Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Meleket
- Member
- Posts: 4349
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 08 May 2025, 11:10
ደራሲ ፍፁም ወልደማርያም፡"ያልተዘመረላቸው ቅጽ ሁለት" በሚል ጽሑፉ
ራስ አሞራው ውብነህ ትውልዳቸው ዳባት ጃኖራ ልዩ ስሙ መረባ አስተርእዮ ሜዳ በሚባል ስፍራ ነው።
ሲለን
አንዱ ጎበዝ ኣንጎራጓሪ ደግሞ ኣዘዞ ድማዛ ነው ሀገራቸው ብሎናል እንዲህ ተቀኝቶ
ሀገር እንደዋዛ ናፍቆት እንደዋዛ፤
የእነ አሞራው ሀገር የመይሳው ካሳ አዘዞ ድማዛ።
እኒህ ኣርበኛን በኣካል የሚያውቋቸው፡ ለአያት ኣርበኛው ውብነህ ተሰማ ሆነ ለቤተሰባቸው መልካም ተግባርን ያከናወኑት ኤርትራዊው አያት አርበኛ ተስፋሚካኤል ትኩእ ደግሞ
ግራዝማች ውብነህ ተሰማ የአድዋ አባገሪማ ተወላጅ
መሆናቸውን “ሀገሬ የህይወቴ ጥሪ” በሚለው መጸሓፋቸው ላይ ከትበውት አልፈዋል።
viewtopic.php?f=2&t=184726&start=20
ታዲያ የዳባት ጃኖራ ሰዎችና የአድዋ አባገሪማ ሰዎች በጠላትነት ተያይተው በአርማጭሆ ይገባኛል ጥያቄ ምክንያት እርስ በእርስ መጋደላቸው ኣያሳዝንምን? ጐበዝ መሬቱ ለሁላችሁም ይበቃችኋልና፡ በፍቅርና በስምምነት መንፈስ ተግባብታችሁ ለመኖር ጣሩ። ራስ ውብነህ ተሰማ ሆኑ ወንድማቸው ደጃዝማች ሐጎስ ተሰማ እንዲሁም ያጎታቸውም ልጅ ደጃዝማች ዋኘው ቢመጡና የጦብያ ልጆች በኣርማጭሆ ምክንያት እርስበእርስ መጋደላቸውን ቢያዩ ምን ይሉ ነበር?
ኣይጥዑምንዬ/2/
ደቂ ኤሩ ዘይብሉ ኣይጥዑምዬ።
Please wait, video is loading...
Meleket wrote: ↑07 Nov 2019, 03:12
.....
“በእነዚህ ደስታ የሌላቸው የዘመቻና የጦርነት፣ የአርበኝነት፣ የስደት ዓመታቶች ከባለቤቴና ከልጆቼ ጋር በሱዳን የእንግሊዝ መንግሥት ባለሥልጣኖች ተገድጄ ከካርቱም ገዳሪፍ እንደወጣሁ፣ የዛሬው ደጃዝማች ውብነህ ተሰማ ባለቤታቸው ወይዘሮ ዘነበሽና ልጆቻቸውን ገዳሪፍ ጥለው በአርማጭሆና በወገራ እስከ በለሳ ሲወናጨፉ፣ ባለቤታቸው ከነልጆቻቸው በባዶ ቤት ተዘግተው አገኘሁዋቸውና በብዙ አዘንሁ። ለግርማዊ ጃንሆይም ሎንዶን የአድዋ አባገሪማ ተወላጅ ግራዝማች ውብነህ ተሰማ ቤተሰዎች ብዙ በመቸገራቸው ምክንያት እንዲታደጕኣቸው ብዬ ብጽፍም ዕድል ሳያገኙ ስለቀሩ በብዙ ተጨነቅን፣ የፋሽር ተወላጅ ናዚር አብዱላሂ የተባለ የጣሊያን ጠላት የሆነ ያንድ ክፍለ ሀገር ገዥ ርዳታ ይሠጣቸው ጀመር።” ገጽ 151
