Page 1 of 1

BBC:-ከቤቱ ብሎም ከመኝታ ቤቱ ተወስዶ ችሎት ላይ የቀረቡት አቶ ታዬ ደንደአ የተያዙት 'ሊሸሹ ሲሉ ነው': OPDO

Posted: 03 Jun 2025, 15:59
by Za-Ilmaknun
የቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ባለቤት ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሰኞ ግንቦት 24/2017 ዓ.ም. አቶ ታዬ ከመኖሪያ ቤታቸው በፖሊሶች ተይዘው የተወሰዱ ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ግን የተያዙት "ሲሸሹ" ነው ተብሎ እንደቀረበ እንደነገሯቸው ገልጸዋል።

አቶ ታዬ ችሎት በቀረቡበት ወቅት ቤተሰብ እንዲሁም ጠበቃቸው አለመገኘታቸውን የተናገሩት ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ፣ "ከቤቱ ብሎም ከመኝታ ቤቱ ተወስዶ ችሎት ላይ ሲቀርብ ግን 'ስትሸሽ ነው ያገኘንህ' መባሉን ነገረኝ" ብለዋል።

ወ/ሮ ስንታየሁ አክለውም ወደ ቂሊንጦ ወርዶ ጉዳዩን እንዲከታተሉ መወሰኑንም ከአቶ ታዬ ደንደአ መስማታቸውን ገልጸዋል።

ዛሬ ችሎት ለመገኘት ጥረት ማድረጋቸውን የተናገሩት የአቶ ታዬ ጠበቃ አቶ አበራ ንጉሥ በበኩላቸው፣ በትናንትናው ዕለት ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ሲያውላቸው እና ቤታቸውን ሲበረብር "በሌላ ወንጀል የተያዙ እንጂ ይኼኛው መዝገብ አልመሰለንም ነበር" ብለዋል።

https://www.bbc.com/amharic/articles/c8d1l7re954o