አበረ፣
ይህ እንግዲህ ሰሞኑን ስለው የነበረው ነው። የእስክንድርም ሆነ የዘመነ ቡድን ለድርድር መቅረቢያ የሚሉትን መስፈርት እንደ ሚያዘጋጁ ሳይታለም የተፈታ ነው።
ይህ ማሲንጋ የተባለ ኢትዮጵያ ጠል ወጠጤ የነካው ነገር በፍጹም አይሳካም ፤ እሱ ከኢትዮጵያ ሳይኮሎጂ ጋር ጭግር ያለው ጥቁር ነው።
ትላንት ማታ አቢይ ድሮን መጠቀም የለበትም ብሎ ቱስ ቱስ ካለ በኋላ ዛሬ ያ ቃሉን ዲሊት አደረገው ። እሱም እነ አቢይን አያከብርም ፣ እነሱም ከጤፍ አይቆጥሩትም።
ወደ ዘመነ ካሴ መግለጫ ስንመጣ ዛሬ የለቀቁት ባለ 9 ነጥብ አጀንዳ ለአቢይ ወይም ለአሜሪካ ተብሎ የተጻፈ ሳይሆን ለሚቃወማቸው አማራ የተዘየደ ነው ። ለምን በለኝ?
ሰዎቹ ያሉት ካቢይ ለመነጋገር ፌዴራል መንግስቱ ሙሉ በሙሉ ካማራ ከወጣ ፣ የብልጽግና በሙሉ ከተዘጉ ፣። ፋኖ የሚያዝበት የአማራ ሽግግር መንግስት ባህር ዳር ከቆመ ፣ አለም አቀፍ ድርጅት ያቢይ መግስት ዘር ማጥፋት ከመረመረ እና መተከል ፣ ሸዋ ፣ ራያና ወልቃይት ላማራ ከተመልሱ በኋላ ነው ለድርድር የምቀርበው የሚለው ቡድኑ ። ይህን መሰል መግለጫ ለሚቃወማቸው አማራ ማማለያ እንጂ የምር ፖለቲካም ሆነ የድርድር መቅረቢያ መስፈር አይደለም።
ይህን መግለጫ ከቀሩት በግልጽ የሚለየው ይህ የጎጃሜዎች ቡድን ምንም አይነት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደ ማይመለከተውና 1000% ፕሮግራሙ የአማራ ክልል ምናልባትም የጎጃም ጠ/ግዛት ብቻ እንደ ሆነ ነው። ለዚህም ነው ተገንጣይ ጎጃሜ ያልኳቸው ።
ይህ ለይምሰል ስር ነቀልና ራዲካል የሚመስል ባዶ መግለጫ ግን ምን ያክል የልጅ ጨዋታ እንደ ሆነ ተመልከት ፡
(1) ላማራ እንታገላለን የሚሉት አክቲቪስቶችና ተዋጊዎች ገና እራሳቸው አንድ ሆነው አንድ ድርጅት እንኳ መፍጠር ያልቻሉ፡
(2) አንድ ወጥ የሆነ ያማራ ፖለቲካም ሆነ ራዕይ የሌላቸው
(3) አንድ፣ ሰው ሁሉ ይህ ነው የሚለው የአማራ አላማ ይህ ነው ያልፈጠሩ
(4) ያጭር ግዜ ፕሮግራም ሆነ የረጅም ግዜ ፕሮግራም አቅርበው ሕዝብ ያላሳመኑ
(5) ከራሳቸው ጓዶች ጋር የሚዋጉና እንዲያውም ስማቸው ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመጨማለቅ ላይ ያለን ቡድን ባንክ ታንክና አይሮፕላን ከታጠ አንድቀ መንግስት ጋር ስልጣን ሳይለቅ አልደራደርም ማለት አንድም ቀልድ አለያም የፖለቲካ መሃይምነት ነው ። ይህን በማለታቸው ብቻ የሞራል የበላይነቱን ለአቢይ እየሰጡት ነው ።
አሜሪካ ገና በፕሪቶሪያ የጋገረው ቂጣ ሳይበስል ለሌላ ፕሪቶሪያ ቱስ ቱስ ማለቱ ያው ባፍሪካ ቀንድ ያጣውን ተሰሚነት ለመመለስ መታተሩ ነው።
!
የሚገርመው ግን ማሲንጋ ይህን ሁሉ ቱስ ቱስ ሲል አቢይ አውሮፓን እየዞረ ነው! ፋሞ በዛሬ ቁመናው ያቢይ መንግስትን የሚያሰጋ ኃይል አይደለም! የቲክ ቶክ ሆያ ሆዬን ወደ ጎን ካደረግን