“ጀግናው ግራዝማች ውብነህ ወንድማቸው አቶ ሐጐስ ተሰማ ግን በየቦታው ጣሊያንን አጥብቀው ወጉት፤ ለሊት ተቀን በመውጋታቸውም አስጨነቁት፤ እንኳን ወንድ ሴቶችም አርበኞች ሆኑ ሀገሬውም ራስ ውብነህ፣ ደጃዝማች ሐጐስ ተሰማ ብሎ ሾማቸው። እራስ ውብነህና ደጃዝማች ሐጎስ፣ ያጐታቸውም ልጅ ደፋሩ ደጃዝማች ዋኘው ሲቀሩም ፸፭ ዘመዶቻቸው በጦር ሜዳ አለቁ። ይህም ሁሉ ሲሆን ከባለቤታቸውና ከልጆቻቸው ይበልጥ ሀገራቸውን አፍቅረው በመጋደላቸው ታሪክ ጸሐፊ አቀብቆ ሊያስብበት በተገባው ነበር። ናለመኖሩም ለሐዲሱ ትውልድ የአሞራው ውብነህ ተሰማና ሐጐስ ተሰማ፣ የለስላሳው ሎጋ ዋኘው ሰውነት በጠላት ጥይት በመበሳሳቱ የመረረ ስቃይ መሰቃየቱንና ደጃዝማች ዋኘው ተብሎ በዚሁ የመረረ ስቃይ እየተሰቃየ በአዲስ አበባ ሆስፒታል መሞቱን ሳላስታውስ አላልፈውም። ደጃዝማች ሐጐስ ተሰማም ከብዙ ጥይቶች በጉሮሮአቸው ያለ ጥይት በበለጠ እህል አላስበላም፣ ውኃም አላስጠጣም ብሎዋቸው በሆስፒታል ዛሬም ወድቀው ይታያሉ።” ገጽ 151
....
ይህን ታሪክ ብርቅ የሚያደርገው አሁን ያለው አዛውንት ትውልድ ንፍጡ ባፍንጫው ይዝረከረክበት በነበረ ወቅት ለነጻነቱ ሲል ብርቱ ገድልን ባከናወነ ኤርትራዊ አባት አርበኛ የዓይን እማኝነት የተጻፈ በሳል ፖለቲካዊ ትንታኔ መሆኑ ነው። viewtopic.php?f=2&t=184726&

-
Axumezana
- Senior Member
- Posts: 16972
- Joined: 27 Jan 2020, 23:15
Post
by Axumezana » 08 May 2025, 17:03
መለከት it looks you are frozen in the past!
-
Meleket
- Member
- Posts: 4349
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 09 May 2025, 10:17
ወደ ኋላ መደ ጥንቱ መለስ ብለን የአርበኛው የአሞራዉን ታሪክ እየኮመኮምን ነው! ወዳጃችን ኣዅሱመጫላ የአገው ምድሩ የበላይ አሉላ ባህርይን እያዬንብህ ነው! ለማንኛዉም ይመችህ!
Meleket wrote: ↑10 Dec 2019, 08:16
....
“፫ኛ ግራዝማች ውብነህ ተሰማ የተባሉ በእውነተኛው ውብነታቸው በሀገር ፍቅር የተነደፉ አርበኛም ጓዛቸውን አስቀድመው በፊት ገዳሪፍ አስገብተው ራሳቸው ግን የአርማ ጭሆን ሰው ሁሉ አሳብረው ብርቱ የወንድ ሥራ ሠሩ፤ ጠላትን በብዙ ማረኩ። በማባረርም እጅግ አስቸገሩት። ያስቸግሩታልም። ስለዚህ ሞያቸው ለግራዝማች ውብነህ ተሰማ ደብዳቤ ቢጻፍላቸው እጅግ መልካም ነገር ነበር።” ገጽ 162
...
