Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10976
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ነገረ-ትግራይ: ከ'ጦርነት ይብቃ፣ ሰላም ይምጣ!' የልደቱ አያሌው መጣጥፍ የተወሰደ

Post by sarcasm » 06 May 2025, 15:25

ከ'ጦርነት ይብቃ፣ ሰላም ይምጣ!' የልደቱ አያሌው መጣጥፍ የተወሰደ (ሚያዚያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም)

3.1. ነገረ-ትግራይ

ሁልጊዜም ስለ ትግራይ ህዝብ ጉዳይ የሆነ ሀሳብ ለመስጠት ስሞክር “ድሮውንም አንተ የህወሀት ጠበቃ ነህ” የሚል ግልብና መቸም ቢሆን ማቆሚያ የሌለው ትችት ከአንዳንድ ወገኖች ሊቀርብብኝ እንደሚችል አስቀድሜ አውቃለሁ። ነገር ግን ከህዝብና ከሀገር ጥቅም አንፃር ፋይዳ አለው ብዬ እስካመንኩበት ድረስ በእኔ በኩል ዛሬም ሆነ ወደፊት ርዕሰ-ጉዳዩን ከማንሳት አልቆጠብም። ዛሬም በትግራይ ያለው ሁኔታ እየተላለቁ ከመፈራረሱ ስጋታችን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው በመሆኑ ሀሳብ ልሰጥበት ወድጃለሁ።

በኢትዮዽያ ፖለቲካ ነገሮችን ከግል ስሜትና አድልኦ /Bias/ ነፃ ሆነው በምክኒያት ለማየት የሚሞክሩ ፖለቲከኞች ቁጥር እጅግ አናሳ ነው። ጉዳዩ ከትግራይ ጋር የተያያዘ ሲሆን ደግሞ የእነዚህ የጥቂቶቹ ሚዛናዊነትም ብዙውን ጊዜ ፈተና ላይ ሲዎድቅ እታዘባለሁ። ይህ የሚሆንበትን ምክኒያት የምረዳው ብሆንም እዚህ ላይ በግልፅ ባልናገረው እመርጣለሁ። ትግራይንም ሆነ ህወሀትን በተመለከተ ያለን ከሚዛን የወደቀ አተያይ ግን በትናንቱ፣ በዛሬውም ሆነ በነገው የሀገራችን ፖለቲካ አንድ ዋና የችግር አንጓ እንደሆነ በእርግጠኛነት ስለምገነዘብ በእኔ በኩል ትኩረት ከምሰጣቸው አሳሳቢ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው።

ዛሬ ኢትዮዽያ ካሏት አስራ አንድ ክልሎች ውስጥ ለብልፅግና አገዛዝ ያልተንበረከከና ራሱን በራሱ ለማስተዳደር የሚሞክር ብቸኛ ክልላዊ መንግስት ያለው በትግራይ ነው። አገዛዙ ቀደም ሲል የሁለት ዓመቱን ጦርነት ለማካሄድ የወሰነው፣ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላም እስካሁን ድረስ በተለያዬ መንገድ እየሞከረ ያለው እንደ ሌሎቹ ክልሎች ሁሉ ትግራይንም በሙሉ ቁጥጥሩ ስር ለማዋል ነው።

አገዛዙ ትግራይን በጫማው ስር ሳያንበረክክ እንቅልፍ ተኝቶ ለማደር የቻለ አይመስልም። የብልፅግና አገዛዝ ይህንን ፍላጐቱን ለማስፈፀም ሲል ህወሀትን በሽብርተኝነት ፈርጆ፡ ህጋዊ እውቅናውን ሰርዞ፣ በአመራሮቹ ላይ የእስር ማዘዥ አውጥቶ፣ የራሱን አሻንጉሊት አስተዳደር ጭምር አቋቁሞ በህግ ማስከበር ስም ሁለንተናዊ ጦርነት በትግራይ ላይ ያካሄደ ቢሆንም እስካሁን ፍላጐቱን ማሳካት ግን አልቻለም።

አገዛዙ በዚያ የሁለት ዓመት ህዝብ ጨራሽ ጦርነት አንድ ሚሊየን በሚገመት ህዝብ ላይ ዘግናኝ ዕልቂት ከፈፀመ በኋላም ፕሪቶሪያ ላይ በተካሄደው ስምምነት ከህወሀት ጋር እንደገና ለመታረቅ፡ የሽብርተኛነት ፍረጃውን ለማንሳት፣ አሻንጉሊቱን መስተዳድር ለማፍረስና ህወሀትን በፓርቲነት እንደገና ለማዎቅ ተገደደ እንጅ እንደ ፍላጐቱ ህወሀትን ከምድረ-ገፅ አጥፍቶ ትግራይን በቁጥጥሩ ስር ለማዋል አልቻለም።

ከዚህ ተጨባጭ ኪሳራ ቅንጣት ትምህርት መውሰድ ያልቻለው አገዛዝ እንደገና ሌላ መቋጫ የሌለው ጦርነት በአማራ ህዝብ ላይ ከፈተ። ይህም አልበቃው ብሎ ዛሬም ተመሳሳይ ነገር ግን ውጤቱ የበለጠ አስቀያሚ የሚሆን ስህተት ለመስራት እየተዘጋጀ ይገኛል። አሁንም እንደገና የህወሀትን እውቅና ለመሰረዝና የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ማክተሙን በአደባባይ በማዎጅ ወደ አዲስ የጦርነት ትርምስ ሊያስገባን እየተንደረደረ ነው። ከሁለት ዓመት በፊት ተሞክሮ ያልተሳካው የጦርነት አማራጭ ዛሬ የብልፅግና አገዛዝ ከብዙ አጋሮቹ ተነጥሎ፣ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትና በፋኖ የተራዘመ ጦርነት ክንዱ የበለጠ ዝሎ፣ የኢኮኖሚ አቅሙ ተዳክሞ በሚገኝበት ሁኔታ የተለየና የተሻለ ውጤት ሊያመጣ ይችላል የሚል ዕምነት በበኩሌ የለኝም።

