Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12265
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

ወይ አረት ኪሎ፣ ወይ ሰፈር ወይ፣ ከተማም እንደ ሰዉ ይናፍቃል ወይ

Post by DefendTheTruth » 23 Mar 2025, 15:24

አዲስ አበባ ዉስጥ ለተወሰኑ ጊዜያት ኖሬያለሁ፣ የተለያዩ ሰፈሮች፣ ከነዚህ ዉስጥ ይበልጡን ደገሞ አረት ኪሎ ነበር፣ ለአረት አመት፣ ተማሪ ሆኜ፣ የዶርም ኑሮ ብሆንም።

አረት ኪሎ ስባል፣ ሀዉልቱ፣ ሳይንስ ፋከልቲዉ፣ ትምህርት ምንስቲር (ጠማመዉ) ሕንፃ፣ ቅድስት ስላሴ፣ ቅድስት ማሪያምን፣ ሁለቱ የጀርመን ከልቸራል መንታ ሕንፃዎች፣ ጆሊ ባር፣ ሌሎቹ ባሮች፣ ሚንልክ ትምህርት ቤት፣ ዘዉዲቱ ሆቴል፣ እና ሌሎችም ቦታዎች ልክ ትናንት አዛ እንደ ነበርኩ ትዝ ይሉኛል። አሁን ሁሉም ተቀይሮዋል፣ አረት ኪሎም ተለዉጣለች፣ እዛም ብሄድ እንግዳ መሆኔ ነዉ፣ ሁሉም ተለዉጦብኛል፣ አገሬ ተለዉጦዋል። ለዚህ ነዉ አገሩ ነፈቃኝ ያልኩት።


DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 12265
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ወይ አረት ኪሎ፣ ወይ ሰፈር ወይ፣ ከተማም እንደ ሰዉ ይናፍቃል ወይ

Post by DefendTheTruth » 23 Mar 2025, 15:31

ባንዳ ና የባንዳ ልጆች የአገርን እድገት በፖለቲካ አሳቦ፣ ስኮንኑት ዉሎ ያድራሉ፣ ያብጠለጥሉታል፣ ያጥላሉታል። የሕዝብ ጥቅምን ይቃወማሉ፣ ከባንዳ ሌላ ምን ይጥበቃል፣ ድሮስ ብሆን?

ባንዳ ነበር፣ አሁንም አለ፣ ለወደ ፊትም ይኖራል። ዋናዉ ቁም ነገር ግን የባንዳ መኖር ሳይሆን ልያስጨንቀዉ የምገባዉ፣ ጭንቀት የምመጠዉ አርበኛ ባይኖር ነበር። ኢትዮጵያ ሀገሬ ብዙ አርበኞች አሉዋት፣ ተስፋ አላት፣ ጭንቀት የለባትም። ባንዳዉ ይጨነቅ!

Abere
Senior Member
Posts: 13634
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ወይ አረት ኪሎ፣ ወይ ሰፈር ወይ፣ ከተማም እንደ ሰዉ ይናፍቃል ወይ

Post by Abere » 23 Mar 2025, 16:02

በዚህ ክረምት camp ለመውጣት አስቤያለሁ። Amazon Rainforest ሽርሽር። የዝናቡን፤ የወፎቹን ዝማሬ፤ ንጹህ ንፋስ። የኮሪደር ልማት ድንኳን Walmart or Amazon ለመግዛት እፈልጋለሁ። የኮሪደር ድንኳኑ ብርሃን የሚያስገባ፤ ብልጭልጭ፤ በቀላሉ ተዘርግቶ በቀላሉ የሚነቀል። እንደ 4 ኪሎ ወይም ፒያሳ ኮሪደር የቀለለ።የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ልምድ ያላችሁ ሃሳብ ብታካፍሉን :mrgreen:

Is this ኮሪደር ልማት tent great? If you like it I will call it "አቤቤ tent" :mrgreen:

https://www.nytimes.com/wirecutter/revi ... r-camping/


Post Reply