Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6030
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ሳይንስ እና ኮምፒዩተር

Post by Naga Tuma » 03 Apr 2025, 18:59

ሳይንስ ሲባል በተለይ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከባድ ጽንሰ ሀሳብ ይመስላል። ምናልባትም ቃሉ ከዉጪ ተዉሶ ስለሆነ ነዉ።

የተረጋገጠ ወይም ማረጋገጥ የሚቻል ዕዉቀት ነዉ ቢባል የበለጠ ሊገባ ይችላል።

ኪነሊቅ የተለመደ ህብረቃላት ነበር። በእንግሊዘኛ ኖዉሌጅ የተለመደ ቃል ነዉ።

የእንግሊዘኛ ኣንዱ የሳይንስ ገለጻ ወይም ዴፍኒሽን የተጠና ዕዉቀት ነዉ ይላል።

ስለዚህ የተማሩት ሳይሆን መማር የሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን ሳይንስ ስለ ዕዉቀት መሆኑን በደንብ ቢገነዘቡ ለሳይንስ ጠንካራ ዝንባሌ ይኖራቸዋል ብዬ እገምታለሁ።

ኮምፒዩተር አጀማማሩ ምናኝ ሜካኒካል ወይም ግጥምጥም ነዉ። ግጥምጥም እንደ አገጣጠሙ ነዉ የሚንቀሳቀሰዉ። ከአገጣጠሙ ዉጪ ኣይንቀሳቀስም።

ግጥምጥሙ በፍጥነት መንቀሳቀስ ቢችልም ዞሮ ዞሮ ግጥምጥም ነዉ።

እንደ ሰዉ ኣዕምሮ ዕዉቀትን ኣጥንቶ ግጥምጥሙ ዉስጥ የተረሳ ዕዉቀት ኣለ ብሎ ኣያስብም።

ኣንድ ግዜ ስራ ጀምሬ ብዙም ሳልቆይ ይኖራል ብዬ የገመትኩትኝን አሰራር እንድያሳየኝ ኣንዱን የመስርያ ቤቱን ባልደረባ ጠየኩኝ።

መነጋገር ጀምረን ብዙም ሳልቆይ ጥያቄዬን ኣለማጤኑን እና ይኖራል ብዬ የገመትኩኝ አሰራር እንደሌላቸዉ ገባኝ።

ከሠራተኛዉ ጋር መነጋገራችንን ጨርሰን በጣም ተገርሜ ለብቻዬ ስራመድ ዚስ ፕሌስ ሃዝ ኤ ፕሮብሌም ኣልኩኝ። ይህን ለራሴ ያጉረመረምኩኝ ቦታዉ ሁሌ ከፊቴ ኣይጠፋም።

የጠበኩት አሰራር ኣለመኖሩ ብቻ ሳይሆን ያንን ሳይንሳዊ አሰራር ሳይኖራቸዉ ስራዉን እንዴት መስራት እንደቻሉ ገረመኝ።

ስራዉ የቢልዮኖች ዶላር ኢኮኖሚን የሚደግፍ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ያካተተ ነዉ።

ለፕሮጀክቶቹ የፕላን ጥናት ግዙፍ የኮምፒዩተር ሞዴል ተሰርቶለታል።

ይህ የኮምፒዩተር ሞዴል ዉሃን የሚሊሊትር ጠብታ ይሁን ኣንድ ሚልየን ሊትር ቁጠር ካልከዉ ከላይ እስከ ታች በትክክል ይቆጥርልሃል።

ይህን ማድረግ በመቻሉ ያወድሱት ነበር።

ዉሃን ጨምሮ የፈሳሽ አለካክ ሳይንስ ኣንድ መሠረታዊ ሀሳብ ኣላካተትም። የሰዉ ኣዕምሮ ኣስቦ እስታዉሶ ካላካተተዉ የኮምፒዩተር ሞዴል ግዙፍም ቢሆን ይህን ሳይንስ ረስተሃል እና ጨምርበት ብሎ ኣይመክርም።

ሳይንሱ በጣም ቀላል ነዉ። ፈሳሽን ለመመጠን ጋን ወይም ኮንትሮል ቮልዩምን ተጠቅምህ ጋኑ ዉስጥ ምን ያህል እንደ ነበር፣ ምን ያህል እንደ ተጨመረበት፣ እና ምን ያህል ከዉስጡ እንደተጨለፈ ማወቅ ያስፈልጋል ነዉ።

በቀላሉ ከገባ ብዬ ነዉ እንዲህ የጻፍኩኝ።

የሳይንሱ ጽንሰ ሀሳብ መሠረቱ ኒዉተን ነዉ። እኔ ኢትዮጵያ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ሆኜ የወሰድኩኝ ኮርስ ዉስጥ ነዉ የተማርኩኝ። ኮርሱን ያስተማረዉ ኢትዮጵያዊ ነዉ።