የዛሬው ህወሀትን የማጥፋት እርምጃ ከትናንቱ የተለየ የሚያደርገው ድርጊቱ እየተፈፀመ ያለው በአገዛዙ ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ የትግራይ ልሂቃን ትብብር ጭምር መሆኑ ነው። ከብልፅግና ሴራ በፀዳ አግባብ የትግራይ ህዝብ ዘላቂ ሰላም እንዲያገኝ ከመጣር ይልቅ የትግራይን ህዝብ ወክሎ የፕሪቶሪያውን ስምምነት የፈረመውን ህወሀትን በዚህ መጠን ለማዳከምና ለማጥፋት መረባረብ በትግራይ የቆመውን ውጊያ እንደገና ከማስቀጠል ባለፈ ሌላ ፋይዳና ውጤት ሊያመጣ አይችልም።

ህወሀት በውስጡ በተፈጠሩ ቅራኔዎች ምን አልባትም በታሪኩ ገጥሞት በማያውቅ መጠን አሁን ላይ የበለጠ የተዳከመ መሆኑ አከራካሪ አይመስለኝም። ይሁንና ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ በሀገሪቱ የመጣው የኃይል አሰላለፍ ለውጥ በህወሀት መከፋፈልና መዳከም ብቻ የሚገለፅ አይደለም። ህወሀት ካለፈው ጦርነት በብዙ ርቀት ብዙ ተዋጊ ኃይል በያዘበት፣ አንዳንድ የቀድሞ ጠላቶቹን ጭምር አጋር ማድረግ በቻለበት፣ ከሙሉ ከበባ ወጥቶ መግቢያ መውጫ ባገኘበት በአሁኑ ወቅት ህወሀትን እንደገና በጦርነት ለማጥፋት የሚደረግ ሙከራ የትም መድረስ የሚችል አይመስለኝም።

የትግራይ ልሂቃን ከቀድሞው በተሻለ ዛሬ ላይ ህወሀትን መተቸት፣ መቃዎምና መታገል መጀመራቸው በወቅታዊነቱ ላይ ጥያቄ ቢኖረኝም ምክኒያታዊና የሚገባ ነው ብዬ አምናለሁ። ምክኒያቱም የዛሬው ህወሀት በመጥፎ የታሪክ አጋጣሚ የሀምሳ ዓመቱን የህወሀት ጥፋቶችና ድክመቶች ሁሉ ሰብስቦ ለመሸከም የተገደደ “ዕድለ-ቢስ” አመራር ጭምር በመሆኑ በብዙ መዋቅራዊ ችግሮችና ድክመቶች የታጨቀ ድርጅት ነው። ነገር ግን ይህንን በበርካታ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች የተተበተበን፣ ዛሬም ቀላል የማይባል ማህበራዊ መሰረት ትግራይ ውስጥ ያለውን ድርጅት ታግሎ መለዎጥ የሚቻለው መቸ፣ እንዴትና እስከምን ድረስ ነው? የሚለውን ጥያቄ ከትግራይ ነባራዊ ሁኔታና ከአጠቃላዩ የሀገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ጋር አስተሳስሮ በስክነት ማየት ተገቢ ይሆናል።

በእኔ ዕይታ- ህወሀትን ታግሎ ለማጠናከር፣ ለመለወጥ ወይም ለማጥፋት ሲፈለግ የሚከተሉትን ቁም-ነገሮች ታሳቢ ማድረግ ጠቃሚ ይሆናል ብዬ አምናለሁ።

አንደኛ- የፕሪቶሪያው ስምምነት ውጊያውን እንጂ ጦርነቱን በዘላቂነት ያላስቆመ መሆኑንና ህወሀትም ሆነ ትግራይ ገና በጦርነት ስነ-ልቦና ውስጥ ያሉ መሆናቸውን፣

ሁለተኛ- የህወሀት ህልውና መሰረዝ ወይም መጥፋት የፕሪቶሪያው ስምምነት ማክተምን በይፋ የሚያረጋግጥና ለጊዜው ቁሞ የነበረውን ውጊያ እንደገና የማስቀጠል ውጤት የሚኖረው መሆኑን፣

ሶስተኛ- በህወሀትና በአብዛኛው የትግራይ ህዝብ መካከል ያለው የሀምሳ ዓመታት ግንኙነት ከፖለቲካ በላይ የሆነ ስነ-ልቦናዊና ስሜታዊ /Sentimental/ ቁርኝት ያለው በመሆኑ በቀላሉና በአጭር ጊዜ ሊለያይ እንደማይችል፣

አራተኛ- ሀገሪቱ ሰላሳ ሶስት ዓመት ሙሉ በስልጣን ላይ በቆየ፣ ሁሉንም ረግጦ የመግዛት ፍላጐት ባለው፣ የህወሀትን መጥፋት ቀዳሚ አጀንዳው ባደረገ አምባገነናዊና ጦረኛ አገዛዝ ስር ባለችበት በአሁኑ ወቅት ህወሀት በተለየ ሁኔታ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሆኖ ሊገኝ እንደማይችል፣

አምስተኛ- በትግራይ የተካሄደው ህዝብ ጨራሽ ጦርነት በዘላቂነት ባልተቋጨበት፣ ጦርነቱን ያካሄደው አገዛዝ አሁንም በስልጣን ላይ በሚገኝበት፣ የጦርነቱ እንደገና የመቀጠል ዕድል ሰፊ በሆነበት ሁኔታ የትግራይም ሆነ የህወሀት ቀዳሚ አጀንዳ ከማናችንም ፍላጐት በተለየ የማዕከላዊነትና የመዋጋት ብቃት መኖር እንጂ የዴሞክራሲያ እና የልማት መኖር ሊሆን እንደማይችል፣

