.
.
ጥሌና አበረችም ደንግጠው ጠፍተዋል


The ball is O-PP developed corridor
ይሄን ውሃ ማን አስጮኸው ቢሉ ውስጡ ያለው ድንጋይ አሉ?! ምቱ ሃይለኛ ነው። የፋኖ በትር የሚቻል አልሆነም። አራት ኪሎን ነዝሮታል። የብልጽግና መንደር ዜማው ተቀይሯል። ከከበሮ ድለቃ ወደ ደረት መድቃት እየተቀየረ ነው። በእርግጥም የዛሬው የመከላከያ መግለጫ ቅኔ ነው። የጣር ድምጽም ይመስላል። ድረሱልኝ እንደማለትም መውሰድ ይቻላል። ዘመቻ - አንድነት በሶስተኛ ቀኑ ጂኒውን እያስጓራው ነው። ስንት ጊዜ ጮሆ ከአራት ኪሎ ይወጣ ይሆን? አብይ አህመድ አስር ጊዜ ''አራት ኪሎ እንመጣለን እያላችሁ'' እያለ የሚደነብረው ለምን እንደሆነ ይገባናል። የፋኖን አቅም ለማሳነስ የሄደበት ርቀት አላዋጣውም። አራት ክላሽ ይዘው እያለ ተዘባበተ። ቆመህ ጠብቀኝ ይዞ አራት ኪሎ የለም ብሎም አላገጠ። ድም ድም የሚለው የፋኖ ኮቴ ግን ወደ አራት ኪሎ ቀረበ እንጂ አልጠፋም።
ዛሬ የመጨረሻ ሙከራውን አድርጓል። በፋኖ ተደቆስኩ ላለማለት ''ጄነራል ምግበይ'' ን እንደገጸባህሪ ከፊት አምጥቶታል። ዘመቻ - አንድነት በሶስተኛው ቀን የብልጽግናውን መንደር እንዲህ ሲያዝረከርክ ማየት ትልቅ እፎይታን ይሰጣል፡ ትልቅ ተስፋን በልብ ያስቀምጣል። ዘመቻው ከቀጠለ የመከላከያ ሰራዊት መግለጫ የሚሆነው '' የጽንፈኛውን ሃይል ያሰማራው ጄነራል አብድል ማጂድ ሳቅር ነው። የዚህ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነው የግብጽ ጄነራል ጽንፈኛው ......''
እያመመው መጣ። በእርግጥም ምቱ ዜማውን እየቀያየረው ነው። ከአራት ኪሎ የሚሰማው ማንቋረር ከሰሞኑ ይጨምራል። ገና ምኑ ተነካና?! ቆንጆዎቹ እየመጡ ነው። ሙሽራው ደርሷል። ጎበዞች ዘይቱን አዘጋጅተዋል። ሰነፋሞቹ ግን ወየውላችሁ - እንዲል ቅዱስ መጽሀፉ።