Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 35603
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ባህል ስልጣኔ አይደለም!

Post by Horus » 27 Apr 2025, 20:11

ብዙ ሰዎች ባህልን እንደ ስልጣኔ የመመልከት ስህተት ይሰራሉ። ባህል ያንድ ሕዝብ ወይም ማህበረሰብ አኗኗር ዘዬ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በፍጹም ስልጣኔ ነው ማለት አይቻልም ። ስልጣኔ ዘመናዊነት ነው። ዘመናዊ ማህበረሰብ ስልጡን ባህል አለው ማለት ይቻላል። ግን ባህል ያለው ሰው ሁሉ ስልጡን አይደለም ።

ለምሳሌ በዚህ 21ኛ ክፍለ ዘመን በእጅ ቆፍረው አትክልት የሚተክሉ እና በበሬ ሞፈር ቀምበር አርሰው እህል የሚያመርቱ ባህል አላቸው ማለት ይቻላል፤ ነገር ግን ዘመናዊ ናቸው ስለሆነም ስልጡን ናቸው ማለት ግን አይችላም ።

ይህ ለምን ሆነ? ለምሳሌ ለምንድን ነው ኢትዮጵያዊያን እስከ ዛሬ በዎለት ቆፍረው በበሬ አርሰው የሚኖሩት? ለሚለው እጅግ ፈታኝ ጥያቄ አንዱና ዋንኛው መልስ የኢትዮጵያዊያን ካልቸር ለፈጠራ ፣ ለስራ ፣ ለፍልሰፋና መሻሻል ያላቸው አሉታዊ እና የንቀት አመለካከት ነው። ለዘመናት በኢትዮጵያ ሰራተኛ ተሰድቧል! አንጥረኛ ተንቋል! ሸካል ሰሪ ፣ ቀጥቃጭ ፣ፋቂና መድሃኒተኛ ከሰው በታች ተደርጎ ታይቷል!

ለኢትዮጵያ ኋላ ቀርነት ፣ ስልጣኔ አልባነት ፣ ኢዘመናዊነትና ብሎም ድህነት ይህ አደገኛ ፣ አሳፋሪና አሳዛኝ የድንቁርና ካልቸር ነው ።

ስለዚህ አንድ ሕዝብ ካልቸር ስላለው ብቻ ስልጡንና ዘመናዊ አይሆንም! ስልጡን ዘመናዊ ሕዝብ አዳዲ ነገሮችን የሚፈጠር ፣ የሚፈለስፍ ፣ የሚጠይቅ ፣ ችግሮችን ለመፍታት የሌሉና ያልታሰቡ መንገዶችን የሚቀድ ፣ አንጎሉ ክፍት የሆነ ፣ አዲስ ነገርን ለመማር የማይፈራ እና ለእውቀትና መፈላሰፍ ዋጋ የሚሰጥ ሕዝብ ነው ስልጡን ዘመናዊ ሊባል የሚችል!

ቸሩ ፈጣሪ ለዚያ ያብቃን! አሚን!

Union
Senior Member
Posts: 11448
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: ባህል ስልጣኔ አይደለም!

Post by Union » 28 Apr 2025, 00:54

ጋላ ስልጤ Horus

አንቺ ግራ የገባሽ ካድሬ :lol: :lol: :lol:

The derg had thousands of tractors and farm helicopters :lol: :lol: :x :x

Horus
Senior Member+
Posts: 35603
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ባህል ስልጣኔ አይደለም!

Post by Horus » 28 Apr 2025, 01:24

Union wrote:
28 Apr 2025, 00:54
ጋላ ስልጤ Horus

አንቺ ግራ የገባሽ ካድሬ :lol: :lol: :lol:

The derg had thousands of tractors and farm helicopters :lol: :lol: :x :x
ኢትዮጵያ መጨረሻ ላይ አንተን መሰል ሪአክሽነሪ ካልቸርና ድንቁርና ሸክም እያራገፈች ነው! 24/7 ትንፈራገጣለህ :lol: :lol:

Selam/
Senior Member
Posts: 15032
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ባህል ስልጣኔ አይደለም!

