Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum


Selam/
Senior Member
Posts: 15409
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: የሌላ ቋንቋ ሙዚቃ ስትሰማ የሚያምህ ከሆነ፣ በጎጥ ነቀርሳ ተይዘሃልና ሃኪም ጋ ሂድ‘

Post by Selam/ » 29 May 2025, 12:28

I love it!
Dama wrote:
29 May 2025, 12:22
Esa Eso is also one of Gurage's traditional muic. Selam lirdash biye new! :lol: :lol:


Meleket
Member
Posts: 4569
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የሌላ ቋንቋ ሙዚቃ ስትሰማ የሚያምህ ከሆነ፣ በጎጥ ነቀርሳ ተይዘሃልና ሃኪም ጋ ሂድ‘

Post by Meleket » 30 May 2025, 04:18

Selam/ wrote:
29 May 2025, 11:21
የሌላ ቋንቋ ሙዚቃ ስትሰማ የሚያምህ ከሆነ፣ በጎጥ ነቀርሳ ተይዘሃልና ሃኪም ጋ ሂድ‘
Selam/ ግሩምና ድንቅ ኣባባል ነው ። ሙዚቃን “ኣድማሳዊ ቋንቋ” ይሉታል ኤርትራዉያን ሙዚቀኞች።

ኢትዮጵያዉያን ቦለቲከኞች ኤርትራዊ ኢንስትሩመታል ሙዚቃን፡ ኤርትራዉያን ቦለቲከኖችም ኢትዮጵያዊ ኢንትሩመንታል ሙዚቃን እንዲያጣጥሙ ቢደረግ፡ እርስበእርስ መናቆራቸው ከንቱ መሆኑ ፍንትዉ ብሎ በታያቸው ነበር!

እስቲ በየማነ ባርያ ሙዚቃ ተዝናኑ! viewtopic.php?f=2&t=328834&p=1421247&

Meleket wrote:
26 Sep 2023, 04:36
ጊታር ወዳዶች ይህቺ ዜማ እንዳታመልጣችሁ . . . .

በተለያየ ምክንያት ወደ ተለያዩ ሃገሮች የተሰደዱ እልፍ ኣእላፍ ኢትዮጵያውያን ይቺን የየማነ ባርያ ዜማ ከነግጥሟ ለማጣጣም እድል ካገኙ፡ የኤርትራ ህዝብ የማነ ገብረሚካኤል (ባርያ)ን ለምን እንደሚወደው ፍንትው ብሎ ይታያቸዋል። የማነና በዚህች ዜማው ውስጥ የተሳተፉ ሙዚቀኞች ምን ያህል ከሱ ሓሳብ ጋር እንደተጣጣሙ ለማዬት የጊታሪስቱን ቁዘማ በመስማት ለመመስከር ይቻላል።

የማነ በግጥሙ እንዳብራራው ስደት አሁን አይደለም የጀመረው፡ ብዝበዛ፡ የሰውን መመኘት፡ በሃይል ብቻ የማመን የጡንቸኞች ኣባዜ ወዘተ ከጥንት የነበረ ነው፡ ገና የሰው ልጅ ሳይሰለጥን። አሁንም ባልሰለጠኑት ህዝቦች መካከል ይህ እኩይ ተግባር ስላለ፡ ስደትም ቀጥሏል። ስደት የሚያቆመው ጨቋኝና ተጨቋኝ የሌለበት ሁኔታ በትግል መጐናጸፍ ሲቻል ብቻ ነው ይለናል፡ ሰላምም በልመና ሳይሆን በትግል እንደምትገኝም ግልጽ አድርጎልናል ነብዩ የማነ ባርያ።

https://sonichits.com/video/Yemane_Bary ... he_Yu_Sdet

ስደት

ዛሬ ገና ኣይደለም የጀመረው ስደት፡
እርስበእርስ ውጊያና ጭካኔና ሁከት፡
ከጥንት የቆዬ ነው ዓለም ስትፈጠር፡
ገና ሳይሰለጥን ሰው ሳለ ኋላቀር።

