Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 13922
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ተጣማጅ አርበኛ በአገር መውደድ ቀንበር...ዐርበኞቹ ሲዘምሩ ሰምታ የባንዳዋ ልጅ "ጽምዶ" እኔ ተጣማጅ። የሸዋ አማራ ጥላቻ ያናወዛቸው ሱሪ ያስታጠቀውን ኃ/ማርያም ማሞ አገር።

Post by Abere » 28 May 2025, 08:47

ተጣማጅ አርበኛ በአገር መውደድ ቀንበር፣
ገዳይ ድል አድራጊ ደም አፍሳሽ ወታደር፣

ገናናው ክብራችን ሰንደቅ ዓላማችን፣
ያኮራሻል አርበኝነታችን፡

ዐርበኞቹ ሲዘምሩ ሰምታ የባንዳዋ ልጅ "ጽምዶ" እኔ ተጣማጅ ብላው እርፍ። የሸዋ አማራ ጥላቻ ያናወዛቸው ፈረሱን እንደ ሰው ሱሪ ያስታጠቀውን ኃ/ማርያም ማሞ አገር።
ሰሞኑን በኤርትራ የባርነት መታሰብያ ዕለት ኢሳይያስ አፈወርቅ የተናገረውን ሰማሁና ሳቅሁኝ - በግርምታ። እርሱም ባንዳ አይደለሁም የሚል ነበር። ለመሆኑ የአስካሪ ተውላጠ ስም ባንዳ መሆኑ ጠፋበት ወይ ነው ያልኩት። ጅብ ከማያውቁት አገር ሂዶ ቆዳ አንጥፉልኝ አይነት ዲስኩር ነበር። ከመረብ ወዲህ ያሉት "ፅምዶዎች" ታሪካቸውን የረሱ ይመስላሉ። ምን ምን ካላልከው ገብቶ ይፈተፍታል ነው እና 30 ሺ እና 40 ሺ ባንዳ ይዞ ለጣልያን ወግኖ ኢትዮጵያን ያደማው ባንዳ ከታሪክ ማህደር ሊፋቅ አይቻልም።

ታሪካችን የሚያውቀው ተጣማጅ ዐርበኛ እንጅ ፅምዶ ባንዳ አይደለም።


Post Reply