Meleket wrote: ↑25 Sep 2020, 04:51
.....
“በሌብነት የተወለደ የወንድ አሞት የሌለው የአገው ምድር በላይ አሉላ የያዘውን ሃብት ላይበላ፣ የማይበላውን ሀብት ፈለገ። ከዚህ ቀደም በሕዝብ ዘንድ ራስ ተብለው የሚዋጉት የጀግናው የአሞራው ውብነህ ተሰማ ባለቤት ወይዘሮ ዘነበችና ልጆቻቸው አርማጭሆ ለመሄድ ከገዳሪፍ በዶካ መንገድ ሲሄዱ ለጣሊያን መነሳታቸውን ነግሮት ተቃጠለ፤ ጉልበትና ድፍረትም ስላጣ ጣሊያን አስመሳይ በሆነ አታላይ ሐሰተኛነቱ ብዛት የአሞራው ውብነህ ተሰማን ባለቤትና ልጆች ማረክሁዋቸው እያለ እውነት አስመስሎ ስላስወራ እኔ እኒህን ሴት ከነልጆቻቸው በመላኬ በኃዘን ተከበብሁ፤ ሰዎቻችንም ሁሉ እውነት መሰላቸውና በያሉበት ተጨነቁ።” ገጽ 206
“ቀጥሎም ከካርቱም ጠፍተው የዛሬ ፊታውራሪዎች ካፒቴን ወርቁ አየለና የመቶ አለቃ ከበደ ይርዳው ፭ ራሳቸውን ሆነው በሌሊት እኔ ዘንድ ገዳሪፍ መጡ፤ ሽሽጌ ካሰነበትሁዋቸው በኋላ በስውር ወደ ዶካ ከማሳፈሬ በፊት “በላይ አሉላ የሚባል የጠላት መሣሪያ” መጥፎ ሰው አለና ዶካ ስትደርሱ እንዳትታዩት አደራችሁን ብዬ እየደጋገምሁ በብዙ አስጠነቀቅሁዋቸው። የኢትዮጵያኖች በሽታ የሆነው በላይ አሉላ ግን ዶካ እንደደረሱ አርበኞች መሆናቸውን ስላወቀ በጐን ሰው ልኮ እኔ መንገድ መርቼ አርማጭሆ አደርሳችኋለሁ ሲላቸው በ፴ብር ገዙትና ሲመራቸው በላይ ቀድሞ መተማ ገብቶ ለጠላት ነግሮ ቆዬ፤ መሪያቸውም ሰተት አድርጎ በመተማ ምሽግ ሥር አስቀምጦዋቸው በሽሽት አመለጣቸውና ተመለሰ፤ የበላይ አሉላ ሰው መሆኑን ተረዱት፤ በላይ አሉላ ባስላከውም ጦር ካሚዮን ድምጽ ነቅተው በወንዙ ጉድጓድ ሥር ተሸሽገው በታምራት ሳይታዩ ቀሩን የሚፈልጋቸው የጣሊያን ጦር እንዳለፋቸው፣ በብዙ ረኃብና የውሃ ጥም መከራን ከተቀበሉ በኋላ ወደ የሻለቃ መስፍን ጐጃም ደረሱ።” ገጽ 206
“ጣሊያንም እንደልማዱ እነ ካፒቴን ወርቁ አየለን በመንገድ ያዝሁዋቸው፣ ያለ ምሕረትም ቅጣታችውን ይቀበላሉ ብሎ ሲያወራ ሰው ሁሉ ትልቅ ኅዘን አዘነ። እኔ ግን የጣሊያንን ወሬ ባላምነውም በላይ አሉላ ተቀብሎ መሸኘቱ ስለተነገረኝ ቃሌን ባለመጠበቃቸውና እኔው ሸኝቼ በመላኬም በካፒቴን ወርቁ አየለ ተናደድሁ፤ ይህንንም ነገር ዛሬ በነሱ ፊት ሳነሳው እጅግ ይመረኛል።” ገጽ 206
