Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Axumezana
Senior Member
Posts: 17060
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

ኤርትራ ማለት የታሸገና ያልታጠነ ቤት ነው እንኳን ለፅምዶ ለጎረቤትነት አይበቃም!

Post by Axumezana » 09 May 2025, 20:14

ታሪክ እንደሚያስተምረን ሻእብያ በዜሮ ድምር ሽርክና ብቻ የሚያምን ድርጅት ሲሆን ከወያኔ ጋር የነበረው ግንኙነት ከታክቲካል ሽርክና በላይ አልፎ አያውቅም። ይኸም ሽርክና በተለይዬ ጊዜ በክህደትና ሽምቆ በኻላ በኩል በካራ እንደ መውጋት በሆነ መልኩ የተገለፀ ሲሆን ከ2020 እስከ 2022 በነበረው ትግራይን የማውደምና TPLFን የማጥፋት ጦርነት ግንባር ቀደም ተዋናይ ነበር። ጅብ በማያውቁት አገር ቁርበት አንጥፉልኝ አለ እንደሚባለው በቅርቡ የራሱንና የግብፅን ተልእኮ ለማስፈፀም ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሚሎክሰው ጦርነት ጠላት ለመቀነስ ቢቻለውም የትግራይን ጦር ከጎኑ ለማሰለፍ "ፅምዶ" በሚል መፈክር ትግራይን ለማማለልና ለማሳሳት እየሰራ ይገኛል። ትግራይ ግን ይኸን አስስታዊ የሆነ ተኩላ ሻእብያ ከአብይ መንግስት ጋር በመሆን ወጥመድ ውስጥ በማስገባት እስከ ወድያኛው መሸኘት ይኖርባታል።