Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Digital Weyane
Member+
Posts: 9676
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

ለመሆኑ ኡኛ ኢትዮጵያውያን መንግስት አለን ወይ? በሳዑዲ ሞት የተፈረደባቸው 47 ኢትዮጵያውያን

Post by Digital Weyane » 31 May 2025, 11:20

በሳዑዲ ሞት የተፈረደባቸው 47 ኢትዮጵያውያን



በደቡባዊ ሳዑዲ አረቢያ ናጅራን እስር ቤት የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የኢትዮጵያ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ሕይወታቸውን እንዲያተርፍ ተማጸኑ።

በእስር ቤቱ እስካሁን ሁለት ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ኃይሎች እንደተገደሉ እና ሌሎቹም ሞታቸውን እየተጠባበቁ መሆኑን የሞት የተፈረደባቸው ሁለት ስደተኞች ለቢቢሲ ገልጸዋል።

እነዚህ በእስር ላይ ያሉ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ 47 እንደሚሆኑ እነኚሁ ስደተኞች ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ አስረድተዋል።

“መቼ እንደምንሞት ባናውቅም ሞት ተፈርዶብናል። ዛሬ ልንገደል እንችላለን ወይም ነገ፤ አናውቅም። በጣም ፈርተናል። ለምን ሞት እንደተፈረደብኝ አላውቅም። ድንበር በሕገ ወጥ መንገድ አልፈሃል ነው የተባልኩት። ከታሰርኩ አምስት ዓመት ከአምስት ወር ሆነኝ” ሲሉ እኚህ ስደተኛ ለቢቢሲ ያደረባቸውን ከፍተኛ ፍርሃት በስልክ ገልጸዋል።

የሞት ፍርድ ሲፈረድባቸው እውነት ይሆናል ብለው እንዳላሰቡ ለቢቢሲ የተናገሩት ኢትዮጵያዊው ስደተኛ እስረኛ ባለፈው ሳምንት ሁለት ኢትዮጵያውያን እስረኞች መገደላቸውን ተከትሎ “የእኛም ዕእጣ ፈንታ ሞት እንደሆነ አወቅን” ይላሉ።

“በሞት እና በሕይወት መካከል ነው ያለነው። ሌሎቹ ከተገደሉ በኋላ መተኛት አልቻልንም” ሲሉ ተናግረው “መንግሥታችን ጉዳዩን እንዲሰማልን እንፈልጋለን” ሲሉ ተማጽነዋል።

አክለውም በእስር ላይ ስላሉት ኢትዮጵያውያን ባሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው “ኤምባሲ መጥቶ ጠይቆን አያውቅም” ሲሉ ተናግረዋል።

በእስር ቤቱ እያሉ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ በበኩላቸው “እዚህ እስር ቤት ያለው ስሜት አስጨናቂ ነው። ፈርተናል። ፖሊስ ወደ እስር ቤት ወረቀት ይዞ በመጣ ቁጥር የሚገደል ሰው ሊወስድ ነው ብለን እንፈራለን። ጠዋትም ማታም ሲመጡ እንደነግጣለን። አሁን ሞትን እየጠበቅን ነው። ምንም ማድረግ አንችልም። ሞታችን የማይቀር ነው” ሲሉ በከፍተኛ ሐዘን ተናግረዋል።

በርካታዎቹ ሞት የተፈረደባቸው ግለሰቦች ያለ ጥፋታቸው እንደሆነ የሚናገሩት ስደተኛ እስረኛው የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳዑዲ መንግሥት ጋር ተነጋግሮ ሕይወታቸውን እንዲታደጋት ተማጽነዋል።

ስደተኛው ኢትዮጵያ ወዳሉ ቤተሰቦቻቸው ደውለው የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ከሳዑዲ መንግሥት ጋር እንዲነጋገሩ ጥያቄ እንዲያቀርቡ መናገራቸውን ገልጸዋል።

“ወደ አገር ቤት ደውለን ቤተሰቦቻችን መንግሥት ጋር ሄደው ከሳዑዲ መንግሥት ጋር እንዲያወሩ ጠይቀውልን ነበር። እንደሚነጋገሩ ቃል ሲገቡላቸው ቤተሰቦቻችን ተመለሱ። መፍትሄ እንደምናገኝ ለቤተሰቦቻን ቃል ቢገባላቸውም እኛ ግን መፍትሄ አላገኘንም” ብለዋል።

አክለውም “ብዙ ሰዎች ሞት ተፈርዶባቸዋል። እስካሁን ሁለቱ ተገድለዋል።. . . አደንዛዥ ዕጽ አስገብታችኋል ተብለው ነው የተከሰሱት። የኢትዮጵያ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ከሳዑዲ መንግሥት ጋር ተነጋግሮ ያድነን። የተከሰሱት በሐሰት ነው። ያለ ጥፋት ነው እየተገደሉ ያሉት” ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የሞት ቅጣት መፈጸም እንደ አዲስ የተጀመረ እንደሆኑ የገለጹት ስደተኞቹ ከዚህ ቀደም የሞት ፍርድ ተፈጻሚ የሚሆነው በሰው ግድያ ወንጀል የተከሰሱ ናቸው ይላሉ።

ቢቢሲ ኢትዮጵያውያኑ በምን ዓይነት ወንጀል ተከሰው ሞት እንደተፈረደባቸው ከእስር ቤቱ ባለሥልጣናት ማረጋገጥ አልቻለም።

በሳዑዲ አረቢያ ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር በተያያዘ በእስር ቤቶች የሚፈጸሙ ግድያዎች በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡ ስጋት እንደፈጠረባቸው የሰብዓዊ መብት ተቋማት በያዝነው ዓመት መስከረም ወር ላይ የካይሮ ኢንስቲትዩት ፎር ሂውማን ራይት ስተዲስ ድረ ገጽ ላይ በወጣ ጥሪ አስታውቆ ነበር።

ተቋማቱ በሳዑዲ በሚገኘው ታቡክ እስር ቤት በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ሕይወታቸው አደጋ ላይ እንደወደቀ ገልጸው ካለፈው ዓመት ጥር ጀምሮ ስምንት እስረኞች በሞት መቀጣታቸውን ገልጸዋል።

Odie
Member
Posts: 4249
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: ለመሆኑ ኡኛ ኢትዮጵያውያን መንግስት አለን ወይ? በሳዑዲ ሞት የተፈረደባቸው 47 ኢትዮጵያውያን

Post by Odie » 31 May 2025, 11:26

አብቹ ክልላቸውንና ዘራቸው እንደሚሟገትላቸው ነው የሚያውቀው:: ስለዚህ ዝርዝሩ በዘርና በክልል ተጣርቶ ለብልፅግና ወኪል ለሆሮስ ይቅረብ ብልዋል!

ደግሞም ይህ የሚያስጨንቃቸው የወደፊት ራእይ የሌላቸው ናቸው:: እኔ ራእይ እያየሁ ነው ድሮም እኔ ሳውዲ ሂዱ መች አልኩ የራሳቸው ጉዳይ ነው ብለዋል :lol: :lol:


Post Reply