Hamza Oromo from FaceBook shared this joke on Megbey's story
እዚህ ጋር አንድ ብዙ ጊዜ የሚወራ ቀልድ ትዝ አለኝ……
ኃይሌ ገብረስላሴ ጠዋት ለትሬኒንግ በሄደበት አንድ ጎረምሳ ቤቱ ሰተት ብሎ ይገባል። ኃይሌም ወደ ቤቱ ሲመለስ ጎረምሳዉ እግሬ አዉጪኝ ብሎ ይፈረጥጣል ኃይሌም ጎረምሳዉን መንደር ለመንደር ቢያሯሩጠዉም ሊደርስበት አልቻለም። ኃይሌም ደክሞት ቆመ አለና……… "አዉቄሃለዉ ቀነኒሳ ነክ" ብሎት ተመለሰ።
ያዉ ከቀነኒሳ ዉጭ ሌላ ሰዉ በሩጫ አይቀድመኝም ነዉ ነገሩ
