Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Fiyameta
Senior Member
Posts: 16872
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ለማስታወስ ያህል.... የአቢይ አህመድ አማካሪ ሆኖ የተሾመው ጌታቸው ረዳ ከዚህ ቀደም ስለ አቢይ አህመድ ከተናገራቸው ... ከባህር በጭልፋ!! ▶︎ •၊၊||၊|။||||။‌‌‌‌‌၊|•

Post by Fiyameta » 19 Apr 2025, 15:52

የጌታቸው ረዳ አማካሪ እንደሆነ የሚነገርለት አይተ Meleket ትግራይን ከድቶ ብልፅግናን ከተቀላቀለ ወዲህ በታማኝነትና በትጋት አቢይ አህመድንና የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስን እንደ ትጉ ባሪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። :oops: :oops:








Meleket
Member
Posts: 4247
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ለማስታወስ ያህል.... የአቢይ አህመድ አማካሪ ሆኖ የተሾመው ጌታቸው ረዳ ከዚህ ቀደም ስለ አቢይ አህመድ ከተናገራቸው ... ከባህር በጭልፋ!! ▶︎ •၊၊||၊|။||||။‌‌‌‌‌၊|•

Post by Meleket » 22 Apr 2025, 10:53

ለሰላም የሚተጉ፡ መልካም ልብ ያላቸውን ዜጎች እናከብራለን።

ለእውነት በጽናት በመቆም፡ በእውቀት ታግዘው፡ በሰላማዊ ትግል፡ ህዝብን ሳያሰልሱ በማንቃት ለሚተጉ ዜጎች እውቅናና ክብር መስጠት ይገባናል።

በቀጠናችን ቦተሊካ፡ እንዲህ ዓይነቱን ኣመለካከት እንደ የዓላማ ጽናት ኣንግቦ፡ ለቀጠናችን ህዝብ ቋሚና ዘለቄታዊ ሰላምን ለማስገኘት፡ ሳይታክትና ሳይደክም፡ በሙሉ ኅሊና ሲተጋ ያየነውን የትግራይ ልጅ፡ ኢትዮጵያዊዉን ጋዜጠኛና የማኅበረሰብ ኣንቂ፡ ማሞገስ፡ ኣይዞህ በርታ በማለት፡ ሞራላዊ ድጋፍን ልንቸረው የሚገባበት ግዜ ላይ ደርሰናል።

ጋዜጠኛውና ያዲሱ ትውልድ ልሒቕ ስታሊን ገብረስላሴ [ዛራ ሚዲያ ኔትወርክ]

ሰላማዊ ጽኑ ዓላማን ኣንግበህ፡ በግብርይውጣና በእልህ በተሞሉ የቀጠናችን “ቦለቲከኞች” ዬተበላሸን ቀጠናዊ ሁኔታ፡ ወደ ሰላም ለመመለስ፤ በቀጠናው ህዝቦች ላይ ባለማባራት እንደ ዶፍ ዝናብ የወረደውን ሞትና ቅዝፈት በመጠዬፍ፡ እንዳይደገም ብቻ ሳይሆን ኣሁን በዚህ ሰዓትም እንዲቆም ለማስቻል፡ በትጋት እዬሰራህ በመሆንህ፡ የሁለቱ ህዝቦች ሰማእታትና “በህይወት” ያሉ ዜጎች በመላ፡ "የሰላማዉያን ሰማእታቶቻችን ሰላማዊ ኣደራ የተሸክምክና ያነገብህ፡ የዓላማ ሰው ነህና ክብር ይገብሃል” ብለናል።

በ146ቱ የጋራ ፈርጦቻችን ማለትም በሄግ ብይን መሰረት በተመላከቱት 146 የፊዚካል ዲማርኬሽን ነጥቦች ወይ ቦታዎች ላይ፡ የሁለቱ ሃገራት የድንበር ሰላም ጥበቃ የሰራዊት ክፍሎች ብቻ ሳይሆን፡ ባለፉት አስከፊ ጦርነቶች መካከል የተሰው የሁለቱ ህዝቦች ሰማእታት ሓወልቶች ወይ የክቡር ኣስከሬኖቻቸው ማረፊያ ይሰራ ወይ ይታነጽ ዘንድ እንጠይቃለን። [ስፍራው የሁለቱ ህዝቦች ሰማእታት በክብር የሚቀመጡበት ሰላማዊ ሰፈር ሆኖ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊተላለፍ ይገባል።] እንላለን እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ በተለመደው ኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