ስድስተኛ- ህወሀት በአሁኑ ወቅት እየደረሰበት ያለውን ውስጣዊና ውጫዊ ጫናና ተፅዕኖ መቋቋም ተስኖት ቢፈርስና ቢጠፋ ትግራይን በብልፅግና ቁጥጥር ስር ከመውደቅም ሆነ ለሌላ የህልውና አደጋ ከመጋለጥ ሊታደግ የሚችል አዲስ የፖለቲካ ኃይል በቀላሉ ተጠናክሮ ሊዎጣ የማይችል መሆኑን፣

ሰባተኛ- ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ነባራዊ እውነታዎች ባልተለዎጡበት ሁኔታ አሁን ላይ ህወሀትን ማዳካምም ሆነ ማጥፋት የትግራይን ህዝብ ህልውና የበለጠ ለአደጋ የሚያጋልጥና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአገዛዙን የስልጣን የበላይነት የበለጠ የማፅናት ውጤት የሚያስከትል መሆኑን በውል መገንዘብ ያስፈልጋል።

በአጠቃላይ- የትግራይ ህዝብ አስተማማኝ የህልውና ዋስትና ባላገኘበትና ሌላ ዙር ጦርነት በአካባቢው እያንዣበበ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት ህወሀትን ከትግራይ ለመንቀል መሞከር ወንዝ እየተሻገሩ የጋለቡትን ፈረስ ለመቀየር እንደመሞከር የሚቆጠር አደገኛ መቀናጣት ነው። ከምንም ነገር በላይ ለትግራይ ህዝብ ዛሬ ላይ የሚያስፈልገው ውስጣዊ ልዩነትና ቅራኔን ሁሉ ለጊዜው ወደ ጐን አስቀምጦ የህልውናን ጉዳይ ቀዳሚና ዋና አጀንዳ አድርጐ ተባብሮ መቆም ነው።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ- ህወሀት በከፍተኛ የህልውና ፈተና ውስጥም እያለ ለአካታችነትና ለህዝብ አንድነት መስራት፣ የትግራይን ህዝብ አማራጭ የፖለቲካ ሀይል የማግኘት መብት ከልብ ማክበር፣ በትግራይ የተፈጠረውን የወቅቱን መከፋፈል ለመፍታት የሚያስችል ሀቀኛ ዕርቅ ለማስፈን መጣር፣ እስካሁን ይዞት የመጣው የፖለቲካ መስመር ለትግራይም ሆነ ለኢትዮዽያ በብዙ እጅ ያልጠቀመ መሆኑን በመገንዘብ ራሱን በሀቅ መገምገምና ለአዲሱ ትውልድ የሚመጥን አዲስ የፖለቲካ አቅጣጫ መያዝ፣ “የጠላቴ ጠላት ወዳጀ” በሚል የተሳሳተ እሳቤ የኢትዮዽያ ታሪካዊ ጠላቶች ተባባሪ ከመሆን መቆጠብና የሰላምን አጀንዳ ከፕሮፓጋንዳ ጥቅም ባለፈ ልባዊ ስትራቴጂክ ዓላማና ግብ አድርጐ መስራት፣ ከሁሉም በላይ አሁን ላይ ሊፈነዳ የተቃረበውን ሌላ አውዳሚ ጦርነት ለማስቀረት አቅምና ሁኔታ በፈቀደለት መጠን ከልብ መታገል ይኖርበታል።

ከዚህ ውጭ በአንድ ደካማ ፓርቲ ላይ ያለ ጊዜውና ያለ ተገቢ መጠን የሚደረግ ጫና የባሰ ቀውስና ድክመት እንጅ አወንታዊ ለውጥና ሰላም ሊያመጣ አይችልም። በተለይም አዲስ የሽምቅ ተዋጊ ፈጥሮ የትግራይን ችግር ለመፍታት መሞከር የስህተቶች ሁሉ ስህተት ይሆናል። ህወሀት ዋና መራሄ-መንግስት በነበረበት የሀያ ሰባት ዓመቱ ቆይታው ለዛሬው ውድቀት ምክኒያት የሆኑ አያሌ ጥፋቶች ሲፈፀሙና ሌላው ህዝብ ኢህአዴግን ሲታገል አብዛኛው የትግራይ ልሂቅ እያየ እንዳላየ አድፍጥ የተቀመጠ ወይም የኢህአዴግ ደጋፊ የነበረ ነው። ያ የትግራይ ልሂቅ ያኔ መራሄ-ህወሀት የሆነውን የኢህአዴግን ስህተቶች ለማረም ከሌላው ህዝብ ጋር በሞቆም ለመታገል ሞክሮ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ ህወሀትም ሆነ የትግራይ ህዝብ ከገጠማቸው አደጋ መዳን በቻሉ ነበር። ኢትዮዽያም እንደ ሀገር ለዚህ ዓይነቱ ጨፍጫፊ የመራሄ-ኦህዴድ የብልፅግና አገዛዝ ባልተጋለጠች ነበር።

የትግራይ ልሂቅ ያን የወደፊት አደጋን አስቀድሞ ለማስቀረት የሚያስችል የለውጥ አጋጣሚ በከንቱ ካሳለፈ በኋላ ዛሬ ዙሪያው-ገደል በሆነበት ህወሀት ላይ ይህንን ያህል መረባረብ ከህወሀት በላይ ትግራይን ለበለጠ አደጋ የሚያጋልጥ ዳግም ጥፋት እንዳያመጣ መጠንቀቅ አለበት። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ህወሀት ሲዳከም ትግራይ ለበለጠ አደጋ መጋለጧ፣ ትግርይም ስትዳከም ኢትዮዮዽያ ለበለጠ አደጋ መጋለጧ አይቀሬ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።

