quote=Selam/ post_id=1509690 time=1727262970 user_id=48435]
አክሱመ-ጩፋ - እሱም የመረጃ ሐዋርያ አንተም የመረጃ ደቂቀ እስጢፋኖስ፣ ታዲያ ምን ይሁን ብለህ ነው ይኸንን ኤርትራዊ ነኝ ባይ ምስኪን መነኩሴ የምትጨቀጭቀው?
የእሱና የአንተ መንፈሳዊ አስተዋፆ ባይኖር ኖሮ እኮ፣ ጥላዎቹ ነቀዝ ሻቦዎች እስከ አሁን የጥላቻ መርዛቸውን ይረጩብንና ይሰድቡን ነበር፤ ያንተ ተጋደላይ ወያኔዎችም እንደ ድሮው እንደ እባብ መሬት ለመሬት እየተሳቡ ይነድፉን ነበር ።
በእናንተ ያልተቋረጠ ብርታት የሁለታችሁም ቤት በደንብ ፀድቶና ተስተካክሎ ዛሬ ደግሞ ድንበሮቻችሁን ተሻግራችሁ እኛንም በጠሎታችሁ ለማደስና መስመር ለማስያዝ መድከም መጀመራችሁ ያስመሰግናችኋል። ታድያ ምን ዓይነት መንፈስ ቢገባባችሁ ነው ዛሬ ይኸንን ከቤት ጀምሮ እስከ ዓለም ድረስ የሚስፋፋ ትልቅ ቅዱስ ስራ አቋርጣችሁ ሲካፈል እንደሚጋጭ ዘራፊ እርስበእርስ የምትናቆሩት?
[/quote]