የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአነጋጋሪ ሁኔታ ለኢትዮጵያውን "የ34ተኛ ዓመት የነጻነት በዓል" መልዕክት አስተላለፉ
ከ 4 ሰአት በፊት
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በአነጋጋሪ ሁኔታ ለኢትዮጵያውን "የ34ተኛ ዓመት የነጻነት በዓል" የመልካም ምኞች መግለጫ አስተላለፉ።
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋዊ ድረ ገጽ ላይ የወጣው የማርኮ ሩቢዮ መግለጫ የተላለፈው ትናንት ማክሰኞ በግንቦት 20 ዋዜማ ነው።
ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ምላሽ ባያገኝም፤ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በይፋዊ ገጹ ላይ የወጣው ጽሁፍ መነሳቱን ቢቢሲ ተመልክቷል።
በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ውስጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ሩቢዮ ማክሰኞ ግንቦት 19/2017 ዓ.ም. ያወጡት መግለጫ፤ "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀን" የሚል ስያሜን የያዘ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው "በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ስም ለ34ተኛው የነጻነት ክብረ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ [መልካም ምኞቴን] አቀርባለሁ" ብለዋል።
አቢይ ደውሎ ሲያለቃቅስ ይቀይሩታል እንደ "ሕዝባቹ በድሮን አትግደሉ" መግለጫ