Post by Selam/ » 28 Apr 2025, 06:39

ጭልፊቱ

ባህል አንድን ማህበረሰብ አጣብቆ የሚይዝ፣ የዕውቀት፣ የዕድገትና የስልጣኔ መሰረት ነው። ይኸም ማለት ከእንሰሶች በስተቀር፣ የባህል መገለጫ የሌለው ህብረተሰብ የለም ማለት ነው።

የግሪክ የሃይማኖት፣ የፍልስፍናና የቤተሰብ ባህል፣ የዓለም የስልጣኔ መሰረት ነው። ዛሬ ቢሆን ኖሮ እንደ ዕብደት የሚቆጠረው፣ የግብፅ የአምልኮ ባህልም የሂሳብ ቀመርን፣ ፅሁፍን፣ ህክምናንና የመሳሰሉትን ለዓለም ስልጣኔ አበርክቷል። ዛሬ እነዚህ ሃገሮች ጥንታዊ ባህሉንም ጥለውት ሄደው በስልጣኔ ግን ወደ ኋላ ቀርተዋል።

ይኸም ማለት ባህል ባለበት ተቸክሎ የሚቀር ሳይሆን የሚሻሻል፣ የሚለወጥና የሚከስም ነው ማለት ነው። ይኸንን በይበልጥ የሚያደርጉት ደግሞ፣ የውጪ ተፅዕኖዎች፣ የተማሩት ህብረተሰቦችና የሃገር አስተዳዳሪዎች (authorities, aristocrats & academics) ናቸው። ያም ማለት ለዕድገትም ይሁን ለውድቀት ዋናው ተጠያቂዎቹ እነሱ ናቸው እንጂ ግብር እየከፈለ የሚያስተምራቸው ምስኪኑ ህዝብ አይደለም ማለት ነው።

ታዲያ ኢትዮጵያን በተመለከተ እነዚህ ሰዎች ስልጣኔ ማለት የሌላውን ሃገር ቴክኖሎጂ መኮረጅና መግዛት ብቻ ስለሚመስላቸው፣ ባህሉን ከታች ወደላይ ከመለወጥ ይልቅ፣ ብልጭልጭ ቁሳቁሳ በላዩ ላይ እየለጠፉበት የዕውቀት መሰረት የሌለው ባዶና ተለጣፊ ባህል ፈጥረዋል። እንደ ድሮው እርስ በእርሱ የሚተሳሰብና የሚደጋገፍ ሳይሆን በጥላቻ የሚፏከት ጃርት የሆነ አዲስ ትውልድ መስርተዋል።

የካድሬ ዋናው ጠባይ፣ ለማንኛውም ጥፋት ተራውን ህዝብና ዕሴቱን መውቀስና አስተዳዳሪዎቹን መከላከል ስለሆነ፣ አንተም ደግመህ ድሃውን በመስደብህ አልተደነቅኩም። ግን ለመሆኑ በኢህአፖና በኢንተርናሲዮናሊዝም ፍልስፍና ተወጥረህ ባህልና ህብረተሰቡን ልታጠፋው ከመሞከር፣ ሲያስቸግርህ ሸሽተህ ከመሄድና ከሩቁ ሆነህ ከመዝለፍ በስተቀር እንዲሻሻል ምን አድርገሃል?

Union
Senior Member
Posts: 11448
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: ባህል ስልጣኔ አይደለም!

Post by Union » 28 Apr 2025, 17:38

ጋላስልጤ Horus ግዜዋ አልፏል አይገባትም :lol:

Naga Tuma
Member+
Posts: 6026
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ባህል ስልጣኔ አይደለም!

