Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 13622
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ይድረስ ለምሬ ወዳጆ --> " አሸንጌ ሀይቅ ላይ የትግራይ ወያኔ ከየትም መጥቶ ዓሣ እያጠመደ፤ አንተ ግን ደጉን የወሎ ሰው ጀ/ል ፈንታው ሙሃባውን ለማጥመድ ትለፋለህ ይባላል]።

Post by Abere » 23 Apr 2025, 09:26

ይድረስ ለምሬ ወዳጆ --> " አሸንጌ ሀይቅ ላይ የትግራይ ወያኔ ከየትም መጥቶ ዓሣ እያጠመደ፤ አንተ ግን ደጉን የወሎ ሰው ጀ/ል ፈንታው ሙሃባውን ለማጥመድ ትለፋለህ ይባላል]። ሙሉ ወሎ እያዘነብህ ነው። ቀድሞውኑ ወያኔ አሸንጌ ሀይቅ እግሩ ውሃ እንዳይነካ መታገል ሲገባህ፤ የትግል አጋዥ የሆነውን ጀኔራል ፋንታውን ተጻራሪ መሆን ከየት የመጣ ነው? ለታሪክህ የምትሰራ ከሆነ የከፈልከው መስዋዕትነት ዋጋ እንድኖረው ከፈለግህ ይህ ሰዎች መሳለቂያ ካደረጉት "ህወሓት ፋኖ" እራስህን ብታገል መልካም ነው። ከወልቃይት ጠገደ ኮ/ል ደመቀ ትምህርት መውስደ ይቻላል። በራያ ኮረም አላማጣ ያሉ አማራዎች የሚያደራጃቸው፤ የሚሰለጥናቸው፤የሚያሰማራቸው አታጋይ ይፈልጋሉ። አሸንጌ ሀይቅ ያለቦታው መጥቶ ዓሳቸውን የሚለቅመውን የአክሱም፤የሽሬ፤የአድውዋ ወፈ-ሰማያት ወያኔ መልቀም ይፈልጋሉ። የአንተ ቁጥር 1 አላማህ ይህ ነው መሆን ያለበት። ይህን ትግል በራያ ኮረም አላማጣ ህዝብ መሀል ካልሆነ ከየት ተነስታችሁ ነው ወሎን ከወያኔ ነጻ የምታወጡት? የራያ ኮረም አላማጣ ህዝብ በታሪክ በአጼ ዮሀንስ ሲሰቃይ የነበረ አሁንም በመንጋ ወያኔ እየተገደለ እየተጋጠ ያለ - እርስቱ እንጅ ህዝቡ የማይፈለግ ነው። የአማራ ህዝብ የትግል መነሻ እኮ 1ኛው እና ዋናው የራያ ህዝብ እምባ፤እልቂት እና ግፍ ነው። ያግፍ በኦሮሙማ ተባባሪነት በወያኔ የምልልስ አጥቂነት ተጠናክሮ በቀጠለበት ሁኔታ የትግል አጋርህ ከሆነው ጀኔራል ፋንታው ሙሃባው ጋር ቅራኔ መግባት ተገቢ አይደለም። የወሎ ህዝብ ከትግል መሪዎቹ ትልቅ ቁም ነገር ይጠብቃል - ወሎ ጠቅላይ ግዛት ከኦሮሙም እና ወያኔ ነጻ መሆን። ለዚህ ደግሞ አንድነት ሃይል ነው እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጄኔራሉ ጋር ሰላም ፍጠር - ይህን ካላደረግህ በእውነትም ህወሓት ፋኖ ሁነሃል። የትግል ልፋትህም እንደ አህያ ስጋ ረክሶ ይቀራል። የወሎ ህዝብ በታሪክ በተለያዩ ነገስታት ከኢትዮጵያኖች ሁሉ በተለየ መልኩ ሲሰቃይ፤ሲዘረፍ ኑሯል - በቅርቡ እንኳን ከዐጼ ቴዎድሮስ ጀምሮ እንደ ወሎ የተረገጠ የተዘረፈ ክ/ሀገር የለም - ይህ ሊያቆም የግድ አንድነት ይላል።