እርግጥ ነው ኤርትራዉያን ይሁኑ ትግሬዎች ወይም ኣማሮች ወይም ዓፋሮች ወይም ኦሮሞዎች በደፈናው ኢትዮጵያዉያን፡ የማኅበረሰብ ኣንቂዎች በመላ፡ የሄጉ የድንበር ብይን በሰላማዊ መንገድ ይተገበር ወይም መሬት ላይ ወርዶ በፊዚካል ዲማርኬሽን ኣማካኝነት ሥጋ እንዲለብስ ሳያሰልሱ ሊተጉ ይገባል። ምክንያቱም የቀጠናው ህዝቦች የዘለቄታዊ ሰላም ዋስትናና ብቸኛ ፍኖት ይህ ስለሆነ። ይህን ሰላማዊ ተግባር ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ወይም በሰላማዊ መንፈስ እንዲተገብር የማይሹ ኣካላት በሙሉ፡ “ጥላቻ፡ ቂም በቀልና ተንኮል ላይ” የተጣዱ፡ በህዝቦቻችን ውስጥ ያሉ ጥቂት የጦርነት ጥቅመኞች [ጦ.ጥ.] ብቻ ናቸው።



ሰላማዊዉ የፊዚካል ዲማርኬሽን ትግባሬ” የኤርትራ ሰፊ ህዝብ ብቸኛው ሰላማዊ ምርጫ ነው!
ሰላማዊዉ የፊዚካል ዲማርኬሽን ትግባሬ” የትግራይ ሰፊ ህዝብ ብቸኛው ሰላማዊ ምርጫ ነው!
ሰላማዊዉ የፊዚካል ዲማርኬሽን ትግባሬ” የዓፋር ሰፊ ህዝብ ብቸኛው ሰላማዊ ምርጫ ነው!
ሰላማዊዉ የፊዚካል ዲማርኬሽን ትግባሬ” የኣማራ ሰፊ ህዝብ ብቸኛው ሰላማዊ ምርጫ ነው!
ሰላማዊዉ የፊዚካል ዲማርኬሽን ትግባሬ” የኦሮሞ ሰፊ ህዝብ ብቸኛው ሰላማዊ ምርጫ ነው!
ሰላማዊዉ የፊዚካል ዲማርኬሽን ትግባሬ” የኢትዮጵያ ሰፊ ህዝብ ብቸኛው ሰላማዊ ምርጫ ነው!


ብቸኛው የቀጠናችን ችግር መፍትሔ፡ “የኤርትራና ኢትዮጵያ ድንበር ሰላማዊ ትግባሬ [ፊዚካል ዲማርኼሽን] ነው።" ከዚያ ቀጥሎ በጋራ የሚኮሰኮሰውና እንዲጎለብትና እንዲዳብር የሚደረገው የቀጠናው ህዝቦች ሰላማዊ ግንኙነትና መስተጋብር ደግሞ በማይበጠሰው የፍቅር ሰንሰለት ይጠመር ዘንድ፡ የቀጠናው ህዝቦች ቦለቲከኞችና ኣመራር ኣካላቶችን ሚናና መልካም ፍላጐት፡ ጥረትና ቁርጠኝነትን ይጠይቃል [150 ሚልየን ነጥቦች]

Meleket
Member
Posts: 4247
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ለማስታወስ ያህል.... የአቢይ አህመድ አማካሪ ሆኖ የተሾመው ጌታቸው ረዳ ከዚህ ቀደም ስለ አቢይ አህመድ ከተናገራቸው ... ከባህር በጭልፋ!! ▶︎ •၊၊||၊|။||||။‌‌‌‌‌၊|•