ይሸጥም ነበረ የሰው ልጅ በዋጋ፡
ታስሮ በሰንሰለት ተመዝኖ ስጋ።
አጥንትና ስጋ ወርደው ወደ ገበያ፡
ለጭካኔያችን ጥግ ሆነዋል መታያ።

ከጥንት ከጥዋቱ ዓለም ሳትሰለጥን፡
ያኔ ጀምሮ ነው ሰላም የጠፋችን።

አሁን በዚህ ዘመን በስልጡኑ ግዜ፡
የሰውን መቀማት የኃይለኛ አባዜ፡
ኣልቀረም ገና ኣለ፡ ይሻዋል ኑዛዜ።
ስለሆነም ስደት አሁንም ቀጥሏል፡
ከግፈኞች ሽሽት ይበልጥ ተፏፉሟል።

አንዳንዴ ጦርነት ሰላምን ይጠራል፡
ጡንቻ ሲተባበር ገዢን ይዘርራል።
የጭቁኖች ትግል በፍጹም አይጠፋም፡
ጦርነትን አልፋ ትመጣለች ሰላም።

ሰላም አትገኝም በመለማመጥ፡
ሰው እስካላቆመ የሰው ደም መምጠጥ፡
በሃሳብ ተባብሮ በዝባዥን መዘርጠጥ።

ሰላም አትገኝም በመሞዳሞድ፡
ሰው እስካላቆመ የሰው ስጋ መጎመድ፡
ኃይልን አስተባብሮ ገዥን ማርበድበድ፡
ግፈኛን ደርምሶ በኃይል መናድ።

ጨቋኝና ገፊ፡ ገዢ ኃይል ሳይጠፋ፡
የሰላም ዘንባባ ኣትበቅልም በተስፋ፡
የሰላም ዘንባባ ኣትመጣም በተስፋ።


ሱዳን ውስጥ የማነ በስደት ይኖር በነበረበት ወቅት፡ ወላጅ እናቱ ሊያዩት ወደ ሃገረ ሱዳን ያመራሉ። ወቅቱ ብርቱ ረሃብና ድርቅ የነበረበት ግዜ ነበር። እህልም ስኳርም ያኔ እጅግ ተወዶ ነበር ኣሉ፡ ታድያ ዬዋሁ የማነ ጆንያ ሙሉ ስኳርና ውሃ ቤቱ በራፍ ላይ ያስቀምጣል። ማንም ኣላፊ ኣግዳሚ የተራበና የተጠማ ዜጋ ስኳሩን እየበጠበጠ እንዲጠጣው መሆኑ ነው። ታድያ እናቱ ይሄን ጆንያ ሙሉ ስኳር በራፋቸው ደጅ ላይ መተውን በማዬት፡ ለሚስቱ “ልጄ እባክሽ ይህን ጆንያ ሙሉ ስኳር ወደ ቤት ውስጥ አስገቢው፡ ለምን በራፍ ላይ በጸሃይና ንፋስ ይሰጣል” ይላሉ። የየማነን ባህርይ ጠንቅቃ የምታውቀው ሚስቱ ሃረገወይንም “ኣዬ እማማ፡ ይህችን ጆንያ ስኳር ወደ ቤት ካስገባኋት፡ የማነ ሌላ ጆንያ ስኳር ገዝቶ እዛችው ቦታ ላይ ያስቀምጣል!” እንዲህ ነው የማነ ባርያ፡ የመስጠት ምሳሌ በመሆን በኤርትራውያን መካከል ሁሌም የሚዘከረው።

የዓለም የስደተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ይህንን ከተካፈልን ዘንዳ፡ በቀጣይ ደግሞ ከዜሞቹ የኣንዷን ግጥሞች እንካፈላለን።





Post Reply