ኢትዮጵያ የተቀቀለ ሥጋ ወደ ቻይና ልትልክ ነው!
Posted: 01 Jun 2025, 07:24
ኢትዮጵያ የተቀቀሉ የሥጋ ምርቶችን ወደ ቻይና መላክ ልትጀምር መሆኑ ተገለጸ

የታሸጉ የስጋ ምርቶች- ከፋይል የተገኘ
25 ታህሳስ 2024
ኢትዮጵያ የተቀቀሉ የሥጋ ምርቶች እና ተረፈ ምርቶችን ለቻይና ገበያ ልታቀርብ መሆኑን የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክትር ዶክተር ሳህሉ ሙሉ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ኢትዮጵያ ለመላክ እየተዘጋጀች ያለችው የተቀቀለ የበግ፣ ፍየል፣ የዳልጋ ከብት እና የግመል ስጋን መሆኑ ዶ/ር ሳህሉ ገልጸዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ "በዚህ ደረጃ ምርቱን ለሚፈልጉ አገራት ነው እየተሰራ ያለው ግን በአሁን ለጊዜው ዒላማ ያደረግነው የቻይናን ገበያ ነው" ብለዋል።
ዶ/ር ሳህሉ "በዋናናት ታርጌት [ዒላማ] የተደረገው ትልቁ ገበያ የሆነውን የቻይና ገበያ [ነው]" ሲሉ የኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋ ዋና መዳረሻን ጠቁመዋል። ዋና ዳይሬክተሩ "ለቻይና ገበያ ዒላማ አድርገን እንስራ እንጂ ውጤቱ ምርታችንን ለሚፈልጉ ሁሉም ገበያዎች ሁሉ የሚሆን ነው" ሲሉ አክለዋል።
ምክትል ዳይሬክተሩ ከቻይና መንግስት እና ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር በተደረገ ንግግር "ከኢትዮጵያ የተቀቀለ የሥጋ ምርት እና ተረፈ ምርት እንደሚቀበሉ ይሁንታ ተሰጥቷል" ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c0q04jnpqxno.amp