“ክፉ ሥራ የሚሠራ ሰው ሁሉ ምንጊዜም ቢሆን የጁን አለማጣቱን በላይ አሉላን ራሱን በቃሉ አናግሬው፤ ክንዱን ቆርጦ ጥሎም ስቃይ አሰቃይቶ፣ የሰው ደም የገበየበትን ገንዘብ ሳይበላ፣ ይሁዳ ሆኖ ሞተ። እንደዚህን ያለውን መከራ ከመስማት እግዚአብሄር ይሰውረን። ጀግናው፣ ደፋር፣ ሃይማኖተኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰው አክባሪ፣ እግዚአብሄርን ፈሪ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ስለ ሀገሩ አፈር አጥብቆ ተጋዳይ፣ ጥንታዊ ባለታሪክ መሆኑ የተመሰከረለት ስለሆነ፣ ዛሬ ባንዳንድ የራሳቸውን የእለት ጥቅም ፈላጊዎችና ሐሰተኞች ሰዎች ምክንያት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያኖች ምንም ሊታሙ ወይም ሊሰደቡ ከቶ አይቻልም፤ ስለምን ይህ የዛሬው መንፈስ ከውጭ ሀገር ሰዎች የወረሱት ስለሆነ።” ገጽ 207
“በአርእስቱ የኔ የተስፋሚካኤልና የሻለቃ መስፍን መከራከር፣ የግርማዊ ጃንሆይ ከካርቱም በአየር ገዳሪፍ መምጣት፣ የተባለበት ስለዚህ የኢትዮጵያ ስደትና ትንሳኤ ነው።” ገጽ 207
በቀጣዩ ክፍል ምዕራፍ አርባ ሦስት “የተስፋ ሚካኤል ትኩእ ከነባለቤቱና ከነልጆቹ ተጠርቶ ካርቱም መውረድ፣ የመጀር ኖት በኔ ማዘን” የሚለውን ትረካቸውን እንጋራለን። ቸር እንሰንብት!
ይህን ታሪክ ብርቅ የሚያደርገው አሁን ያለው አዛውንት ትውልድ ንፍጡ ባፍንጫው ይዝረከረክበት በነበረ ወቅት ለነጻነቱ ሲል ብርቱ ገድልን ባከናወነ ኤርትራዊ አባት አርበኛ የዓይን እማኝነት የተጻፈ ቅንነትን የተላበሰ በሳል ፖለቲካዊ ትንታኔ መሆኑ ነው።
-
Meleket
- Member
- Posts: 4349
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » Yesterday, 05:08
የኤርትራዊው ኣርበኛ ተስፋሚካኤል ትኩእ ምስክርነት፡ ስለ የአርማጭሆውና የትግሬ ተወላጁ ኣርበኛ ራስ ውብነህ ተሰማ (ኣሞራው)! የእንግሊዝን ሰንደቅ ዓላማ ኣውርደው የቶብያን ሰንደቅ ዓላማ የሰቀሉ ጀግና ነበሩ ኣሉ ኣሉ ዳባቴው ኣሞራዉ ውብነህ!
