Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Selam/
- Senior Member
- Posts: 15035
- Joined: 04 Aug 2018, 13:15
Post
by Selam/ » 09 Apr 2025, 07:04
ፒፒ በትግራይ ላይ፣ አሁንም ቀለደ
ሹመት እንደ ሂሳብ፤ እያወራረደ
ታደሰ ወረደ፣ ለስልጣን ሻፈደ
ሕወአትን ይዞ፣ ለዓብዮት ሰገደ
ደፂ ደቃቃው ግን፣ እንደ ጉድ አበደ
-
Misraq
- Senior Member
- Posts: 14981
- Joined: 27 Sep 2009, 19:43
- Location: Zemunda
Post
by Misraq » 09 Apr 2025, 08:18
ጌታቸው ሰገደ : ከስልጣን ወረደ
ተተኪውም መጣ : ታደሰ ወረደ
ሲወርድ ምን እንበለው : አብይ ክላ ሲለው
እምበር ተጋዳላይ : በቃ ዋጋም የለው
-
Selam/
- Senior Member
- Posts: 15035
- Joined: 04 Aug 2018, 13:15
Post
by Selam/ » 09 Apr 2025, 08:46
ታደሰ ወረደ፣ ከጦር በረገገ
አቅጣጫ ቀይሮ፣ በስልጣን አደገ
የምስኪኑን ትግራይ፣ መብት እየነፈገ
-
Meleket
- Member
- Posts: 4350
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 09 Apr 2025, 09:38
በግጥም ለመዝናናት ያህል ብቻ ነው
ታደሰ ኣልወረደም፡ ወጣ እንጂ ታደሰ፡
ለመውረድ አይደለም ናቅፋ የደረሰ።
ጌቾ ጎበዝ ነበር ባፉ ጤፍ ይቆላል፡
ከነ ኣብርሃም ጋራ ሚሆነው ይታያል።
ደብረጽዮንም ቢሆን ግርፍ ነው የናቅፋ፡
ንቁ ነው ሁልጊዜ ቢመስል ያንቀላፋ፡
ህልክ/እልህ ይዞት እንጂ ማን ማንን ሊያጠፋ።
ሕወሓት ልብ ኣርጎ ለሰላም ከለፋ፡
ወደብ ተመኚ ሁላ ባፍጢሙ ተደፋ።
ልብ ካላረገ ሕወሓት ካልተማረ፡
ወይ ካልተቀነሰ ወይ ካልተደመረ፡
ጨዋታው ሲጀመር ያንን ሁሉ ህይወት ለምንድን ገበረ?
ለዘብዘብ ብሎ እስካላከረረ፡
ሌላ ኣማራጭ ኣለው ያልተሞካከረ፡
ድንበሩን በቅጡ እያሰማመረ፡
ሄግን ተቀብሎ በሰላም በኖረ፡
ወደብ ተመኞቹን እያኮማተረ።
-
Odie
- Member
- Posts: 3809
- Joined: 24 Jun 2024, 23:07
Post
by Odie » 09 Apr 2025, 09:44
ጀነራል ወረደ
ስልጣን ስለወደደ
ወደ አዘቅት ወረደ
እንደተገፈተረ እየተንገዳገደ
ገንፎ እየዛቀ ብልኮ እያጣፋ ለዋቀ እየስገደ
ትግሬን እያሻሻጠ በዘር እየነገደ
መመለሻ የለውም እንዲህ ሲልከስከስ
የጌተቸው በጉ እጣ እስኪደርስው ድረስ

-
Meleket
- Member
- Posts: 4350
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 09 Apr 2025, 09:48
“ይደገም ይደገም” የሚለውን ድምጽ ስለሰማን ነው! ለመድገም ያህል ነው።
Meleket wrote: ↑09 Apr 2025, 09:38
በግጥም ለመዝናናት ያህል ብቻ ነው
ታደሰ ኣልወረደም፡ ወጣ እንጂ ታደሰ፡
ለመውረድ አይደለም ናቅፋ የደረሰ።
ጌቾ ጎበዝ ነበር ባፉ ጤፍ ይቆላል፡
ከነ ኣብርሃም ጋራ ሚሆነው ይታያል።
ደብረጽዮንም ቢሆን ግርፍ ነው የናቅፋ፡
ንቁ ነው ሁልጊዜ ቢመስል ያንቀላፋ፡
ህልክ/እልህ ይዞት እንጂ ማን ማንን ሊያጠፋ።
ሕወሓት ልብ ኣርጎ ለሰላም ከለፋ፡
ወደብ ተመኚ ሁላ ባፍጢሙ ተደፋ።
ልብ ካላረገ ሕወሓት ካልተማረ፡
ወይ ካልተቀነሰ ወይ ካልተደመረ፡
ጨዋታው ሲጀመር ያንን ሁሉ ህይወት ለምንድን ገበረ?
