Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 35332
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ዛሬ ቀዳም ሥዑር (ሥርዝ ቀዳም ሰንበት) ነው!

Post by Horus » 19 Apr 2025, 00:07

በተለምዶ ቅዳሜ የሚባለው ትክክለኛ ሥሙ ቀዳም ሰንበት ይባላል ፣ የኦሪት ሰንበት ነው ። ቀዳም ሰንበት ቀዳሚ ሰንበት ማለት ነው። ዛሬ ሥርዝ ቅዳሜ የተባለው ስለሚጾምበት ነው ። ከዛሬ ሌላ በቅዳሜም ሆነ እሁድ ስለ ማይጾም ነው ። የአማርኛ ተናጋሪዎች እሁድ የሚሉት የጉራጌ ኦርቶዶክሶች ዑር ሰንበት ይሉታል። ዑር የተለምዶ ትርጉሙ ዋና (አቢይ) ማለት ሲሆን ጥንታዊ ትርጉምና ሥረ ቃሉ ብርሃን ማለት ነው ። ለምሳሌ ዑራኤል ወይም የብርሃን አምላክ እንደ ምንለው ማለት ነው ።

መልካም ሣዑር (ሹር) ቅዳሜ እና ትንሳኤ ይሁንልን!




Post Reply