ህወሀት ዛሬ ላይ ለገጠመው ድክመትና ውድቀት ልሂቁ የራሱ የማይናቅ ድርሻ እንደነበረውም ሊረሳው አይገባም። በተለይም የትግራይ ህዝብ ጠንካራ አማራጭ ሀይል እንዳይኖረው በማድረግ ረገድ ልሂቁ የተጫዎተው ሚና ቀላል አይደለም። የትግራይ ልሂቅ ቢያንስ ዛሬ ላይ በርካታ የኦሮሞ ልሂቃን የመራሄ-ኦህዴዱን የብልፅግና አገዛዝ፣ በርካታ የአማራ ልሂቃን የአገዛዙን ዋና አጋር የሆነውን ብአዴንን በሚታገሉበት መጠን የትግራይ ልሂቃን የትናንቱን መራሄ-ህወሀት አገዛዝ ታግለውት ቢሆን ኖሮ የአሁኑ የትግራይም ሆነ የኢትዮዽያ ነባራዊ ሁኔታ በብዙ እጅ የተለየና የተሻለ በሆነ ነበር። ነገር ግን ህሊና በእብሪት ተሞልቶ ነበርና፣ ወደፊት የኃይል ሚዛኑ በኢህአዴግ ውስጥም ሆነ በኢትዮዽያ ሲለወጥ የሚፈጠረው አደጋ ከባድ እንደሚሆን ለማስጠንቀቅ የሞከርን ሰዎች በወቅቱ እንደ ሟርተኛ ከመታየት ባለፈ ሰሚ አላገኘንም።

በማዕከል የነበረውን ስልጣን ተነጥቆ ራሱ ዋና የጥቃት ሰለባ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ህወሀት በድንገት አቃፊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን መጠበቅም ግብዝነት ይመስለኛል። የቱንም ያህል ተቋማዊ ነፃነት እንዲኖር ብንፈልግ የኢትዮዽያ መንግስት፣ የብልፅግና ፓርቲና መከላከያ ሰራዊት አንድም-ሶስትም ሳይሆን አንድና-አንድ ሆኖ በህዝብ ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀመ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ህወሀትና የትግራይ መከላከያ ኃይልም /TDF/ ሆነ ህወሀትና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተለያዩ ሶስት አካላት ሆነው ለማየት መሞከር ከምኞት ያለፈ ትርጉም የሚኖረው አይመስለኝም። የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባር ላይ ባልዋለበት ሁኔታም ይህንን ለማድረግ የሚያስችል የህግና የፖለቲካ አመክንዮ ሊኖር የሚችል አይመስለኝም።

ከሁሉም በላይ ትክክለኛውን ጊዜና ሁናቴ ያልዋጀ ለውጥ ውጤቱ ጠቃሚ አይሆንም። ለምሳሌ የዚህ መጣጥፍ ፀሀፊ ሀገሬ ኢትዮዽያ የባህር-በር ባለቤት ብትሆን ከማንም ያላነሰ ደስተኛ በሆንኩ ነበር። ከዚህ ፍላጐቴ በተፃራሪ የወቅቱን የጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ የባህር-በር ጥያቄ የምቃዎመው ግን ጥያቄው የተነሳበት የጀርባ ዓላማ፣ ጊዜና ሁናቴ እንኳንስ የታሰበውን ጥቅም የሚያስገኝ ሀገሪቱን የበለጠ ዋጋ የሚያስከፍል ፈርጀ-ብዙ መዘዝ ይዞ እንደሚመጣ ስለምገነዘብ ነው።

2010 ዓ.ም ላይ “ቲም ለማ” ወደ ስልጣን መጣ ሲባል ለውጡ ውጤታማ እንዲሆን ከተፈለገ ኢህአዴግን “አታፍርሱት” ብየ እንደተከራከርኩት ሁሉ፣ ዛሬም እድሜ ልኬን የታገልሁትን ህወሀትን “አታፍርሱት” የምለው በተመሳሳይ መርህ ላይ በመቆም ነው እንጂ በተለየ ምክኒያት አይደለም። የኢትዮዽያዊነት ፖለቲካ አራማጅ እንደመሆኔ መጠን በአንድ ጉዳይ ላይ አቋም የምይዘው ከግሌ ወይም ከአንድ ቡድን ጊዜያዊ ስሜትና ፍላጐት በመነሳት ሳይሆን የሀገሪቱንና የህዝቧን የመካከለኛና የሩቅ ዘመን ዕጣ-ፈንታ ግምት ውስጥ አስገብቸ ነው። ስለሆነም፣ የትግራይ ልሂቃንም ሆናችሁ የህወሀትን መጥፋት የምትናፍቁ ሌሎች የሀገሪቱ ልሂቃን የወቅቱን የትግራይ ጉዳይ በስሜትና በጥላቻ ሳይሆን ልብ ገዝታችሁ በስክነት ብታጤኑት ተገቢ ይመስለኛል።

Meleket
Member
Posts: 4479
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ነገረ-ትግራይ: ከ'ጦርነት ይብቃ፣ ሰላም ይምጣ!' የልደቱ አያሌው መጣጥፍ የተወሰደ

Post by Meleket » 07 May 2025, 08:34

ኣቶ ልደቱ በእርግጠኝነት ለመናገር፡ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ሰላማዉያን ፖለቲከኞች መካከል በቀዳሚነት ከሚመደቡት ጋር ቀዳሚ ሆነው ተገኝተዋል፡ በኛ በኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ነጻ እይታ።