ለዘብዘብ ብሎ እስካላከረረ፡
ሌላ ኣማራጭ ኣለው ያልተሞካከረ፡
ድንበሩን በቅጡ እያሰማመረ፡
ሄግን ተቀብሎ በሰላም በኖረ፡
ወደብ ተመኞቹን እያኮማተረ።
-
Abere
- Senior Member
- Posts: 13624
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Post
by Abere » 09 Apr 2025, 10:57
የአስካሪ ልጅ መለስ ጉድህን አላየህ!
ኦሮሙማ ፓፓ ወርቅህ ተጋሩ ላይ አስቀመጠብህ፤
1 አመት ረዳን ሌላ አመት ወረደ እየቀያየረ፤
ትግሬ ለኦሮሙማ በደንብ ገበረ።
ጫማ ጉልበት ስሞ እየተማለደ፤
ይኖራል ተጋሩህ እየተናደደ -እየተዋረደ።
የአባት ስራ ለልጅ አይደርስም መስሎህ፤
ስንቱን በበደኖ ስንቱን በወልቃይት አንተ አሳርደህ፤
ቀን ቆጥሮ ቀን ቆጥሮ ያበላኸው ኦነግ ተቀመጠብህ።
-
Dama
- Member
- Posts: 4278
- Joined: 22 Jun 2024, 21:05
Post
by Dama » 09 Apr 2025, 12:33
Abiy was not transparent in declaring General Tadese as President of Tigrey.
He was supposed to get the number of email votes the general received. And who was the second highest nominations obtainer? And thd 3rd nominee?
-
Misraq
- Senior Member
- Posts: 14981
- Joined: 27 Sep 2009, 19:43
- Location: Zemunda
Post
by Misraq » 09 Apr 2025, 13:15
.
.
.
የበሻሻው ሌባ : ተጫወተባቸው
ስኳር እያላሰ : እያስጨፈራቸው
የለመለመ ሳር : በእጁ እያሳያቸው
ጠራቸው ነዳቸው: ገደል ከተታቸው
ከዛም እየሳቀ : ተረቱን ተረተባቸው
-
Meleket
- Member
- Posts: 4350
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 10 Apr 2025, 04:40
ወንድማችን ኣበረን በግጥም ለማዝናናት ያህል ብቻ ነው!
መለስስ ቆቅ ነበር በናቱ የወጣ፡
የማንንም ጨቋኝ ማንንም ፈጣጣ፡
በምላስ ጠራርቦ ኣይቀጡ እዬቀጣ፡
ስንቱን ጭቁን ዜጋ የተባለ ጦጣ፡
መብቱን ኣጉናጽፎ ስልጣን ላይ ያስወጣ።
መለስስ ብልህ ነው ባባቱም የወጣ፡
በትግሬም በጦቢያም ልማትን ያመጣ፡
ለማዬት የጣረ ጦብያ ተለዉጣ፡
ኣባይን ገዳድቦ፡ ያገሩን ባላንጣ፡
መሬት ላይ ዘርሮ ጠሃይ ላይ ያሰጣ።
የመለስ ችግሩ እልህ ውስጥ መግባቱ፡
‘ኤርትራን’ ሊቀጣ ከልቡ መትጋቱ፡
የኤርትራ ግመሎች ጨዉን እንዲጋቱ፡
ዓሰብን ጠላልቶ አጕል ሟሟረቱ፡
ኤርትራን ለመጉዳት ጅቡቲ ማለቱ፡
ያይን ቀለም ብሎ ጥላቻ ማስላቱ፡
አማራን ጨቋቁኖ ትግሬን “ማጎልበቱ”።
የመለስ ችግሩ ሻዕብያን መዳፈር፡
የኤርትራን ድንበር፡ ፍርድ ኣለመተግበር።
ሕወሓት ወያኔ ከታሪክ ተምሮ፡
መኖር ከጀመረ ኤርትራን ኣፍቅሮ፡
የሄግን ብያኔ በቅጡ ኣክብሮ፡
ደምበር አሰማምሮ፡
የወደብ ሕልመኛ ካላባ ጠምባሮ፡
ከበሻሻም ቢሆን ያዉም ከኣጋሮ፡
ከኣዋሽም ቢሆን ካኮቦና ባሮ፡
ለመኖር የሚሻ ፈጥሮ ኣምባጓሮ፡
ፍጻሜው ይሆናል የፋሲካ ዶሮ።
Abere wrote: ↑09 Apr 2025, 10:57
የአስካሪ ልጅ መለስ ...