
ከ3 ሳምንት በኋላ
ኢትዮጵያ የባህል ዕሴቿን እና ኪናዊ ፀጋዎቿን ለብሪክስ አባል ሀገራት ልታስተዋውቅ ነው
#Ethiopia | “የኢትዮጵያ የባህል ድልድይ ህዝብ ለህዝብ ትስስር” በሚል መሪ ቃል ኢትዩጵያ ላይ ያሉ ቱባ ባህላዊ ዕሴቶችን፣ ኪናዊ ፀጋዎችን እንዲሁም የፈጠራ ምርቶችን በመጠቀም ከኢትዩጵያ ከተለያዩ አካባቢዎች በተውጣጡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለብሪክስ አባል ሀገራት ለማቅረብ ዝግጅት ጀምራለች፡፡
ኢትዩጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በዲፕሎማሲው መስክ ከምትሰራቸው ስራዎች አንዱ የባህልና የኪነ ጥበብ ዲፕሎማሲ እንደመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዚህ ልክ አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡
ይህንን ዝግጂት ለማቅረብም የሚያስችል የውል ስምምነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሻኩራ ፕሮዳክሽን ጋር ተፈራርሟል:: ከዚህ በተጨማሪም ለሻኩራ ፕሮዳክሽን ባለቤት አቶ ካሙዙ ካሣ ለኪነ ጥበብ ላበረከቱት አስተዋፅኦ የ2000 ካሬ ሜትር ቦታ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ
Ministry of Culture & Sport-Ethiopia