እስቲ እኛም እሳቸው ካነሷቸው ነጥቦች ኣንዳንዶቹን እናተኩርባቸው በሰማያዊ ኣድምቀንም፡ የኛን እይታም በቅንፍም ውስጥ ኣስገብተን ኣስምረንበትም እንለፍ።

sarcasm wrote:
06 May 2025, 15:25
ከ'ጦርነት ይብቃ፣ ሰላም ይምጣ!' የልደቱ አያሌው መጣጥፍ የተወሰደ (ሚያዚያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም)

3.1. ነገረ-ትግራይ

.......
በኢትዮዽያ ፖለቲካ ነገሮችን ከግል ስሜትና አድልኦ /Bias/ ነፃ ሆነው በምክኒያት ለማየት የሚሞክሩ ፖለቲከኞች ቁጥር እጅግ አናሳ ነው። ጉዳዩ ከትግራይ ጋር የተያያዘ ሲሆን ደግሞ የእነዚህ የጥቂቶቹ ሚዛናዊነትም ብዙውን ጊዜ ፈተና ላይ ሲዎድቅ እታዘባለሁ። ይህ የሚሆንበትን ምክኒያት የምረዳው ብሆንም እዚህ ላይ በግልፅ ባልናገረው እመርጣለሁ። [ኣካፋን ኣካፋ ለማለት ምነው ኣልመረጡም? ምን ተገኜ!][ኣቦ ሙሉ ጤናና ረዢም ዕድሜ ተመኝተንለዎታል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።]

ዛሬ ኢትዮዽያ ካሏት አስራ አንድ ክልሎች ውስጥ ለብልፅግና አገዛዝ ያልተንበረከከና ራሱን በራሱ ለማስተዳደር የሚሞክር ብቸኛ ክልላዊ መንግስት ያለው በትግራይ ነው። አገዛዙ ቀደም ሲል የሁለት ዓመቱን ጦርነት ለማካሄድ የወሰነው፣ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላም እስካሁን ድረስ በተለያዬ መንገድ እየሞከረ ያለው እንደ ሌሎቹ ክልሎች ሁሉ ትግራይንም በሙሉ ቁጥጥሩ ስር ለማዋል ነው።

አገዛዙ ትግራይን በጫማው ስር ሳያንበረክክ እንቅልፍ ተኝቶ ለማደር የቻለ አይመስልም። የብልፅግና አገዛዝ ይህንን ፍላጐቱን ለማስፈፀም ሲል ህወሀትን በሽብርተኝነት ፈርጆ፡ ህጋዊ እውቅናውን ሰርዞ፣ በአመራሮቹ ላይ የእስር ማዘዥ አውጥቶ፣ የራሱን አሻንጉሊት አስተዳደር ጭምር አቋቁሞ በህግ ማስከበር ስም ሁለንተናዊ ጦርነት በትግራይ ላይ ያካሄደ ቢሆንም እስካሁን ፍላጐቱን ማሳካት ግን አልቻለም።

አገዛዙ በዚያ የሁለት ዓመት ህዝብ ጨራሽ ጦርነት አንድ ሚሊየን በሚገመት ህዝብ ላይ ዘግናኝ ዕልቂት ከፈፀመ በኋላም ፕሪቶሪያ ላይ በተካሄደው ስምምነት ከህወሀት ጋር እንደገና ለመታረቅ፡ የሽብርተኛነት ፍረጃውን ለማንሳት፣ አሻንጉሊቱን መስተዳድር ለማፍረስና ህወሀትን በፓርቲነት እንደገና ለማዎቅ ተገደደ እንጅ እንደ ፍላጐቱ ህወሀትን ከምድረ-ገፅ አጥፍቶ ትግራይን በቁጥጥሩ ስር ለማዋል አልቻለም።

ከዚህ ተጨባጭ ኪሳራ ቅንጣት ትምህርት መውሰድ ያልቻለው አገዛዝ እንደገና ሌላ መቋጫ የሌለው ጦርነት በአማራ ህዝብ ላይ ከፈተ። ይህም አልበቃው ብሎ ዛሬም ተመሳሳይ ነገር ግን ውጤቱ የበለጠ አስቀያሚ የሚሆን ስህተት ለመስራት እየተዘጋጀ ይገኛል። አሁንም እንደገና የህወሀትን እውቅና ለመሰረዝና የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ማክተሙን በአደባባይ በማዎጅ ወደ አዲስ የጦርነት ትርምስ ሊያስገባን እየተንደረደረ ነው። ከሁለት ዓመት በፊት ተሞክሮ ያልተሳካው የጦርነት አማራጭ ዛሬ የብልፅግና አገዛዝ ከብዙ አጋሮቹ ተነጥሎ፣ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትና በፋኖ የተራዘመ ጦርነት ክንዱ የበለጠ ዝሎ፣ የኢኮኖሚ አቅሙ ተዳክሞ በሚገኝበት ሁኔታ የተለየና የተሻለ ውጤት ሊያመጣ ይችላል የሚል ዕምነት በበኩሌ የለኝም።