Meleket wrote: ↑21 Oct 2020, 04:04
የቆፍጣናውን ኤርትራዊ አባት አርበኛ የተስፋሚካኤል ትኩእን መጠሐፍ 43ኛ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል። ለዛሬ ስለእንግሊዝና ጣሊያን የምስጢር ጓደኝነትና የእንግሊዝን ባንዴራ ስላቃጠሉት ስለ የአርማጭሆው ራስ ደጃዝማች ውብነህ ተሰማ በጨረፍታም ቢሆን የጠቆሙንን ሓቆች እንኮምኩም።
“ጀግና ሳለ በኩራቱ ብዛት ድል ማድረግ የተለየው ሂትለራዊ የጀርመን አዋቂና ብርቱ ወታደር የእንግሊዝ ከተማ ሎንዶንን በየቀኑ በአረዮፕላን ስለደበደባትና የእንግሊዝ የምስጢር ጓደኛውና አገልጋዩም የሆነው የጣሊያን ሙሶሊኒ ስለከዳው፡ የእንግሊዝ መንግሥት ያለ ውዴታው ፊቱን ወደ የኢትዮጵያ አርበኞች አዞረ።” ገጽ 208
“የኢትዮጵያ ብልህ ጥንታዊ ሕዝብ የእንግሊዝ መንግሥት ምን ኅሳብ እንዳለው እለቱን አወቀ፤ “ንጉሣችንን ይዘን በሰላም ሀገራችን እንግባና እንግሊዝ ሲገዛን እናያለን፤ በጀግናው አጼ ቴዎድሮስና በደፋሩ፣ በሰማእቱ በአጼ ዮሐንስ ላይ የሰራውን ግፍና ተንኮል አንዘነጋውም” ሲል የእንግሊዝ ስብከት አስታወሰው ከነከነውም።” ገጽ 208
“በዚሁም ጊዜ ሁሉ ይህን የእንግሊዝን ስብከት ያለስጋት፣ በድፍረት የተቃወሙት የትግሪው ተወላጅ የአረማጭሆው ራስ ደጃዝማች ውብነህ ተሰማና ከወንድማቸው ከደጃዝማች ሐጐስ ተሰማ ጋር ሆነው ጠባቸው እየከረረ ሄደ። በአርማጭሆ መንገድ ኢትዮጵያን እረዳለሁ ብሎ መጀር ባንቲክ የተባለ እንግሊዛዊ መስፍን ወጥቶ ባንዴራ ተከለ ማለትን ሲሰሙ አሞራው ውብነህ ተሰማ እሳት ለብሰው መጥተው፣ “ስለምን በሀገሬ ባንዴራህን ተከልክ” ብለው ጥይት አጉርሰው ባንዴራይቱን ከተተከለችበት አውርደው በቁጣ ቀደው ወረወሩለት። ልክ ኢጣሊያኖችን እንደሚገድሉዋቸው ዓይነት አድርገውም ለመግደል ተነሱ፤ ሰው ሁሉም ለምኖ የሰውዬውን መገደል አስቀረው።” ገጽ 208
“በዚሁም የደነቆረ ኦሪታዊ ያረጀ ያፈጀ የማታለል ኃሳቡ የእንግሊዝ መንግሥት ጣሊያንን አስወጥቶ ኢትዮጵያን ለመግዛት የነበረውን ምኞት ለማጽደቅ ከንቱ የሆነ ስብከቱን ሰበከ፤ ካንዳንድ የሸዋ ሰዎችና እነሱንም ከመሰሉ ጥቂት ሰዎች በቀር ተቀባይ ስለአላገኘም የተመቸውን ጊዜ ፈለገ። ሱዳንን ተገዥዎቹ በሆኑት ቁጥር በሌላቸው ህንዶች ወታደሮች አለበሳት። ወደ ለቀቀው ከሰላና ጋላባት፣ ወደ መተማና ወደ አሥመራ በከረን ግንባር አሰለፋቸው። በኋላም ከረን የህንዶች መቃብር ሆነች። መስከረም ፯ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. የአርማጭሆ ራስ ደጃዝማች ውብነህ ተሰማ የእንግሊዝን ባንዴራ የቀደዱበት መስፍን የሻለቃ ባንቲክ እቤቱታውን ለመንግሥቱ ስላቀረበ በግርማዊ ጃንሆይ ቃል ተጠርተው ገዳሪፍ መጡ። ከኔም ጋር ተገናኙና ስለዚሁ የቀደዱት የባንዴራ ነገር አንስተው ጃንሆይ በዚህ ይቆጡ ይመስለዎታል ወይ ሲሉ በሰፊው አጫወቱኝ።” ገጽ 209
