Page 1 of 1
ጽምዶ ማለት ጥምዶ ወይም ጭምዶ ማለት ነዉ?
Posted: 28 May 2025, 00:18
by Naga Tuma
ጽምዶ የግዕዝ ቃል ነዉ?
ጽምዶ ጽምዶ ሲሉ ስለ መለኮታዊዉ ጽምዶዎች ይሆን ብዬ ነበር።
Re: ጽምዶ ማለት ጥምዶ ወይም ጭምዶ ማለት ነዉ?
Posted: 28 May 2025, 06:26
by sarcasm
ቃሉ ሁለት አካላት አንድ ስራ ላይ መቀናጀት ይገልጻል። አንድ በሬ ከአንድ በሬ ጋር አቀናጀ፤ ጠመደ። ጥንድ በሬ ፡ በአንድነት እርሻ ላይ የሚሰማሩ የተቀናጁ ሁለት በሬዎች። ወንድና ሴት አንድ ቤተሰብ ሲሆኑ። ባልና ሚስትም ጥንድ ሊባሉ ይቻላል? ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚለው የፀሐዬ ዩሐንስ ዘፈን አስታወኩኝ። Partnership or alliance በእንግሊዘኛ ሊገልጹት ይችላሉ። በአማርኛ ደግሞ ቅንጅት መቀናጀት ሊገልጹት ይችላሉ።
ጥንድነት (ጥምድነት) is probably the exact translation.
Naga Tuma wrote: ↑28 May 2025, 00:18
ጽምዶ የግዕዝ ቃል ነዉ?
ጽምዶ ጽምዶ ሲሉ ስለ መለኮታዊዉ ጽምዶዎች ይሆን ብዬ ነበር።