ስያሜ እና ምሳሌ፥ ኢትዮጵያ
Posted: 03 Jun 2025, 17:57
ኢትዮጵያ ከጥንት ግዜ ጀምሮ ያለ ቃል መሆኑ ታሪክን ላነበቡ በጣም ግልጽ ነዉ።
ተመሳሳይ ቃል ስለ ጥንት ግዜ የግሪክ ሰዉ እና የመሮዌ እመቤት ወዳጅነት የተጻፈ ዉስጥ ይገኛል።
ስለዚህ ኢትዮጵያ የጥንት ግዜ ስያሜ ነዉ። ያ ስያሜ የታሪካዊ ሃገር መጠርያ ሆነ።
ኦሪት ተብላ ቢሆን ኖሮ በሌላ ስያሜ ትታወቅ ነበር ማለት ነዉ። ሳብያ ተብላ የነበረ ቢሆንም እንዲሁ።
ለዚህ ስያሜ ምሳሌ የጥንት ግዜ ምስሎች ኣሉ። የፈረኦ ቱት ወይም ትዬን መጥቀስ ይቻላል። የሳባ ምስል ተቀርጾ የተገኘ መሆኑን ኣላዉቅም።
በዚህ ጥንታዊ ስያሜ እና ምሳሌ ዙርያ የተረጋጋች ጠንካራ ሃገር እንዲኖራቸዉ ሕዝቧን እንዴት ተሳናቸዉ?
ዉቅያኖስ ኣቋርጠዉ ኣዲስ ኣህጉር ዉስጥ ስንት ግፎችን ፈጽመዉ ምዕራባዊያን ለተባሉት ስያሜና ምሳሌ በኣጭር ግዜ ዉስጥ ገናና ከሆኑ የእኛስ ሕዝብ ለጥንታዊ ስያሜ እና ምሳሌ ጠንካራ መሆን እንዴት ተሳነን?
ለዚህ ጥንታዊ ስያሜ እና ምሳሌ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የኣንድ ሃገር ወገኖች ስለሆን ኣብረን እንጠንክር ማለት እንዴት ተሳነን?
ቋንቋ ነዉ ከተባለ ቆንቆ ማለት እና ቋንቋ ማለት ብቻ የሕዝቡን ጥንታዊነት ኣመልካች ነዉ።
ይህ ብቻ ሕግን የምናከብር እንጂ መንግስትን የማንፈራ ዜጎች ሆነን፣ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተባብረን ጠንካራ ሃገር ይኑረን ማለት ኣያስችልም ነበር?
እንተባበር ማለት ቅንነት ነዉ። ትብብር ያጠነክራል።
ኣሁን ከዐለም ሃገሮች በኢኮሮሚ በአረተኛ ደረጃ ለይ የምትገኝ ካሊፎርንያ አሜሪካ ስትቋቋም ተሳታፊ ኣልነበረችም። በኋላ ነዉ መጨመር እንፈልጋለን ብለዉ ልኡክ ወክለዉ ልከዉ እሺ ተብለዉ የተጨመሩት።
በቅርቡ የሰማሁኝ መልካም ዜና ጅቡቲ የኢትዮጵያ አካል ለመሆን ምኞት ኣሳየች የሚል ዐይነት ነበር።
ስም ይዞ ባህር አጠገብ ተወሽቆ ከመቀመጥ ስም ያለዉን ነገር ኣብሮ መስራት ያስችላል።
ሃገር ዉስጥ ያሉም ሆኑ ከሃገር ዉጪ ያሉ የኢትዮጵያ ፖለትካ ኣቀንቃኞች ጥንታዊ ስያሜዉን ሰምተን፣ ጥንታዊ ምሳሌዎቹን ኣይተን፣ ከጫፍ እስከ ጫፍ የኣንድ ፖለትካ ማህበረሰብ ስለሆን ተባብረን ጠንካራ ሃገር ይኑረን ማለት ምን ያህል ይከብዳል?