Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4364
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Reporter: በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ የነበሩ ባለሀብቶች ማሽኖቻቸውን ከአገር ለማስወጣት ጥያቄ እያቀረቡ ነው ተባለ

Post by Za-Ilmaknun » 12 May 2025, 12:04

https://www.ethiopianreporter.com/141212/

በዘጠኝ ወራት ከ37 ሺሕ በላይ ሠራተኞች መልቀቃቸው ተነግሯል!

በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በሚገኘው ኢንዱስትሪ ፓርክ የተሰማሩ ጦርነት ሸሽተው የወጡ ባለሀብቶች፣ ማሽኖቻቸውን ከአገር ለማስወጣት ጥያቄ እያቀረቡመሆናቸውን፣ የኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ።
በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ከአገር ሸሽተው የሄዱ ባለሀብቶችን ለረዥም ጊዜያት በኢንተርኔትና በአካል በመገናኘት ኩባንያዎቻቸው ተመልሰው ወደ ልማት እንዲገቡጥረቶች ቢደረጉም ፍላጎት አለማሳየታቸውን፣ በኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽንና ማኔጅመንት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሚል ኢብራሂምተናግረዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ በዘጠኝ ወራት 128 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ምርት ወደ ውጭ ለመላክ ታቅዶ አፈጻጸሙ 83 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ወይም የዕቅዱን 65 በመቶ ብቻመሆኑን ኮርፖሬሽኑ ያቀረበው ሪፖርት ያስረዳል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሀ ይታገሱ (ዶ/ር) በዘጠኝ ወራት ለታየው የውጭ ምንዛሪ ማነስ ምክንቱን ሲያብራሩ፣ በግጭትና በአጎዋዕገዳ ሳቢያ ገቢ የመጨመር ሳይሆን እ.ኤ.አ. ከ2021 ጀምሮ የመቀነስ ሁኔታ እየታየ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ኢንቨስትመንት ሰላምና መረጋጋት የሚፈልግ በመሆኑ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች የመምጣት፣ እዚያ የነበሩት የመቀጠልና መልሶ ሥራ የመጀመርጉዳይ በመቀሌ ብቻ ሳይሆን በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ ፓርኮች ተግዳሮት አጋጥሟል ያሉት ይታገሱ (ዶ/ር)፣ ‹‹ጦርነት እያለ ኢንቨስትመንት የሚታሰብ አለመሆኑንልናስብበት፤›› ይገባል ብለዋል፡፡ አገር ጥለው የወጡት ከመቀሌ ብቻ ሳይሆን ከኮምቦልቻ፣ ከባህር ዳርና ከደብረ ብርሃን ብዙ ባለሀብቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ከመቀሌ ወጥተው ወደ ሌላ አገር እንሄዳለን ከሚሉ ባለሀብቶች በተጨማሪ፣ ከሐዋሳ፣ ከኮምቦልቻ፣ ከሰመራ፣ ከባህር ዳር፣ ከደብረ ብርሃን፣ ከቦሌ ለሚ ፓርኮች ጭምርከአገር ለቀው መውጣታቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ችግሩ በአገር ላይ የመጣ ነው ብለዋል።

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ባቀረበው ጥያቄ፣ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች በዘጠኝ ወራት 37,035 ሠራተኞች መልቀቃቸውንከቀረበው ሪፖርት መረዳቱን ጠቅሶ ምክንያቱን ጠይቋል፡፡ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ካሚል በሰጡት ምላሽ በፓርኮቹ ውስጥ በሚቀጠሩ ሠራተኞች ልክ የሚለቁመኖራቸውን፣ አልፎ አልፎም ከተቀጠሩት በላይ እንደሚለቁ ተናግረዋል።