Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6203
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

አያነ አባ ወይም የአባት ኣምላክ እና ደያብሎስ

Post by Naga Tuma » 02 Jun 2025, 16:51

አያነ አባ ወይም የአባት ኣምላክ ማለት ምን ማለት ነዉ?

በስመ ኣብ ማለትም ተመሳሳይ ጽንሰ ሀሳብ ያለዉ ይመስላል።

በልጅነቴ ስሰማ ያደኩኝ አያነ አባ ወይም የአባት ኣምላክ ማለት መለኮታዊ ጠባቂ እንደሆነ ነዉ ህሊናዬ ዉስጥ የተቀረጸዉ።

ጽንሰ ሀሳቡ ጥንት ግዜ ጀምሮ የነበረ ይመስለኛል። ቢሆን ነዉ አያነ አባ፣ የአባት ኣምላክ፣ በስመ ኣብ እየተባለ የሰነበተ የሚመስለኝ። ለምሳሌ ወልዳ ካሳደገችዉ ልጇ የተለየች እናት የአባቴ ኣምላክ ጠብቅልኝ ብላ ትተኛለች።

ቁልፍ ጥያቄ ከጥንት ግዜ ጀምሮ ምን ተስተዉሎ ነዉ ይህ አባባል የህዝብ ንቃተ ህሊና ዉስጥ ሰርጾ ገብቶ የሰነበተዉ?

ደያብሎስ ማለትም ከጥንት ግዜ ጀምሮ የህዝብ ንቃተ ህሊና ዉስጥ ሰርጾ ገብቶ የኖረ ነዉ። ተንኮለኛ እንደሆነ ነዉ የሚታወቀዉ።

አያነ አባ ወይም የአባት ኣምላክ እና ዳያብሎስ ሲጋጠሙ አያነ አባ ወይም የአባት ኣምላክ አሸናፊ ይሆናል። ካልዘነጋሁ እንዲሆንም ነዉ በስመ ኣብ የሚባለዉ።

ስለዚህ የሕዝብ ንቃተ ህሊና ዉስጥ ሰርጾ ገብቶ የሰነበተ ጽንሰ ሀሳብ ርቱዕ ጥናት ያለዉ ኣለ?