Post by Naga Tuma » 29 Apr 2025, 22:25

Horus wrote:
27 Apr 2025, 20:11
ብዙ ሰዎች ባህልን እንደ ስልጣኔ የመመልከት ስህተት ይሰራሉ። ባህል ያንድ ሕዝብ ወይም ማህበረሰብ አኗኗር ዘዬ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በፍጹም ስልጣኔ ነው ማለት አይቻልም ። ስልጣኔ ዘመናዊነት ነው። ዘመናዊ ማህበረሰብ ስልጡን ባህል አለው ማለት ይቻላል። ግን ባህል ያለው ሰው ሁሉ ስልጡን አይደለም ።

ለምሳሌ በዚህ 21ኛ ክፍለ ዘመን በእጅ ቆፍረው አትክልት የሚተክሉ እና በበሬ ሞፈር ቀምበር አርሰው እህል የሚያመርቱ ባህል አላቸው ማለት ይቻላል፤ ነገር ግን ዘመናዊ ናቸው ስለሆነም ስልጡን ናቸው ማለት ግን አይችላም ።

ይህ ለምን ሆነ? ለምሳሌ ለምንድን ነው ኢትዮጵያዊያን እስከ ዛሬ በዎለት ቆፍረው በበሬ አርሰው የሚኖሩት? ለሚለው እጅግ ፈታኝ ጥያቄ አንዱና ዋንኛው መልስ የኢትዮጵያዊያን ካልቸር ለፈጠራ ፣ ለስራ ፣ ለፍልሰፋና መሻሻል ያላቸው አሉታዊ እና የንቀት አመለካከት ነው። ለዘመናት በኢትዮጵያ ሰራተኛ ተሰድቧል! አንጥረኛ ተንቋል! ሸካል ሰሪ ፣ ቀጥቃጭ ፣ፋቂና መድሃኒተኛ ከሰው በታች ተደርጎ ታይቷል!

ለኢትዮጵያ ኋላ ቀርነት ፣ ስልጣኔ አልባነት ፣ ኢዘመናዊነትና ብሎም ድህነት ይህ አደገኛ ፣ አሳፋሪና አሳዛኝ የድንቁርና ካልቸር ነው ።

ስለዚህ አንድ ሕዝብ ካልቸር ስላለው ብቻ ስልጡንና ዘመናዊ አይሆንም! ስልጡን ዘመናዊ ሕዝብ አዳዲ ነገሮችን የሚፈጠር ፣ የሚፈለስፍ ፣ የሚጠይቅ ፣ ችግሮችን ለመፍታት የሌሉና ያልታሰቡ መንገዶችን የሚቀድ ፣ አንጎሉ ክፍት የሆነ ፣ አዲስ ነገርን ለመማር የማይፈራ እና ለእውቀትና መፈላሰፍ ዋጋ የሚሰጥ ሕዝብ ነው ስልጡን ዘመናዊ ሊባል የሚችል!

ቸሩ ፈጣሪ ለዚያ ያብቃን! አሚን!
በቅርቡ ስለ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ዝና የለጠፍከዉን ኣይቼ ተምሮ ፍሬ መሆን በጎ ነዉ፣ በተጨማሪም እነሱ ያመጡትን የፈጠራ ፍሬዎችን ዘርዝርልን ለማለት ፈልጌ ይቅር ብዬ ኣለፍኩኝ።

እዚሁ ፎረም ላይ ስልጣኔ ማለት ስለ ስልጣን ነዉ ብለን ተወያይተን ከተስማማን ብዙ ኣልሰነበተም።

ሸነቸ እና ሴኔት ስለ ስልጣን ባህል መሆኑን ተወያይተን ነበር።

ስለዚህ ስልጣኔ ማለት ስለ ስልጣን ማለት መሆኑን ኣትዘንጋ። ስልጣን በዲሞክራሲ ይሁን ስልጣኔ ነዉ።

የሲቭላይዜሽን ቃል መሠረት ሲቭል ነዉ። ሰላማዊ ማለት ነዉ። ነጋ ማለት ነዉ።

ነገሠ ሲባል ሠላም ሆነ፣ ሠላም ነገሠ ማለት ኣይዴለም? ሕግ ነገሠ ማለት ኣይዴለም? ሴረ ነገሠ ማለት ኣይዴለም?

