Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4364
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

BBC:በኦሮሞ ዲሞክራሲ ፓርቲ (OPDO) ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉ የጤና ባለሙያዎች ስም ዝርዝር አስከ አርብ ከሰዓት በኋላ ድረስ 81 ደረሰ

Post by Za-Ilmaknun » 16 May 2025, 13:39

ቢቢሲ የተመለከተው እና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ የሕክምና ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉ የጤና ባለሙያዎች ስም ዝርዝር አስከ አርብ ከሰዓት በኋላ ድረስ 81 መድረሱን ያመለክታል።አዲስ አበባ የሚገኙትን ጥቁር አንበሳ እና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎችን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በርካታ የጤና ባለሙያዎች ከሆስፒታል እና ከቤታቸው በፀጥታ ኃይሎች እየተወሰዱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።

23 የጤና ባለሙያዎች ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል የታሰሩ ሲሆን፤ ስምንት የሚሆኑ ሐኪሞች ትናንት ሐሙስ ግንቦት 7/2017 ዓ.ም. እኩለ ሌሊት ላይ ከዩኒቨርስቲው የጋራ በመኖሪያ ቤት "በመከላከያ፣ በአድማ ብተና እና በሚሊሻ አባላት" ተወስደው መታሰራቸውን ባልደረቦቻቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ባፉት ቀናት በርካታ ሆስፒታሎች በሥራ ላይ የማይገኙ ባለሙያዎች ላይ "አስተዳዳራዊ እርምጃ" እንደሚወስዱ ማስጠንቀቂያዎችን ያወጡ ሲሆን፤ ሬዝደንት ሐኪሞች ደግሞ የሕክምና ኮሌጆች ከሚያቀርቡት "መኖሪያ ቤት" ለቀው እንዲወጡ አሳውቃል።

'የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ' አስተባባሪዎች ከመንግሥት አዎንታዊ ምላሽ ባለማግኘታቸው ሙሉ ለሙሉ የሥራ ማቆም አድማ ከሰኞ ጀምሮ ለመምታት የያዙትን አቅድ እንደሚገፉበት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

https://www.bbc.com/amharic/articles/cn8zxd33d0xo