“እኔም “አይዞዎት ኃሳብ አይግባዎት። የኔና የመንግሥቴ ፈቃድ ወይም ማዘዣ ሳይኖረው ደርሶ በፈቃዱ ጠላታችንን ወራሪውን ጣሊያን ይመስል የእንግሊዝን ባንዴራ የሻለቃ ባንቲክ በሀገሬ ላይ ስለተከለ አውርጄ ቀድጄዋለሁ፤ ጥፋቱም የራሱ ነው ብለው እውነቱን ገልጸው ለግርማዊነታቸው ከነገሩዋቸው ይደሰታሉ እንጂ ምንም እንደማይለዎት አውቃለሁና የሚገባዎትን መልካም ትልቅ ሥራ ስለሰሩ የሚያሰጋ ነገር ስለሌለበት አያስቡ” ብዬ በማበረታታት መከርሁዋቸው፤ እውነትም ጊዜው ረዳቸው እንጂ እንኳንስ ባንዴራው ተቀዶ እንዲያውም የእንግሊዝ መንግሥት ምሕረትና ይቅርታም ባላደረገላቸው ነበር። የአርማጭሆ ራስ ደጃዝማች ውብነህ ተሰማም በዚሁ ስለ ሀገራቸው በሠሩት ሥራ በመጠየቃቸው ተናደዱና ካርቱም እንደደረሱ ታመው ወደቁ፤ በቸርነቱም ዳኑ።” ገጽ 208
“የኢትዮጵያና የጣሊያንም ጦርነት ጥቅምት ወር ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ጀምሮ እየገነነ ሄደ። ጠላታችንም አስቀድሞ ተስፋ ቆረጠ። ኢትዮጵያዊ ወጣትም በቅጽበት ወደ ንጉሡ ዞረ። ጠላቱን አሳደደ፤ በብዙ በቀል ተበቀለው። ጥቅምት ፲፰ ቀን በሻምበል ወርቁ አየለ የሚታዘዘውን ጦር ለመሸኘት የሻለቃ መስፍን ስለሺና እኔ ዶካ ሄደን ሸኝተን ተመልሰን። እነዚህም ሰዎች በቋራ፣ በበላያና ወንበራ አድርገው የምስራች ለለቀምትና ጐጃም ለግንደበረትም ሕዝብ ለመናገር ለመላላክም በፍጥነት የተላኩ ሰዎች ነበሩ። የተላኩበትን ጉዳይ ፈጸሙ። እኛም ከዶካ ገዳሪፍ ስንመለስ ወዲያው ከሰላና መተማ ተያዙ። ምንም ችግርና መከራ የማይፈታው የኢትዮጵያ አርበኛም በፈቀደው መንገድ እንደልቡ ሆኖ መሄድና መመለስም ጀመረ። ጠላቱንም ዙሪያውን ከበበ።” ገጽ 210
በቀጣዩ ክፍል የዚሁን ምዕራፍ “የተስፋሚካኤል ትኩእ ከነባለቤቱና ከነልጆቹ ተጠርቶ ካርቱም መውረድ፡ የመጀር ኖት በኔ ማዘን” ” የሚለውን አንድ ንኡስ ክፍል በመቃኘት የአርበኛውንና የሜጀር ኖትን በነገር መጎሻሸም እናያለን።
ይህን ታሪክ ብርቅ የሚያደርገው አሁን ያለው አዛውንት ትውልድ ንፍጡ ባፍንጫው ይዝረከረክበት በነበረ ወቅት ለነጻነቱ ሲል ብርቱ ገድልን ባከናወነ ኤርትራዊ አባት አርበኛ የዓይን እማኝነት የተጻፈ ቅንነትን የተላበሰ በሳል ፖለቲካዊ ትንታኔ መሆኑ ነው።