እኔም ኢትዮጵያም፣ አሜሪካም የግራጁዌት ተማሪ ረዳት ሆኜ ለጥቂት ዓመታት ተመሳሳይ ኮርሶችን ኣስተምሬኣለሁ።

ስራዉ ቦታ የጠበኩት አሰራር ኣለመኖሩ ሰሮቶ ማሳየቱን እንደ ዕድል ነዉ ያየሁት።

ስራዉን እየሰራን ኣንድ ግዜ የኮምፒዩተር ሞዴሉ ተጠቃሚ የግል አማካሪ ጥያቄ ይዞ መስርያ ቤቱ መጣ።

እሱ ይመልስልሃል ተብሎ ወደ እኔ ተላከ።

እኔ ጋ መጥቶ ጥያቄዉን ጠየቀኝ። ጥያቄዉ ገብቶኝ ይህን ጥያቄ የሚመልስ ስራ እየሰራሁኝ ነዉ ኣልኩት።

መልሴን ሰምቶ ሞዴሉን መታዘቡን ፊቱ ላይ እየየሁ ተነስቶ ሄደ።

ሞዴሉን ለማሻሻል ግዙፍ ኮንትራት ተሰጥቶ ግዙፍ ስራ ተሰራ። ሳይንስ ዝንፍ እንደማይል ተራ በተራ ያሳየ ስራ ነበር።

ኣንድ ነገረኛ ኣማካሪ ስራ መቼ ዝንፍ ማለት እንደጀመረ ግራፍ እየተሰራ ያሳይ ነበር። የስራ ሀላፊነት መዉሰድ እና ስራ ዝንፍ ማለት መጀመር የራሱን ታሪክ ይናገራል።

እኔ ያስፈልጋል ያልኩኝ ሳይንስ ስራዉ ዉስጥ እንዲካተት መልሼ መላልሼ ብመክር የሚጓተት ሆነ።

ኣይቼ ኣይቼ በኋላ ስራዉን በግሌ ባለኝ ግዜ ቤቴ ሰርቼ ኣንድ የሳይንስ መጽሔት ዉስጥ እንዲታተም ላኩኝ።

ተቀባይነት ኣግኝቶ ታተመ። ኣንድ የማላዉቀዉ ፕሮፌሰር ስራዉን ኣድንቆ ይታተም ማለት እንጂ ምንም አስተያየት ኣልጨመረበትም። ፒር ሪቪዉ ዉስጥ ይህን ዐይነት መልስ መስማት ኣርኪ ነዉ።

መስርያ ቤቱ ዉስጥ በችሎታዉ የተከበረ ሰዉ በሌላ ነገረኛ የታተመዉን ወረቀቴን እንዴት ኣየሀዉ ተብሎ ኣንድ ግዜ ተጠየቀ።

ተነባቢነትን ማግኘት የሚችል መልካም ስራ ነዉ በማለት መልሶ ሳያሳትም በፊት ስራዉን ብያሳየን በጎ ነበር የሚል ሀሳብ ጨመረበት።

ስንት የለፋሁባቸዉን ስራዎች ተራ በተራ እየተነጠኩ ታግሼ፣ ይህን ስራ ማካተት ያስፈልጋ ብዬ ስመክር ሰንብቼ፣ ሰልችቶኝ በግሌ ሰርቼ ለህትመት የበቃ ስራን ቀድሞ ብያሳየን በጎ ነበር የሚል ሀሳብ ተሰማ።

ስራ ጀምሬ ወራት ሳልቆይ ጥያቄ ጠይቄ መልስ ስላላገኘሁ ዚስ ፕሌስ ሃዝ ኤ ፕሮብሌም ያስባለኝን ሙጭጭ ብዬ ቁልጭ ኣድርጌ ኣሳየሁ። የታተመዉ ሳይንሳዊ ስራ የማይፋቅ ነዉ።

የለፋሁባቸዉን ስራዎቼን ያለምንም ይሉኝታ ተራ በተራ ኣስረክብ መባሉን ማስታወስ ኣልሻም። የምያስታዉሰኝን ኣልሻም። ያንገሸግሸኛል።

በመስራያ ቤቱ በችሎታዉ የተከበረ ሰዉ ይህ መሠረታዊ የሆነ ሳይንሳዊ ሀሳብ እንዴት እንዳልመጣለት እንቆቅልሽ ሆኖብኝ ነበር።

በኋላ የመጀመርያ ድግሪዉን የተማረዉ በሌላ ሙያ ነዉ የሚል ወሬ ሰማሁ። ወሬዉ ትክክል ይሁን ኣይሁን ኣላዉቅም። ወሬዉ ትክክል ከሆነ ለእንቆቅልሹ መልስ ይሆንልኛል።

ወደ እኔ ተልኮ መልስ ሳያገኝ የተመለሰን ሰዉ ያሳተምኩትን ወረቀት አድራሻዉን ፈልጌ ልልክለት ኣስቤ ኣልተሳካልኝም።

ይህ የስራ ልምድ በርካታ ነገሮችን የምያመለክት ይመስለኛል።

ኣንደኛ ኮምፒዩተር ግጥምጥሞሽ ስለሆነ ሳይንሳዊ ጽንሰ ሀሳብ ከተረሳ ይህ ተረስቷል ብሎ ኣይመክርም።

ሁለተኛ በኣፄ ሀይለ ሥላሴ ግዜ የተጀመረ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት መሠረት እና መስመር ይዞ የነበረ መሆኑን ያመለክታል።

ሶስተኛ ኣንድ የሳይንስ ጽንሰ ሀሳብ ብቻ የቢልዮኖች ዶላር ኢኮኖሚን ዕቅድ የምያቀላጥፍ መሆኑን ያመለክታል።

አራተኛ የሰዉ ኣዕምሮ ሳይንሳዊ ጽንሰ ሀሳብን ተምሮ እና ኣስተዉሎ ካላስታወሰ ጽንሰ ሀሳቡ በራሱ ተነስቶ ዘሎ የማንም ኣዕምሮ ዉስጥ የማይገባ መሆኑን ያመለክታል።

ሳይንስን የማስተማር እና የመማር ኣስፈላጊነት ለዚህ ነዉ።

ኮምፒዩተር በጣም ቀልጣፋ የሆነ ማሸን ቢሆንም በሰዉ ኣዕምሮ ከታዘዘዉ መስመር ወጥቶ የሳይንስ ጽንሰ ሀሳብ የሚፈጥር ወይም ከተረሳ የምያስታዉስ ኣይዴለም።