Re: ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል ከፈለጋችሁ የእግዚአብሔርን ሕግ አትጣሱ። ሰውን አታምልኩ፣ ኤምሬቶችንም ቢሆኑ።

እኛ በልጽገናል!
እኛ በልጽገናል በእውነት ከፍ ብለናል፣
ለውጥም አምጥተናል ብዙ ተምረናል፣
አው እኛ በልፅገናል ደረጃም ይዘናል።
አበት አንዳንዶቹ አበት ከፍታቸው፣
የፊት ቦርጫቸው የኃላ ገፃቸው፣
እውነት በልጽገዋል እንዲሁ ስታያቸው።
አበት ኩራታቸው አበት ጥጋባቸው
እንዲሁ ስታያቸው ይለያል ስራቸው🥺
ዘይቱ ሰንበት ብሏል እኛን ከሸወዴ፣
የሳሙናስ ተውት ሰማይ ሰቅሏል በአንዴ፣
ጤፉም ሃይ ባይ ጠፍቶ ወዳጁን ክዶታል፣
ሞትም ያለወትሮው በእውነት ተደፋፍሯል፣
ድንች ነበር የኛ እሱም ከፍ ብሏል፣
ቲማቲም ራሱ ቁርጥ ካልሆንኩ እያለ፣
በግም ደረት ነፍቶ በሬዎች ጋር እየዋለ።
ዳቦም ዳሩን ይዞ ይዋኛል በተራው፣
የሽንኩርቱን ተውት የሱስ የባሰ ነው፣
አትክልት ፈራፍሬው ደረቁም እርጥቡም፣
የሚለበስ የሚበላም የሚታይ የማይታይም፣
ትንሹም ትልቁም ረጅሙም አጭሩም
ያልተለወጠ ያልናረ አልተገኘም .......
እነ አትክልት እነ ፍራፍሬ፣
እነ ዳቦና ጤፍ እነ ጥራጥሬ፣
እናንተ ተረኞች ለውጥ ፈላጊዎች
እናንተ ጎበዞች እንባ ጠባቂዎች
በእውነት በልጽጋቸዋል ታርክም ሰርታቸዋል፣
የሰዉ ልጅ የማይረሳው ክስተት አሳይታቸዋል፣
ለሁሉም የሚሆን መንገድም ፈጥራቸዋል።
ታዲያ ማነው ያላደገው ያልበለጸገው?
ማነው ከፍ ያላለው ደረጃ ያልየዘው?
ንገሩኝ እስቲ! ለውጥ ያልታየው በማነው?
Re: ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል ከፈለጋችሁ የእግዚአብሔርን ሕግ አትጣሱ። ሰውን አታምልኩ፣ ኤምሬቶችንም ቢሆኑ።
I appreciate the advice, but I found out it’s from Esu’s soulless slave, Skuni. I’m sorry for you, Sister.