Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 35334
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ፍቸ ፋሲካ ማለት ነው ፡ ማኛም አሰላንህም!!

Post by Horus » 18 Apr 2025, 13:33

አገር ቤት መንደራችን የፊቸ ገበያ!


Odie
Member
Posts: 3533
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: ፍቸ ፋሲካ ማለት ነው ፡ ማኛም አሰላንህም!!

Post by Odie » 18 Apr 2025, 22:54

Horus wrote:
18 Apr 2025, 13:33
አገር ቤት መንደራችን የፊቸ ገበያ!

Gurage proper is big. You post ቡኢ and Sodo related things. That is what you know closely.
ፍቸ ያው ፈታ ከሚለው ቃል ተመሳሳይ ነው:: ጦም ተፈታ ወይም የጦም ፍቸ ነው የሚባለው::
ሞህር የዼንጤና ኦርቶዶክስ ምድር ነው
ቸሃ ካቶሊክ አለ (የአባ ፍራንሲሰ ምድር)
እኖር ሁሉም ሃይማኖት አለ:: መድሃኔአለም አቦ ቤ/ክ ይጠቀሳሉ:: እንደጋኝ ሙሉው ኦርቶዶክስ ነው ዼንጤም በውስኑ አለ::
ጌይታ/ጎማረ እስላም ሳይበዛ አይቀርም ግን ክርስትናም ይኖራል
እዣም ኦርቶዶክስ ይኖራል
እነዚህ ምእራብ ጉራጌ አካባቢዎች ፍቸ የፍቸ ገበያ ይኖራቸዋል:: They have pristine culture relatively away from addis, very peaceful hard working society and proud Ethiopians.

Horus
Senior Member+
Posts: 35334
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ፍቸ ፋሲካ ማለት ነው ፡ ማኛም አሰላንህም!!

Post by Horus » 19 Apr 2025, 01:13

እንደጋኝ የእኔ ፌቨሪት ናቸው፣ ገርልፍሬንድ ነበረችኝ ። አው ፊቸ መፍታት ማለት ነው። ፍትህ የሚባለው የሕግ ቃል መፍታት፣ መፍትሄ ማለት ነው ምክኛቱም ሕግ ወይም ሕግድ (እግድ) የታገደ የታሰረ ማለት ነው ። በክስታኔኛ ኧገድ እሰር ፣ ዎገድ ማሰር ማለት ነው ። በጆካ ሴራ ቅጫ የሚባለ በአማርኛ መቀጫ ፣ መቅጫ የሚባለው ነው ። ቅጫ ወይም ቅጣት ቅጥ የሚለው ቃል እርባታ ነው ። ቅጥ በክስታኔኛ እኩል ማለት ሲሆን ቅጥ ያለው ፣ ቅጥ ያጣ ፣ ትክክል ያልሆነ የተዛባ ማለት ነው ። ቀጥታ የሚለውም የዚያ እርባታ ነው። ስለዚህ ጀስቲስ ቅጥ መሆን ፣ የሁለት ነገሮች እኩል መሆን ነው ። ጉራጌኛ ቋንቋ እንደ ባህር የጠለቀ ነው! ቢገባችሁ!

Post Reply