የዛሬው ህወሀትን የማጥፋት እርምጃ ከትናንቱ የተለየ የሚያደርገው ድርጊቱ እየተፈፀመ ያለው በአገዛዙ ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ የትግራይ ልሂቃን ትብብር ጭምር መሆኑ ነው። ከብልፅግና ሴራ በፀዳ አግባብ የትግራይ ህዝብ ዘላቂ ሰላም እንዲያገኝ ከመጣር ይልቅ የትግራይን ህዝብ ወክሎ የፕሪቶሪያውን ስምምነት የፈረመውን ህወሀትን በዚህ መጠን ለማዳከምና ለማጥፋት መረባረብ በትግራይ የቆመውን ውጊያ እንደገና ከማስቀጠል ባለፈ ሌላ ፋይዳና ውጤት ሊያመጣ አይችልም። [ኣቶ ልደቱ እነዚያ ‘አንዳንድ የትግራይ ልሂቃን’ ብለው ካሏቸው ኣካላት ጋር ለመነጋገር ሞክረዋልን። የነዚያ ‘ኣንዳንድ የትግራይ ልሂቃን’ ኣመለካከት ምን እንደሆነ ከሊሂቃኖቹ ለመስማት ችለዋልን፧ እስቲ ከጌታቸው ጋር ፊት ለፊት ቆመው ይህን አመለካከትዎን ይግለጹለትና እሱም የሚለውን እንስማ። መቼም በጨዋ ደንብ ሁለታችሁም ለመነጋገር አትሰንፉም። መድሕን ገብረስላሰ ወይም ቴድሮስ ጸጋይ እስቲ እነዚህን ልሂቃን ፊተፊት አድርጋችሁ ኣመለካከታቸውን ለህዝብ ይገልጹ ዘንድ ለማነጋገር ሞክሩ፡ ከናንተ ዬተሻለ ጎበዝ ነጻ ጋዜጠኛ ለማግኘት ስለማይቻል ነው። አደራውን የጣልንባችሁ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር’።]

ህወሀት በውስጡ በተፈጠሩ ቅራኔዎች ምን አልባትም በታሪኩ ገጥሞት በማያውቅ መጠን አሁን ላይ የበለጠ የተዳከመ መሆኑ አከራካሪ አይመስለኝም። ይሁንና ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ በሀገሪቱ የመጣው የኃይል አሰላለፍ ለውጥ በህወሀት መከፋፈልና መዳከም ብቻ የሚገለፅ አይደለም። ህወሀት ካለፈው ጦርነት በብዙ ርቀት ብዙ ተዋጊ ኃይል በያዘበት፣ አንዳንድ የቀድሞ ጠላቶቹን ጭምር አጋር ማድረግ በቻለበት፣ ከሙሉ ከበባ ወጥቶ መግቢያ መውጫ ባገኘበት በአሁኑ ወቅት ህወሀትን እንደገና በጦርነት ለማጥፋት የሚደረግ ሙከራ የትም መድረስ የሚችል አይመስለኝም።

የትግራይ ልሂቃን ከቀድሞው በተሻለ ዛሬ ላይ ህወሀትን መተቸት፣ መቃዎምና መታገል መጀመራቸው በወቅታዊነቱ ላይ ጥያቄ ቢኖረኝም ምክኒያታዊና የሚገባ ነው ብዬ አምናለሁ። ምክኒያቱም የዛሬው ህወሀት በመጥፎ የታሪክ አጋጣሚ የሀምሳ ዓመቱን የህወሀት ጥፋቶችና ድክመቶች ሁሉ ሰብስቦ ለመሸከም የተገደደ “ዕድለ-ቢስ” አመራር ጭምር በመሆኑ በብዙ መዋቅራዊ ችግሮችና ድክመቶች የታጨቀ ድርጅት ነው። ነገር ግን ይህንን በበርካታ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች የተተበተበን፣ ዛሬም ቀላል የማይባል ማህበራዊ መሰረት ትግራይ ውስጥ ያለውን ድርጅት ታግሎ መለዎጥ የሚቻለው መቸ፣ እንዴትና እስከምን ድረስ ነው? የሚለውን ጥያቄ ከትግራይ ነባራዊ ሁኔታና ከአጠቃላዩ የሀገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ጋር አስተሳስሮ በስክነት ማየት ተገቢ ይሆናል።

በእኔ ዕይታ- ህወሀትን ታግሎ ለማጠናከር፣ ለመለወጥ ወይም ለማጥፋት ሲፈለግ የሚከተሉትን ቁም-ነገሮች ታሳቢ ማድረግ ጠቃሚ ይሆናል ብዬ አምናለሁ።

አንደኛ- የፕሪቶሪያው ስምምነት ውጊያውን እንጂ ጦርነቱን በዘላቂነት ያላስቆመ መሆኑንና ህወሀትም ሆነ ትግራይ ገና በጦርነት ስነ-ልቦና ውስጥ ያሉ መሆናቸውን፣

ሁለተኛ- የህወሀት ህልውና መሰረዝ ወይም መጥፋት የፕሪቶሪያው ስምምነት ማክተምን በይፋ የሚያረጋግጥና ለጊዜው ቁሞ የነበረውን ውጊያ እንደገና የማስቀጠል ውጤት የሚኖረው መሆኑን፣

ሶስተኛ- በህወሀትና በአብዛኛው የትግራይ ህዝብ መካከል ያለው የሀምሳ ዓመታት ግንኙነት ከፖለቲካ በላይ የሆነ ስነ-ልቦናዊና ስሜታዊ /Sentimental/ ቁርኝት ያለው በመሆኑ በቀላሉና በአጭር ጊዜ ሊለያይ እንደማይችል፣

አራተኛ- ሀገሪቱ ሰላሳ ሶስት ዓመት ሙሉ በስልጣን ላይ በቆየ፣ ሁሉንም ረግጦ የመግዛት ፍላጐት ባለው፣ የህወሀትን መጥፋት ቀዳሚ አጀንዳው ባደረገ አምባገነናዊና ጦረኛ አገዛዝ ስር ባለችበት በአሁኑ ወቅት ህወሀት በተለየ ሁኔታ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሆኖ ሊገኝ እንደማይችል፣

አምስተኛ- በትግራይ የተካሄደው ህዝብ ጨራሽ ጦርነት በዘላቂነት ባልተቋጨበት፣ ጦርነቱን ያካሄደው አገዛዝ አሁንም በስልጣን ላይ በሚገኝበት፣ የጦርነቱ እንደገና የመቀጠል ዕድል ሰፊ በሆነበት ሁኔታ የትግራይም ሆነ የህወሀት ቀዳሚ አጀንዳ ከማናችንም ፍላጐት በተለየ የማዕከላዊነትና የመዋጋት ብቃት መኖር እንጂ የዴሞክራሲያ እና የልማት መኖር ሊሆን እንደማይችል፣

