Page 1 of 1
Re: የሻዕቢያ የእግር ኳስ ቡድን ዛሬም ማንቸስተር ዩናይትድን አሸነፈ። ጓዶች ምን እናድርግ እንደዚህ ዓይነት ትግል ነው የገጠመን!!! ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ
Posted: 14 Apr 2025, 07:19
by Selam/
አሌክስ የሚደነቅ ተጫዋች ነው። period!
ግን እኔ በግሌ በሰው ሃገር ተወልደውና አድገው እዛው ስኬት ላገኙ ኢትዮጵያውያኖች ብዙም ደንታ የለኝም። ከጣሊያን ወይንም ከጀርመን ተሰደው አሜሪካ ስኬታማ እንደሆኑት ሰዎች ማለት ነው። መለኪያዬ ለሃገራቸው ምን አበረከቱ የሚለው እንጂ፣ ለእንግሊዝ ክለብ ስንት ጎል አስገቡ የሚለው አይደለም።
ሆኖም የአፍሪካ ነገር ‘ያለ አንድ የላት ዕንቅልፍ የላት ነውና’ እንግሊዝ ውስጥ በገባው ጎል መንደፈራ ትቀወጣለች፦ ዲሲ በተከፈተው ነዳጅ ማደያ መርካቶ ትፈነድቃለች። ካናዳ ላድ አፈቀርኩሽ ብሎ ለዘፈነው አቀንቃኝ፣ ካዛንቺስ ዳንኪራ ትመታለች።
Re: የሻዕቢያ የእግር ኳስ ቡድን ዛሬም ማንቸስተር ዩናይትድን አሸነፈ። ጓዶች ምን እናድርግ እንደዚህ ዓይነት ትግል ነው የገጠመን!!! ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ
Posted: 14 Apr 2025, 07:49
by Digital Weyane
ሻዕቢያዎች በእስፖርት እና በሙዚቃ አለምን እየተቆጣጠሩ ባሉበት ወቅት ኡኛ የብልፅግና ሃይማኖት ተከታዮች እያየን እንዳላየን እየሰማን እንዳልሰማን ማለፍ ሃይማኖታችንም ሆነ ሕሊናችን የማይፈቅድ በመሆኑ፣ ብሎም በታሪክ የሚያስወቅሰን ስለሆነ ሁላችንን ለሚመለከተው አካል ጩኸታችንን ማሰማት አለብን።