ሴረ ቱማ ወይም ሕግ መመስረት የሴረ በላይነት ነገሠ ማለት ኣይዴለም? የስልጣኔ መጀመር ማለት ኣይዴለም?

ኣርስቶትል ሰዉን ራሽናል ኣኒማል ያለዉ ስለምን ነበር? ሶክራትስ ገበያተኛ የሞላበት መሃል ችቦ ይዞ ሰዉ ፍለጋ የሮጠዉ ስለምን ነበር?

የግሪክ ስልጣኔ ተጀመረ የተባለዉ ጥቁር እና ነጭ ጠጠሮችን ገንቦ ዉስጥ በመወርወር ስልጣን ላይ የሚወጣን በመምረጥ ነበር ተብሏል።

ተወያይተዉ ምርጫን የተማሩት ከሌላ ቦታ ነበርም ተብሏል።

ስለዚህ ስልጣኔ ስለ ምን እንደሆነ በጥልቁ ለመለየት ስልጣን እና ሲቭል ወይም ሰላማዊ በቂ ቃላት ኣይዴሉም?

ለፈጠራ የሚገፋፋ የአከባቢ ተፈጥሮም ነዉ ተብሏል።

የዐለም በርካታ ከተሞችን ተፈጥሮ ትንሽ ኣጥንቼ አዲስ አበባ ለሆምዮስታሲስ ኣንደኛ መሆኑን ኣስተዋልኩኝ። ቀጥሎ ያገኘሁት ሳን ድዬጎ ነዉ።

በተፈጥሮ አየሩ እና ዉሃዉ ተስማሚ ከሆኑ ማሞቅያ ወይም ማብረጃን ለመፍጠር ምንድነዉ ሰዉን የሚገፋፋዉ?

ዐለም ላይ ኣዲስ ነገር የፈጠሩት በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸዉ።

ሌላዉ የተፈጠረዉን እየተማረ ይጠቀማል።

ስለዚህ በእኔ አስተያየት ስለ ስልጣኔ ከተነሳ ነጋ፣ ሰላም፣ ሸነቸ፣ ሴረ፣ ሕግ እያለ ጥንት ግዜ ስልጣኔን የጀመረዉን ሕዝብ ለቀቅ ኣድርገህ የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት እና ሌሎች ፍሬዎች ምን ፈጠራችሁን ጠበቅ ማድረግ ነዉ።

Misraq:

ገዳ ማልቱ ዸልቼ፧?

Horus
Senior Member+
Posts: 35603
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ባህል ስልጣኔ አይደለም!

Post by Horus » 29 Apr 2025, 23:45

ናጋ፣
እንደ ተለመደው ትቀባጥራለህ ። ሲቪል ሰላም ማለት አይደለም። ሲቪል የከተማ ነዋሪ ማለት ነው። በባላገር ተበታትኖ ሳይሆን በከተማ ዜጋ ሆኖ ነዋሪ ማለት ነው ። ስልጡን ስልተኛ የተማረ ፣ ባለዘዴ ማለት ነው። ስልጣንና ሓይል የተያያዙት አገር የሚያስተዳድሩ እውቀትና ስልት ያላቸው ስልጡን ሰዎች ስለነበሩ ነው ፤ እንደ ዛሬ ደደብ መሃይም በጠብመንጃ መግዛት ሳይጀምር ።

ነገሰ ገዛ ማለት ነው ፣ ንጉስ ገዢ ማለት ነው እንጂ ሰላም ማለት አይደለም።

ሴራ ሕግ ማለት ሲሆን ሕግ ማገድ ፣ እግድ፣ ማስገደድ ማለት ነው ።

ስለዚህ ስለማታውቀው ነገር አትቀባጠር

ሰነቸው የሴራ አባት ማለት ሲሆን በእድሜና እውቀት የላቁ የሴራ የሕግ አባቶች ናቸው ።

ሴራ የኦሮሞ ቃል ሳይሆን ሸሪዓ ማለት ሲሆን የሴም ቃል ነው ፣ እሱም ሕግ ማለት ነው ፤ ዛሬ እስላሞች የሚገዙበት !

Post Reply