ስድስተኛ- ህወሀት በአሁኑ ወቅት እየደረሰበት ያለውን ውስጣዊና ውጫዊ ጫናና ተፅዕኖ መቋቋም ተስኖት ቢፈርስና ቢጠፋ ትግራይን በብልፅግና ቁጥጥር ስር ከመውደቅም ሆነ ለሌላ የህልውና አደጋ ከመጋለጥ ሊታደግ የሚችል አዲስ የፖለቲካ ኃይል በቀላሉ ተጠናክሮ ሊዎጣ የማይችል መሆኑን፣

ሰባተኛ- ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ነባራዊ እውነታዎች ባልተለዎጡበት ሁኔታ አሁን ላይ ህወሀትን ማዳካምም ሆነ ማጥፋት የትግራይን ህዝብ ህልውና የበለጠ ለአደጋ የሚያጋልጥና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአገዛዙን የስልጣን የበላይነት የበለጠ የማፅናት ውጤት የሚያስከትል መሆኑን በውል መገንዘብ ያስፈልጋል።

በአጠቃላይ- የትግራይ ህዝብ አስተማማኝ የህልውና ዋስትና ባላገኘበትና ሌላ ዙር ጦርነት በአካባቢው እያንዣበበ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት ህወሀትን ከትግራይ ለመንቀል መሞከር ወንዝ እየተሻገሩ የጋለቡትን ፈረስ ለመቀየር እንደመሞከር የሚቆጠር አደገኛ መቀናጣት ነው። ከምንም ነገር በላይ ለትግራይ ህዝብ ዛሬ ላይ የሚያስፈልገው ውስጣዊ ልዩነትና ቅራኔን ሁሉ ለጊዜው ወደ ጐን አስቀምጦ የህልውናን ጉዳይ ቀዳሚና ዋና አጀንዳ አድርጐ ተባብሮ መቆም ነው።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ- ህወሀት በከፍተኛ የህልውና ፈተና ውስጥም እያለ ለአካታችነትና ለህዝብ አንድነት መስራት፣ የትግራይን ህዝብ አማራጭ የፖለቲካ ሀይል የማግኘት መብት ከልብ ማክበር፣ በትግራይ የተፈጠረውን የወቅቱን መከፋፈል ለመፍታት የሚያስችል ሀቀኛ ዕርቅ ለማስፈን መጣር፣ እስካሁን ይዞት የመጣው የፖለቲካ መስመር ለትግራይም ሆነ ለኢትዮዽያ በብዙ እጅ ያልጠቀመ መሆኑን በመገንዘብ ራሱን በሀቅ መገምገምና ለአዲሱ ትውልድ የሚመጥን አዲስ የፖለቲካ አቅጣጫ መያዝ፣ “የጠላቴ ጠላት ወዳጀ” በሚል የተሳሳተ እሳቤ የኢትዮዽያ ታሪካዊ ጠላቶች ተባባሪ ከመሆን መቆጠብና የሰላምን አጀንዳ ከፕሮፓጋንዳ ጥቅም ባለፈ ልባዊ ስትራቴጂክ ዓላማና ግብ አድርጐ መስራት፣ ከሁሉም በላይ አሁን ላይ ሊፈነዳ የተቃረበውን ሌላ አውዳሚ ጦርነት ለማስቀረት አቅምና ሁኔታ በፈቀደለት መጠን ከልብ መታገል ይኖርበታል። [የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የተባሉት፡ ሕወሓትም “የጠላቴ ጠላት” በሚል ፈሊጥ እንዳይወዳጃቸው ኣበክረው ያሳሰቡት የትኞቹን “ጠላቶች ነው” ለምን በስማቸው ኣልጠሯቸዉም?]

ከዚህ ውጭ በአንድ ደካማ ፓርቲ ላይ ያለ ጊዜውና ያለ ተገቢ መጠን የሚደረግ ጫና የባሰ ቀውስና ድክመት እንጅ አወንታዊ ለውጥና ሰላም ሊያመጣ አይችልም። በተለይም አዲስ የሽምቅ ተዋጊ ፈጥሮ የትግራይን ችግር ለመፍታት መሞከር የስህተቶች ሁሉ ስህተት ይሆናል። ህወሀት ዋና መራሄ-መንግስት በነበረበት የሀያ ሰባት ዓመቱ ቆይታው ለዛሬው ውድቀት ምክኒያት የሆኑ አያሌ ጥፋቶች ሲፈፀሙና ሌላው ህዝብ ኢህአዴግን ሲታገል አብዛኛው የትግራይ ልሂቅ እያየ እንዳላየ አድፍጥ የተቀመጠ ወይም የኢህአዴግ ደጋፊ የነበረ ነው። ያ የትግራይ ልሂቅ ያኔ መራሄ-ህወሀት የሆነውን የኢህአዴግን ስህተቶች ለማረም ከሌላው ህዝብ ጋር በሞቆም ለመታገል ሞክሮ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ ህወሀትም ሆነ የትግራይ ህዝብ ከገጠማቸው አደጋ መዳን በቻሉ ነበር። ኢትዮዽያም እንደ ሀገር ለዚህ ዓይነቱ ጨፍጫፊ የመራሄ-ኦህዴድ የብልፅግና አገዛዝ ባልተጋለጠች ነበር።

