Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 35643
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

HERE IS ANOTHER GENIUS! ብሩክ ብርሃኑ 13 ዓመቱ ነው! ማየት ማመን ነው!!!

Post by Horus » 26 Apr 2025, 11:25

የዚህን ህጻን ልጅ ሌላውን ትተን የቋንቋ ችሎታው ብቻ ያስገርማል! እድሜና ትምህርት ላይ ያለንን አስተሳሰብ ሁሉ ይለውጣል ። ልጆች ትምሀር ቢያንስ ከ3 አመት መጀመር አለባቸው ። ልጆች በ12 አመት ኮሌጅ መግባት አለባቸው ።

Dama
Member
Posts: 4318
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: HERE IS ANOTHER GENIUS! ብሩክ ብርሃኑ 13 ዓመቱ ነው! ማየት ማመን ነው!!!

Post by Dama » 26 Apr 2025, 11:52

CROSS. CROSS. CROSS. CROSS. CROSS.CROSS.
Fanatic adults are plenty. Usually violent radicals. Intolerant. Discriminators. Alienators. The other versions of Siltes.

Affable
Member
Posts: 354
Joined: 15 Jul 2023, 13:21

Re: HERE IS ANOTHER GENIUS! ብሩክ ብርሃኑ 13 ዓመቱ ነው! ማየት ማመን ነው!!!

Post by Affable » 26 Apr 2025, 11:53

አወ ጥሩ ታዝበሀል Horus. ልጁ ከቴክኖሎጂ እውቀቱ ባሻገር የቋንቋ አጠቃቀሙ የሚያስደንቅ ነው። በ እንግሊዘኛ የተጠቀማቸውን ቃላቶች እንኳ በትክክል ትርጉማቸው ምን ማለት እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። “ግለተኝነት” የሚለውን ቃል ተጠቅሜበት የማውቅ አይመስለኝም። ከሱ ነው የሰማሁት። He is a genius ; no doubt about it.

Horus
Senior Member+
Posts: 35643
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: HERE IS ANOTHER GENIUS! ብሩክ ብርሃኑ 13 ዓመቱ ነው! ማየት ማመን ነው!!!

Post by Horus » 26 Apr 2025, 12:48

Affable wrote:
26 Apr 2025, 11:53
አወ ጥሩ ታዝበሀል Horus. ልጁ ከቴክኖሎጂ እውቀቱ ባሻገር የቋንቋ አጠቃቀሙ የሚያስደንቅ ነው። በ እንግሊዘኛ የተጠቀማቸውን ቃላቶች እንኳ በትክክል ትርጉማቸው ምን ማለት እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። “ግለተኝነት” የሚለውን ቃል ተጠቅሜበት የማውቅ አይመስለኝም። ከሱ ነው የሰማሁት። He is a genius ; no doubt about it.
እንደ ምታውቀው ስለ ህጻናት ኮግኒቲቨ እድገት ድሮ እነ ጀን ፒያዤ የሰሩት ምርምር ያረጀ ይመስለኛል ። ስለ ሕጻናት ፐርሰናሊት ፎርሜሽን (መቀረጽ) ላይ ያለው የ6 እና 7 አመት ወሰን ያረጀ ይመስለኛል። ዛሬ በመላው አለም ሕጻናት እጅግ ትንሽ ሆነው አንጎላቸው ኮምፕሌክስ ጽንሰ ሃሳቦችን የመገንዘብ እና ፕሮሴስ የማድረግ ፣ ምክንያታዊ ህሳቤ (ሪዝኒግ) ችሎታቸው በጣም በትንሽነት ላይ እያሉ መግለጽ ጀምረዋል።

ዘመኑ በቴክኖሎጂና ሰው ሰራሽ ክህሎት እየመጠቀ ሄዶ እኛ ግን ስለ ትምህርትና ስልጠና ያለን ፍልስፍና ወደ ኋላ ቀርቷል ። እነዚህ ምጡቅ የምንላቸው ሕጻናት የቀድሞው የትምህርትና ስልጠናን ፓራዳይም እያፈረሱት ነው ። They are a wake up call for change in our understanding of infant cognition and cognitive development of children.

የ3 አመት ልጅ ቢያንስ 1ኛ ክፍል መጀመር ይኖርበታል! በ4 አመታቸው ኮድ የሚያደርጉ ህጻናት እየበዙ ነው ። ስለዚህ ማንኛውም ልጅ በ15 አመቱ ኮሌጅ የሚደርስ ከሆነ ዛሬ ምጡቅ የምንላቸው ከ11 እስከ 13 ባለው እድሜ ኮሌጅና ከዚያም በላይ የሚደርስ እድገት ይኖራቸዋል።

Post Reply