
"መንገድ ጀምረን 30 ደቂቃ ሳይሞላ ጀልባው ይዋዥቅ ጀመረ። የየመን ሕገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች በአረብኛ ማውራት ጀመሩ። ስደተኞችን ከጀልባው ለመወርወር ነበር የሚመካከሩት። ከዚያም ሰባት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አስገድደው ወደ ባሕሩ ጣሏቸው"
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም (አይኦኤም) እንደሚለው፣ አብዛኞቹ ስደተኞች ጥያቄያቸው የኢኮኖሚ ቢሆንም በተለይ ከአማራ ክልል እና ከኦሮሚያ ክልሎች የሚሰደዱት ወጣቶች ግጭት እና እስራትን በመሸሽ ነው ከኢትዮጵያ የሚወጡት። "
100 ሺህ ስደተኞች 300 ዶላር ቢከፍሉ 30 ሚሊዮን ዶላር የሚገኝበት ሥራ ነው ማለት ነው" ይላሉ። በሳዑዲ የቤት ሠራተኛ ሆነው የተቀጠሩ እና በግንባታ ሥራ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ወደ 750 ሺህ እንደሚጠጉ ይገመታል።
Read it here....
https://www.bbc.com/amharic/articles/c3dkj88v30ko