የትግራይ ልሂቅ ያን የወደፊት አደጋን አስቀድሞ ለማስቀረት የሚያስችል የለውጥ አጋጣሚ በከንቱ ካሳለፈ በኋላ ዛሬ ዙሪያው-ገደል በሆነበት ህወሀት ላይ ይህንን ያህል መረባረብ ከህወሀት በላይ ትግራይን ለበለጠ አደጋ የሚያጋልጥ ዳግም ጥፋት እንዳያመጣ መጠንቀቅ አለበት። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ህወሀት ሲዳከም ትግራይ ለበለጠ አደጋ መጋለጧ፣ ትግርይም ስትዳከም ኢትዮዮዽያ ለበለጠ አደጋ መጋለጧ አይቀሬ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።

ህወሀት ዛሬ ላይ ለገጠመው ድክመትና ውድቀት ልሂቁ የራሱ የማይናቅ ድርሻ እንደነበረውም ሊረሳው አይገባም። በተለይም የትግራይ ህዝብ ጠንካራ አማራጭ ሀይል እንዳይኖረው በማድረግ ረገድ ልሂቁ የተጫዎተው ሚና ቀላል አይደለም። የትግራይ ልሂቅ ቢያንስ ዛሬ ላይ በርካታ የኦሮሞ ልሂቃን የመራሄ-ኦህዴዱን የብልፅግና አገዛዝ፣ በርካታ የአማራ ልሂቃን የአገዛዙን ዋና አጋር የሆነውን ብአዴንን በሚታገሉበት መጠን የትግራይ ልሂቃን የትናንቱን መራሄ-ህወሀት አገዛዝ ታግለውት ቢሆን ኖሮ የአሁኑ የትግራይም ሆነ የኢትዮዽያ ነባራዊ ሁኔታ በብዙ እጅ የተለየና የተሻለ በሆነ ነበር። ነገር ግን ህሊና በእብሪት ተሞልቶ ነበርና፣ ወደፊት የኃይል ሚዛኑ በኢህአዴግ ውስጥም ሆነ በኢትዮዽያ ሲለወጥ የሚፈጠረው አደጋ ከባድ እንደሚሆን ለማስጠንቀቅ የሞከርን ሰዎች በወቅቱ እንደ ሟርተኛ ከመታየት ባለፈ ሰሚ አላገኘንም።

በማዕከል የነበረውን ስልጣን ተነጥቆ ራሱ ዋና የጥቃት ሰለባ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ህወሀት በድንገት አቃፊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን መጠበቅም ግብዝነት ይመስለኛል። የቱንም ያህል ተቋማዊ ነፃነት እንዲኖር ብንፈልግ የኢትዮዽያ መንግስት፣ የብልፅግና ፓርቲና መከላከያ ሰራዊት አንድም-ሶስትም ሳይሆን አንድና-አንድ ሆኖ በህዝብ ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀመ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ህወሀትና የትግራይ መከላከያ ኃይልም /TDF/ ሆነ ህወሀትና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተለያዩ ሶስት አካላት ሆነው ለማየት መሞከር ከምኞት ያለፈ ትርጉም የሚኖረው አይመስለኝም። የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባር ላይ ባልዋለበት ሁኔታም ይህንን ለማድረግ የሚያስችል የህግና የፖለቲካ አመክንዮ ሊኖር የሚችል አይመስለኝም።

ከሁሉም በላይ ትክክለኛውን ጊዜና ሁናቴ ያልዋጀ ለውጥ ውጤቱ ጠቃሚ አይሆንም። ለምሳሌ የዚህ መጣጥፍ ፀሀፊ ሀገሬ ኢትዮዽያ የባህር-በር ባለቤት ብትሆን ከማንም ያላነሰ ደስተኛ በሆንኩ ነበር። ከዚህ ፍላጐቴ በተፃራሪ የወቅቱን የጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ የባህር-በር ጥያቄ የምቃዎመው ግን ጥያቄው የተነሳበት የጀርባ ዓላማ፣ ጊዜና ሁናቴ እንኳንስ የታሰበውን ጥቅም የሚያስገኝ ሀገሪቱን የበለጠ ዋጋ የሚያስከፍል ፈርጀ-ብዙ መዘዝ ይዞ እንደሚመጣ ስለምገነዘብ ነው። [ኣቦ ሙሉ ጤናና ረዢም ዕድሜ ተመኝተንለዎታል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።]

2010 ዓ.ም ላይ “ቲም ለማ” ወደ ስልጣን መጣ ሲባል ለውጡ ውጤታማ እንዲሆን ከተፈለገ ኢህአዴግን “አታፍርሱት” ብየ እንደተከራከርኩት ሁሉ፣ ዛሬም እድሜ ልኬን የታገልሁትን ህወሀትን “አታፍርሱት” የምለው በተመሳሳይ መርህ ላይ በመቆም ነው እንጂ በተለየ ምክኒያት አይደለም። የኢትዮዽያዊነት ፖለቲካ አራማጅ እንደመሆኔ መጠን በአንድ ጉዳይ ላይ አቋም የምይዘው ከግሌ ወይም ከአንድ ቡድን ጊዜያዊ ስሜትና ፍላጐት በመነሳት ሳይሆን የሀገሪቱንና የህዝቧን የመካከለኛና የሩቅ ዘመን ዕጣ-ፈንታ ግምት ውስጥ አስገብቸ ነው። ስለሆነም፣ የትግራይ ልሂቃንም ሆናችሁ የህወሀትን መጥፋት የምትናፍቁ ሌሎች የሀገሪቱ ልሂቃን የወቅቱን የትግራይ ጉዳይ በስሜትና በጥላቻ ሳይሆን ልብ ገዝታችሁ በስክነት ብታጤኑት ተገቢ ይመስለኛል።

ደግመን ደጋግመን ለኢትዮጵያዊው ሰላማዊ ፖለቲከኛ ለአቶ ልደቱ ኣያሌው ሙሉ ጤናና ረዢም እድሜ ተመኝተንላቸዋል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

Post Reply