
የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል አንድ አካባቢን "መቆጣጠራቸው" እና የወረዳ አስተዳዳሪን ማቁሰላቸው ተገለጸ
https://www.bbc.com/amharic/articles/c4g2q626g84o

ከ 9 ሰአት በፊት
የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ላሬ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ "ቢልኩን" የተባለ አካባቢን "መቆጣጠራቸውን" እና የላሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪን ማቁሰላቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ተናገሩ። ታጣቂዎች ተቆጣጥረውታል የተባለው አካባቢ ነዋሪዎች ወደ ሌላ ከተማ እንደሸሹም ተገልጿል።
ኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳንን ከምትጎራበታቸው ክልሎች አንዱ በሆነው ጋምቤላ ታጣቂዎች ጥቃት መፈጸም የጀመሩት ከትናንት በስቲያ ከረቡዕ ሚያዝያ 22/2017 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሆነ አንድ የላሬ ወረዳ ኃላፊ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
እንደ ኃላፊው ገለጻ "የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው የገቡት" ከደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር ግጭት ውስጥ ያሉት የሱዳን ሕዝቦች ነጻነት እንቅስቃሴ/ተቃዋሚ (Sudan People's Liberation Movement In Opposition) ታጣቂዎች ናቸው።
ታጣቂዎቹ የገቡት የኑዌር ብሔረሰብ ዞን ላሬ ወረዳ ስር በምትገኘው የድንበር አካባቢዋ ፓጋግ ቀበሌ እንደሆነ ምንጩ ገልጸዋል። ከሀገሪቱ መንግሥት ጋር ግጭት ውስጥ ያሉት ታጣቂዎች ድንበሩን አቋርጠው የገቡት "ተኩስ ሲከፈትባቸው ሸሽተው" እንደሆነም ተናግረዋል።
ብለዋል።[ታጣቂዎቹ] የራሳቸውን ድንበር ዘለው ወደ እኛ ድንበር ነው የገቡት። እስከ ትናንት [ሐሙስ] ድረስ ያገኘነው መረጃ በእኛ ድንበር [ውስጥ] ነው ያሉት። የኢትዮጵያ ባንዲራ ጭምር ነው የወሰዱት
እንደሆነ መረጃ እንዳላቸውም አክለዋል።ታጣቂዎቹ እስከ ትናንት ድረስ እየገቡ
ኃላፊው፤ ታጣቂዎቹ ድንበሩን አቋርጠው ከገቡ በኋላ "በነዋሪዎች ላይ ተኩስ" መክፈታቸውን እና "ቤቶችን ማቃጠላቸውን" ተናግረዋል።
የታጣቂዎቹን እንቅስቃሴ ተከትሎ "ሕዝቡን ለማረጋጋት" እና "ድንበሩን ለመመልከት" ወደ አካባቢው የተጓዙት የላሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቶክ ሞንግ በተከፈተባቸው ጥቃት እንደቆሰሉም ምንጩ ገልጸዋል።
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መረጃም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ትናንት ሐሙስ ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም. ተኩስ እንደተከፈተባቸው እና
አረጋግጧል።በቀኝ እግራቸው ታፋ ላይ ተመትተው መቁሰላቸውን
የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ "የመንግሥት አካላት" በአካባቢው የተገኙት በደቡብ ሱዳን የተነሳው "የእርስ እርስ ግጭት" በድንበር አካባቢ በሚገኘው
መሆኑን ለማጣራት እንደነበር ገልጿል።ፓጋግ ቀበሌ ኩብሪ ቢልኩን ተብሎ ወደ ሚጠራው አካባቢ እየተዛመተ

የላሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቶክ ሞንግ
የወረዳ ዋና አስተዳዳሪው በጋምቤላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።
አቶ ቶክ
በአሁኑ ሰዓት "በጥሩ ሁኔታ ላይ" እንደሚገኙ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የወረዳ ኃላፊ ገልጸዋል።ሰውነታቸው ውስጥ የገባው ጥይት ባይወም
ከወረዳው አስተዳዳሪ ውጪ
የሚናገሩት ኃላፊው፤ የአካባቢው ታጣቂዎች እና ፖሊስ የምላሽጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች እንደሌሉ
ጠቅሰዋል።ተኩስ ከመክፈት መቆጠባቸውን
በአካባቢው የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች
ሲሉም እርምጃ ያልተወሰደበትን ምክንያት አስረድተዋል።ተኩስ ቢከፍቱ ኖሮ ብዙ ጉዳት ይደርስ ነበር
ኃላፊው እንደሚገልጹት፤ ድንበሩን አቋርጠው የገቡት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች አሁንም አካባቢውን "እንደተቆጣጠሩ" ናቸው።
ብለዋል።እንደ መረጃ ያገኘነው እዚያ ብዙ ቤት ተቃጥሏል። በርካታ ሕዝብ እየተፈናቀለ ነው ያለው
ከአካባቢው የሸሹ ነዋሪዎች ወደ ወረዳው ዋና ከተማ ኮርገንግ እየገቡ መሆኑንም አክለዋል። ታጣቂዎቹ፤ በፓጋግ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው እና የድንበር አካባቢ የሆነውን "ብልኩን" የተባለ መንደር "ሙሉ በሙሉ" እንደተቆጣጠሩት ኃላፊው ተናግረዋል።
እንደ ምንጩ ገለጻ የታጣቂዎቹን እንቅስቃሴ ተከትሎ የወረዳው አስተዳደር ከክልሉ መንግሥት ድጋፍ እንዲደረግለት ጥሪ አቅርቧል።
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መረጃ ላይም የላሬ ወረዳ ፖሊስ
መግለጹን ጠቅሷል።ከዞኑ እና ከክልሉ ፖሊስ እንዲሁም ከሚመለከታቸው የፌደራል የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ሁኔታውን በቅርበት በማጣራት ላይ እንደሚገኝ
በዛሬው ዕለትም [አርብ] የክልሉ እና የዞኑ የመንግሥት፣ የፀጥታ እና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የተፈናቀሉ ሰዎችን ለመጎብኘት ወደ ኮርገንግ ከተማ መጓዛቸውን ምንጩ ተናግረዋል።
ቢቢሲ በጉዳዩ ከጋምቤላ ክልል ሌሎች ባለሥልጣናት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።