Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Fiyameta
Senior Member
Posts: 17706
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

❗ አሳዛኝ ልብ ሰባሪ ዜና ተሰማ ❗ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ያለበት የውጭ ዕዳ መጠን ከ575 ዶላር በላይ መድረሱ ተነገረ ‼️

Post by Fiyameta » 29 May 2025, 16:53



እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ያለበት የውጭ ዕዳ መጠን ከ575 ዶላር በላይ መድረሱ ተነገረ




ሳሙኤል አባተ
May 25, 2025


እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ያለበት የውጭ ዕዳ መጠን 575.6 ዶላር መድረሱን፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ባወጣው ሪፖርት ገለጸ፡፡

አሶሴሽኑ የአገሪቱን ከ2021 እስከ 2023 የኢኮኖሚ አፈጻጸም አስመልክቶ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. እስከ 2023 ድረስ ያለባት የብድር መጠን 62.5 ቢሊዮን ዶላር መድረሱንና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊም የተጠቀሰው መጠን የውጭ ዕዳ እንዳለበት ጠቁሟል፡፡

የብድር ጫናው እንዲበዛ ካደረጉ ምክንያቶች መሀል የመንግሥት ወጪ አስተዳደር አቅም ማነስ፣ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ደካማነት፣ ኢኮኖሚውን ሊደግፉ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን አለማስፋት፣ የወጪ ንግድ መቀዛቀዝና የማምረት አቅም እየቀነሰ መምጣት ዋነኞቹ እንደሆኑ በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡

በማኅበሩ ከፍተኛ የማክሮ ኢኮኖሚ ተመራማሪ ናስር የኑስ (ዶ/ር)፣ ከዚህ በፊት አገሪቱ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ከተለያዩ ተቋማትና አገሮች የተበደረቻቸው ብድሮች ውጤታማ አለመሆናቸው ዋነኛ የብድር ጫና ምክንያት መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የብድር መክፈያ ጊዜን በመደራደር እንዲራዘም ማድረጓ ጥሩ ቢሆንም፣ ሊከፈል የነበረውን ገንዘብ አሁንም ኢኮኖሚውን መደጎም በማይችሉ መንገዶች ወጪ ከተደረገ የዕዳ ጫናው ይጨምራል እንጂ ሊቀንስ እንደማይችልም ተመራማሪው ተናግረዋል፡፡

የመንግሥት ወጪ በተቀናጀና ኢኮኖሚውን በሚጠቅም መንገድ ካልተተገበረ ዕዳ መክፈል ከማይችሉ አገሮች መካከል እንድትመደብ ከማድረግ ባለፈ፣ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ያልሆነች አገር እንድትሆን ያደርጋታልም ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት ከዓለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማትና አገሮች የተገኙ ብድሮች ባደረሱት ጫና ምክንያት፣ መንግሥት በወጪ ቅነሳ ላይ መቆየቱ ለኢኮኖሚው መቀዛቀዝ ተጨማሪ ምክንያት እንደሆነም ተመራማሪው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከወጪ ንግድ ከሚገኘው ገቢ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ የብድር ጫና ካለባቸው አገሮች መካከል አንዷ የሚያደርጋት እንደሆነ፣ ከዓመታዊ ምርት ወይም ጂዲፒ አንፃር ደግሞ በአማካይ ላይ እንደሆነች በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

መንግሥት የገጠመውን የገንዘብ እጥረት ለመፍታት ከግብር የሚሰበስበውን መጠን በየዓመቱ እያሳደገ መሆኑን የተናገሩት ናስር (ዶ/ር) ጭማሪው ተቀጣሪና መደበኛ የሥራ መስኮችን ዒላማ ያደረገ በመሆኑ የዋጋ ግሽበትን ከማባባስ ባለፈ አገራዊ የኢኮኖሚ መረጋጋትን አላመጣም ብለዋል፡፡

በመሆኑም መንግሥት ለኢኮኖሚው ተጨማሪ አቅም የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን ማስፋት፣ አዳዲስና ያልተለመዱ የግብር መሰብሰቢያ አማራጮችን በመፈለግ የዋጋ ግሽበትን በማያባብስ፣ ከተቋማት ጋር መናበብን መሠረት ባደረገ መንገድ እንዲተገበርም ተመራማሪው አሳስበዋል፡፡

በከተማ ከሚኖረው ማኅበረሰብ ውስጥም ከ25 በመቶ በላይ የሆኑ ሴቶች ሥራ አጥ ናቸው የተባለ ሲሆን፣ አገሪቱ ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ እየተገበረችው ያለው የሥነ ሕዝብ ፖሊሲ ከአሁኑ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተመጋጋቢ እንዳልሆነም ተገልጿል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2020 ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት ተገማች አለመሆን፣ የሕዝብ እምነት ማጣት፣ መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸው የልማት ሥራዎች መኖር፣ ግጭቶችና የውጭ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች መቀነስ የመንግሥትን አቅም እንዳዳከሙ አሶሴሽኑ በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

https://ethiopianreporter.com/141688/


Fiyameta
Senior Member
Posts: 17706
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ❗ አሳዛኝ ልብ ሰባሪ ዜና ተሰማ ❗ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ያለበት የውጭ ዕዳ መጠን ከ575 ዶላር በላይ መድረሱ ተነገረ ‼️

Post by Fiyameta » 29 May 2025, 18:03

This is so sad. But what's even more sad is that, the regime borrows billions more to spend on media propaganda to cover up the debt and economic crisis in the country. The propagandists are known to sell their own mothers for $1. :x :x

Digital Weyane
Member+
Posts: 9674
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: ❗ አሳዛኝ ልብ ሰባሪ ዜና ተሰማ ❗ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ያለበት የውጭ ዕዳ መጠን ከ575 ዶላር በላይ መድረሱ ተነገረ ‼️

Post by Digital Weyane » 29 May 2025, 18:18

ባንዳነት ማለት እየተከፈለህ የውክልና ጦርነት የምትዋጋ ይመስለኝ ነበር ለካስ ተበድረህ ነው የውክልና ጦርነቱ የምትዋጋው። በአለማችን ታይቶ የማይታወቀውን የድድብና ጥግ ያላየንበት ጊዜ የለም። ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ :cry: :cry: :cry: :cry: :cry:





Fiyameta
Senior Member
Posts: 17706
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ❗ አሳዛኝ ልብ ሰባሪ ዜና ተሰማ ❗ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ያለበት የውጭ ዕዳ መጠን ከ575 ዶላር በላይ መድረሱ ተነገረ ‼️

Post by Fiyameta » 31 May 2025, 04:06

The only people that can afford to pay their $575 debt are the former-TPLF-cadres-turned-PP-cadres who earn $1,700 a month defending Abiy and UAE. :shock: :shock: :shock:



Post Reply