናት ና የእረፍት ጊዜዉን ለማሳለፍ። የግንፍሌ ወንዝም ዘመን አልፎላት አሁን ላይ እንዲህ ያማረች ቦታ ሆናለች። ድሮ የግማት ቦታ ነበረች። ሁሉም ያልፋል ና።


DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12461
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: አዲስ ድሮ ና ዘንድሮ፣ በአይን እማኝ እይታ!

Post by DefendTheTruth » 04 Jun 2025, 08:50

ፅዱዋ አዲስ፣ ማራኪ፣ መንፈስ አዳሽ፣ እዛ ቦታ ላይ አለመኖሬ አስቀናኝ!


Post Reply