Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12876
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Shocking: የዓብይ አህመድ የተጭበረበረ የትምህርት ዶክመንት ወደ ሕጋዊ መስመር እንዲገባ ሊደረግ ነው

Post by Thomas H » 25 Mar 2025, 21:41

Meseret Media

·
በርካታ የፖለቲካ አመራሮች ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ስላላቸው ዶክመንቶችን የመለየት ሂደት እክል ገጥሞታል ተባለ
- 460 ሺህ ፎርጂድ የትምህርት ዶክመንት ወደ ህጋዊ መስመር እንዲገባ ሊደረግ መሆኑ ተጠቁሟል
(መሠረት ሚድያ)- ሕገወጥ እና ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ መስፋፋቱን ተከትሎ በመንግሥት የተወሰዱ እና እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ችግሩን ከመቅረፍ ይልቅ መመርያ በማውጣት ሀሰተኛ ትምህርት ያላቸውን ህጋዊ በማድረጉ ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን ምንጮች ተናገሩ።

460 ሺህ ፎርጂድ የትምህርት ዶክመንት ያላቸው ግለሰቦች ሰነዶቻቸው ህጋዊ ወደማድረጉ እየተሄደ መሆኑም ታውቋል።
በመመርያ 990/2016 መሰረት እንዲሁም በኢቲቪ አማካኝነት መስከረም 2016 ዓ/ም ላይ 500 ሺህ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ያላቸው ግለሰቦች እንዳሉ ለህዝብ መነገሩ ይታወሳል።

ይሁንና የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከቀናት በፊት 'እውነት ወይስ ሀሰት?' በሚል በተደረገ አንድ ውይይት ላይ ለቀረበላቸው የሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን የተመለከተ ጥያቄ ሲመልሱ ተጣርቶ የተገኘው 40 ሺህ መሆኑን መግለፃቸው ታውቋል።

"ይህ ማለት ከ500 ሺህ ውስጥ 460 ሺህ ፎርጅድ ወይም የተጭበረበረ ትምህርት ህጋዊ እየተደረገ ነው ማለት ነው" በማለት ጉዳዩን ለአመታት ሲከታተሉ የነበሩ እና ለመንግስትም ጥቆማ ሲሰጡ የነበሩ አንድ ግለሰብ ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።
"በየግዜው የሀሰተኛ ትምህርት ማስረጃን የማጣራት ጉዳይ እየተጀመረ ይቋረጣል፣ በመንግስት መዋቅር ውስጥ በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ወደ ስልጣን የመጡ የስራ ሃላፊዎች እና ያለሙያቸው ሙያተኛ የሆኑ ሰራተኞች እስካልተወገዱ ድረስ በሀገራችን የሚስተዋለው የሌብነትና የመልካም አስተዳደር ችግር ይቀረፋል ብሎ ማመን አስቸጋሪ ነው" የሚሉት ግለሰቡ ይህን ሀላፊነት በዋናነት መውሰድ የሚገባው የትምህርት ሚኒስቴር እንኳን የሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን ማጣራት ሲገባው በተለያየ ጊዜ መመርያዎችን በማውጣት ፎርጅድን ህጋዊ ማድረጉን ተያይዞታል ብለዋል።

የካቲት 2016 ዓ/ም ላይ የወጣው መመርያ የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ 1152/2011 ባወጣው አዋጅ ላይ በአንቀጽ 40 መሰረት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ሙሉ በሙሉ ጥሰው ሰርተፍኬት ያገኙትን ህጋዊ ያደርጋል ያሉን ሌላ የሚኒስቴር ቢሮው ምንጫችን ደግሞ አዋጁን ለማስፈጸም የወጣውን መመርያ 5/2004 ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ያመጣውን ሳይከተሉ የተማሩትን ህጋዊ ያደርጋል ብለዋል።
"የከፍተኛ ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በጣም እየተበራከተ መምጣቱን ከቁጥራዊ መረጃ ጋር አያይዞ ለህዝብ ሲገልጽ ቢቆይም በፖለቲካ ውሳኔ በተቋሙ የተጣሩትን ሀሰተኛ ትምህርት ማስረጃ በአሁኑ ሰዓት ህጋዊ ተደርገዋል" ያሉት ስሜ አይጠቀስ ያሉት ምንጫችን ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጣራቱን ስራ የሚሰራው አካል በፖለቲከኞች ጣልቃ ገብነት ስራውን መስራት ካልቻለ የማጣራት ሂደቱን አስቸጋሪ ያረገዋል ብለዋል።
"ይህን የምለው ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ጭምር ሀሰተኛ ትምህርት እንዳላቸው ፀሀይ የሞቀው ሀቅ በመሆኑ ነው" በማለት ጉዳዩን አብራርተዋል።
የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ከ1995 ጀምሮ እስከ 2014 ዓ.ም መረጃቸውን ለተቋሙ ካስገቡ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እስካሁን ከተመረቁ 1.1 ሚሊየን ተማሪዎች መካከል ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የያዙ መሆናቸውን ይፋ አድርጎ ነበር።
መረጃን ከመሠረት!