Post by Meleket » 22 Apr 2025, 11:21

ይህ ትግራይ ካፈራቻቸው 4 ጎምቱ ቦለቲከኞች አንዱ እንደሆነ የሚገለጸው፡ ብርሃነ የተባለ የቦለቲካ ኣዝማሪ፡ “ኣንቀጽ 39ን ተጠቅመን፡ የራሳችንን እድል እራሳችን እንወስናለን፡ ቢያንስ ቢያንስ ከዓዲ ግራት ጀምረን፡ ከኤርትራ ጋር ተቀላቅለን፡ “ዓባይ ትግራይ” የሚለው ትልማችን ባይሳካም “ዓባይ ኤርትራ” እንድትመሰርቱ፡ እንጠይቃለን” ብሎ እንዳያስቀን እዬሰጋን ነው! :mrgreen:

የኢትዮጵያ መንግስት፡ ዓለም ያወቀውን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው፡ ያለ መግቢያ ፈቃድ ዘው ብለው ወደ ሃገሩ የሚገቡ ማንኛቸውንም ዜጎች፡ በተለይ ደግሞ ህጋዊ መንግስትን ለመገርሰስ ኣስበው ከ “ሽብርተኞች” ጋር ሲዶልቱ የተገኙ ሰዎችን፡ ኢንተርፖል ሊያሳድንና ሊያሳድድ ስለሚችል፡ የኛውን ኣጥንት ቆጣሪ ኣንቂ፡ ጥንቃቄ ቢያደርግ እንመክረዋለን። ከኣንዳርጋቸው ጥጌ ቢማር መልካም ነው ብለን አንሳልቅበትም፡ ምክያቱም ዛላምበሳ ድረስ ዘው ብሎ ገብቶ የጦቢያን መንግስት በማማት፡ ሰሜን እዝን በገፍ ከገደሉ ኣካላት ጋር ሲዶልት፡ የሚያሳይ ምስሉን ራሱ የኛው ኣጥንት ቆጣሪ ኣንቂና፡ ኤርትራዉያን ኣባቶችን ዘላፊ “ወዲ ሓወቦና” ያላንዳች ይሉኝታ ዘርግቷልና!

Meleket wrote:
21 Apr 2025, 05:17
ዓድዋ፣
ክትመጸኩም ዲያ ክትከድዋ!

ዓዲግራት፣
ከድኩማ’ዶ መጸት!

እንደጠረጠርነው ዓወል ስዒድ የተባለው “ኣንቂ” ወደ ትግራይ ኣቅንቸ፡ ብርሃነ የተባለ ትግራዋይ የሕወሓት ‘ታጋይ’ ጋር ተገናኝቻለው ሲል፡ እኛ በፋሲካ በኣል ኣማካኝነት “በጨለማ ያለ ህዝብ ብርሃን ኣዬ” የሚል የቅዱስ መጸሓፍ ቃል እየተነበበልን ነበር። ለማንኛውም ይህ ኣጥንት ቖጣሪ የነበረ ኣንቂ፡ በለቀቀው መልእኽት በ50፡23 ኛ ደቂቃ ላይ ሑመራን ወልቃይትን ጸለምትን “ክልል ትግራይ” ማለትም “Tigray region” ብሎ በቀይ ቀለም የተጣፈበት ካርታ በማሳዬት፡ እዉቅናዉን ለትግራይ ለመስጠትና ለመሸለም ሲውተረተር ኣይተነዋል። እነ ስታሊንን ሃይለንና ሌሎች የትግራይ ህዝብ ኣንቂዎችን ለማማለል መሆኑ ነው! “ኣዬ ቦተሊካ፡ የብረዚደንታችን ኣያት ያረፉባት ጐንደር ምን ትል ይሆን” ብለን አንሳለቅም። :mrgreen:

ለመሆኑ በፖለቲካዊ መፍትሔ ኣማካኝነት መፈታት የሚገባው የነሑመራ ወልቃይትና ጠለምትን መሬት ለትግራይ ክልል መስጠቱ ለምን ዓላማ ነው? ኣማሮችንና ፋኖን ባጠቃላይ ኣያሳዝንምን? ኣንለዉም፡ ምክንያቱም እኛን ይበልጥ የሚያሳስበን የኤርትራና የኢትዮጵያ ድንበር በቅጡ ፊዚካል ዲማርኬሽን እንዲከናወንበት መወትወት እንጂ በጐረቤት ሃገር ለመቀላወጥ ዘው ብሎ መግባት ወይም በጐረቤት ሃገር ጉዳይ ዘው ብሎ መግባት ኣይደለምና! :mrgreen:

