Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6009
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

የኩኖ ኣምላክ የወለደዉ ጎሳ ዬለም፣ ግራኝ የወለደዉ ጎሳ ዬለም፣ ኮለምበስ የወለደዉ ጎሳ ዬለም

Post by Naga Tuma » 11 Apr 2025, 16:29

እኔ ሌሎች ተመራማሪዎች ያሉትን ሰምቼ ሳይሆን ከራሴ ምርምር ተነስቼ ነዉ የተመራመሩት ያሉት የገባኝ።

አማርኛ እንደ ቋንቋ የተወለደዉ የኣፄ የኩኖ ኣምላክ ንግስና ዘመን ነዉ የሚባል ታሪክ ሰምቻለሁ ወይም ኣንብቤኣለሁ።

ኣንድ የትግርኛ ተናጋሪ ኣዛዉንትን ስራ ቦታ በየጠዋቱ ሠላም ሠላም እንባባል የነበረ ኣንድ ቀን ሆነ ብዬ ቡና ልጋብዞት ኣልኳቸዉ። እሺ ብለዉ ቡና እየጠጣን በምን ምክንያት እንደተነሳ ባላስታዉስም ከትግሬ ያልተወለደ አማራ አማራ ኣይዴለም ይባላል ኣሉኝ። የቡና ግብዣ ይህን የምያህል አባባል ገለጸልኝ። ወሎ ዉስጥ ቤተ አማራ የተባለዉ መቼ እንደሆነ ኣላዉቅም።

ይህ ታሪክ ስህተት ካልሆነ አማርኛን መናገር የጀመሩ ከአማርኛ ቋንቋ መወለድ በፊት የነበሩ ጎሳዎች ነበሩ ማለት ነዉ።

ኣዕምሮዬ ይህቺን ዕዉነት ያስተዋለ ቀን ነዉ አማራ ማለት እና አማርኛ ተናጋሪ ማለት ልዩነታቸዉ የገባኝ።

ኣዕምሮዬ ይህቺን ዕዉነት ማስተዋል ያልተጠበቀ ልዩ ጥቅም ነበረዉ። ስለ ጎጠኝነት ማሰላሰል በኣንዴ ተነቅሎ ከኣዕምሮዬ ወጥቶ ኣዕምሮዬ ከዛ ነፃ ሆነ።

የግራኝ መሃመድ ዘመን ከቦረና ተነስቶ ምዕራብ ሸዋ ስለ ደረሰ ሊበን የተባለ ሰዉ ታሪክ ከልጅነት ጀመሮ ስሰማ ያደኩኝ ነዉ።

ይህ ቪድዮ ስለዛ ታሪክ ያስታዉሳል።



ከዛ በፊት በአከባቢዉ በግብርና ይተዳደሩ የነበሩ ጎሳዎች ነበሩ። ከቦረና የመጡትን ገበሬ ነን ቢሏቸዉ ቦረናዎቹ ገበሮ ኣሏቸዉ።

የአከባቢዉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሁለቱን ጎሳዎች የምያዉቃቸዉ ገበሮ እና ቦረና እንደሆኑ ነዉ። ሁለቱም ኦሮምኛን የሚናገሩ፣ አማርኛን ያልረሱ ናቸዉ።

ኦሮሞ የቃሉ መሠረት ኦርመ ወይም ባዕድ የተባለ ቃል ነዉ የሚለዉ ታሪክ ዕዉነት ከሆነ ኦሮምኛ ተናጋሪ ጎሳዎች እንጂ ኦሮሞ የሚባል ጎሳ ዬለም ማለት ነዉ። ቦረና የኦሮሞ አባት ነዉ ከተባለ ከቦረና ያልተወለደ ኦሮሞ ኦሮሞ ኣይዴለምን ያመጣል። በተጨማሪ ቦረን ሰገል፣ ገበሮ ሰገልተመ የሚባል አባባል ኣለ። ቦረና ዘጠኝ ናቸዉ፣ ገበሮ ዘጠና ናቸዉ እንደማለት ነዉ።

የኩኖ ኣምላክ ዘመን ባህሌን ብለዉ ከሸዋ ወደ ቦረና የተሰደዱ ነበሩ የሚል አፈ ታሪክም ኣለ።

ኦሮምኛ ተናጋሪ እንጂ ኦሮሞ የሚባል ጎሳ ዬለም ከተባለ ይህም ኣዕምሮን ነፃ የምያደርግ ዕዉነት እና ዕዉቀት ነዉ።

ይህ ሁላችንንም የተለያየ ቋንቋዎችን የምንናገር የኢትዮጵያ ዜጎች ያደርገናል።

ይህ ማለት አሜሪካዊነት ዜግነት እንጂ አሜሪካዊ የሚባል ጎሳ ዬለም እንደማለት ነዉ። ኮለምበስ የወለደዉ ጎሳ ዬለም።

አሜሪካዊ ነን የሚሉትን የጎሳቸዉን መሠረቶች ማጥናት የሚፈልግ ብዙ ማጥናት ይችላል። ከኢትዮጵያ መጥተዉ አሜሪካዊ ነን የሚሉትን ጨምሮ።

ኣንድ ግዜ መሠረቱ ኢትዮጵያ የሆነ ሰዉ ስራ ቦታ እኔ ጋ መጥቶ የሃገሬ ሰዉ ሲለኝ ሂድ እና ሃገርህን ፈልግ ኣልኩት። በቅጽበት ኣይ ኣም ኣን አሜሪካን፣ ዋት ዱ ዩ ሚን ኣለኝ። ኣይቼዉ ዝም ኣልኩኝ።

የሳይኮሎጂ ነገር። ሃገር ጠንካራ ናት ሲባል ዜግነት ያምረዋል። ሃገር ደካማ ናት ሲባል የሌላ ሃገር ዜግነት ያምረዋል።

ያልተመራመረ ወይም የደነቆረ ጉዞ ዉጣ ዉረድ ኣለዉን መስማት ይቸግረዋል።

የኩኖ ኣምላክ፣ ግራኝ፣ ኮለምበስ የሰዉ ልጅ ታሪካዊ ጉዞ ዉስጥ የተከሰቱ ሰዎች ናቸዉ። ይሁን እንጂ በየኩኖ ኣምላክ ዘመን፣ በግራኝ ዘመን፣ በኮለምበስ ዘመን የተወለደ የሰዉ ጎሳ ኣንድም ዬለም።

ይህ ማለት ሰዎቹ ዝርያ ኣልነበራቸዉም ማለት ሰይሆን በእነሱ ዘመን ይኖሩ የነበሩት ጎሳዎች የሰዎቹ ዉጤቶች ኣይዴሉም ለማለት ነዉ።

ይህ ዕዉነት ኣይዴለም? ከሆነ ምን ዐይናት ኣዕምሮ ነዉ ማስተዋል የሚሳነዉ?

ሳይንሳዊ አስተሳሰብ ኢትዮጵያ ዉስጥ ስር እየሰደደ ባለበት ዘመን፣ ሁለተኛ ሬይነሳንስ ተብሎ ዓመታት ከተቆጠሩ በኋላ ኢትዮጵያ ዉስጥ የማይደረመስ ድንቁርና ኣይኑር። የድንቁርና ድርምስ ላይ ኢትዮጵያ ሁሉንም ዜጎችዋን በዕኩልነት ሀርሞኒ ኣሰባስባ ትለምልም።