በነገራችን ላይ ይህ ብርሃነ የተባለ “ቦለቲከኛ” ትግራይ ካፈራቻቸው አራቱ ብርቱ ቦተሊከኞች ኣንዱ ሆኖ ማለትም፡ የዓረነው ገብሩ አስራት፡ የደምህቱ ሞላ አስገዶምመድሚዳይ ጋር የሚመደብ፡ ብርቱ “ቦለቲከኛ” መሆኑ ይታወቃል።
:mrgreen:

ወዲ ሓወቦና መቼም ለዚህ የትግሬ ቦለቲከኛ የመጀመርያው ጥያቄ፡ “ኤርትራና ኢትዮጵያ ድንበራቸውን እንዳያካልሉ፡ ጠቅላዪ ኣብይ የመከላከያ ሰራዊት ከባድ መሳሪያዎች ከደንበር ኣካባቢ እንዲርቅ ሲወስኑ፡ ሕወሓት እንቅፋት በመፍጠር፡ ሰሜን ዕዝንም በማጥቃት፡ ኣላስፈላጊ ጦርነት ዳግም እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል?” ስለሚለው ኣባባል እይታህን ኣጋራን። “እነ ዋሾው ስዩም መስፍንና ኣባይ ጸሓዬ ድባቅ ሲመቱ የት ነበርክ?” ወዘተ የሚል ጥያቄዎች ይጠይቀዋል ብለን እንጠረጥራለን እኛ የነጎሚዳና የነ ኣባ ጥመሩ ኤርትራዉያን!።

ረሓብ ካለባችሁ ደግሞ ለናንተም ላማሮችም ለኦሮሞዎችም ለጦቢያዉያን ባጠቃላይ፡ በራችን ክፍት መሆኑን የሰፊዉ የኤርትራ ህዝብ መልእኽት ይድረስህ ብሎት ይሆናል ብለን እንጠረጥራለን፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር።

በኤርትራ የነጻነት ቀን አንድም ታዳሚ ሆኖ በኣካል ይገኝ ይሆናል ተብሎ የሚጠረጠረ “ብርሃነ”፡ የኤርትራን ህዝብ ይቅርታ ጠይቆ፡ የሄግን ብያኔን እንደሚያከብርም በይፋ ገልጦ፡ በኤርትራዉያን የሰማእታት ሓውልት ስር የኅሊና ጸሎት እንዲያደርግና እቅፍ ኣበባም እንዲያስቀምጥ ከወዲሁ እናሳስበዋለን፡ እኛ ባገርና በህዝብ ቀልድ የለም የምንለው፡ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች።

በኢትዮጵያ መንግስት ተጋብዘህ ወደ ኢትዮጵያ መግባትና፡ ሳትጋበዝ ያለ የማእከላዊ መንግስት ኣካላት ፈቃድ ዘው ብለህ መግባት ልዩነቱ ምን እንደሆነ እታለም Fiyameta እስኪ ለኛው 'ኣጥንት ቆጣሪው ኣንቂ' ኣስረጅልን! ለወዳጅሽ ለኮሎኔል ታሪኩም ሞቅ ያለ ሰላምታን ኣቅርቢልን።
:mrgreen:






Meleket
Member
Posts: 4247
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ለማስታወስ ያህል.... የአቢይ አህመድ አማካሪ ሆኖ የተሾመው ጌታቸው ረዳ ከዚህ ቀደም ስለ አቢይ አህመድ ከተናገራቸው ... ከባህር በጭልፋ!! ▶︎ •၊၊||၊|။||||။‌‌‌‌‌၊|•

Post by Meleket » 24 Apr 2025, 04:43

ኢትዮጵያ እንዳትፈራርስ ኣስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን” የምትለው፡ “የፎቶ ሾፗ 'ንግሥት' ዘመን ተሻጋሪ ምክረ ሃሳብ!
Fiyameta wrote:
29 Apr 2022, 02:59
Fiyameta wrote:
19 Apr 2025, 15:52
የጌታቸው ረዳ አማካሪ እንደሆነ የሚነገርለት አይተ Meleket ትግራይን ከድቶ ብልፅግናን ከተቀላቀለ ወዲህ በታማኝነትና በትጋት አቢይ አህመድንና የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስን እንደ ትጉ ባሪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። :oops: :oops:



Post Reply