Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Abere
- Senior Member
- Posts: 13633
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Post
by Abere » 21 Mar 2025, 08:42
The Weight of Words: Existential vs. Access - >The Lyrics is About Ownership of Assab
Wondering a dozen Eritrea trolls fussing about the distinction between "Access" and "Ownership". And the only take I have from them is their prayers have been the lighter of the two. Access is just an ordinary term which one needs not always out of necessity but optional need. If access has been an issue Ethiopia has a dozen options - it is not about that. It is about ownership of Assab. Denying ownership means an existential threat, where Ethiopia has no option other than taking over it by force. Leaving aside the capacity and willingness of Abiy doing so, as an insider of TPLF, Shabia and OLF he very well know the constant fear of Shabia as well as the clandestine deal among the trio anti-Ethiopian thugs. What we are hearing now is Assab was stolen by Shabia due to the goodwill of its cousin Woyane. Thus, the biggest take away is anytime in the future, Assab is coming home, Sweet home Ethiopia. The Shabia bird is foolishly sitting on another bird egg, bigger than itself.
-
Meleket
- Member
- Posts: 4364
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 21 Mar 2025, 09:39
Meleket wrote: ↑12 Aug 2018, 08:53
ርእዮት - ግርድፍ ግጥም
አንድ እናት ነበረች ልጆች የነበሯት፣
እጅግ ውብ የሆነች እንከን የማይወጣት።
ያለም ነገር ሆኖ እርጅና መጥቶ፣
ልጆች ስታሳድግ እንግልቷ በዝቶ፣
ብዙ ስቃይ አየች የማያልቅ ተወርቶ።
ግን አልሰነፈችም በማድረጓ ጥረት፣
አንድ ልጇን ዳረች መርቃ በክብረት።
ያለም ነገር ሆኖ የጤናዋ ጉዳይ፣
ለልጆቿ ስትል እሷ ስትሰቃይ፣
ከእለት ወደ እለት መሻሻል ሳያሳይ፣
ከእርጅናው ጋራ አባሰባት ስቃይ።
እንዲህ እንዲህም ሲል ያይኗን ብርሃን አጣች፣
ልጆቿ ሲያብቡ እሷ ግን ገረጣች።
ይህንን ታዝባ ባለ ትዳር ልጇ፣
እናቷን መርዳቷን አረገች ግዳጇ።
እናቷን ስትመራ በመንገዷ ሁሉ፣
ለመመረቅ ነበር እንዲያው በጥቅሉ።
እናትየዋ ግን የእናት ነገር ሆኖ፣
ልጆቿን ስትመግብ አንድ ልጇ ጨክኖ፣
አንድ ሃሳብ አመጣ አወላግዶ አጢኖ፣
ካወቅኩ ባይ ልጇ በቀረበ ‘መላ’፣
በሰላሙ ሰፈር ተንኮል እንዲያጠላ፣
እንዲህ እንዲህ አላት በነገር ፍተላ።
“ልጄ በመሆንሽ ራሴ የወለድኩሽ፣
የምልሽን ስሚ እንዲያው አትቅለስለሽ።
ይህ ያይኖችሽ ብርሃን ከኔ የወረስሽው፣
ባለቤቱ እኔ ነኝ ቁርጥሽን እወቂው።
ይህን ሃቅ አጢነሽ ተንግዲህ በኋላ፣
ማንኛውም ስራሽ እኔን ማያጉላላ፣
እንዲሆን አድርጊ እኛ እንዳንጣላ!
እንዲያውም ይህ ዓይንሽ ሁሉን ምታይበት፣
ባለቤቱ እኔ ነኝ እንዳሻኝ ምሆንበት፣”
ብላ እንድታስብ ያቺ ምስኪን እናት፣
አወቅኩ ባይ ልጇ በአንክሮ መከራት።
ባለትዳር ልጇ የመላች በትዕግስት፣
መረጠች ለናቷ እውነቱን ልትነግራት።
“እማማ እናታለም ወላጄ ውቢቱ፣
ይህን ሃቅ ስሚኝ እንዲያው ባዛኝቱ።
ድሮ ዓይኖች ነበሩሽ ምን ምን የመሰሉ፣
“በፌደሬሽን” ወቅት ላንቺ የተተከሉ፣
ያያቸውን ሁሉ እንዲያው ሚያማልሉ፣
እኛን በማሳደግ ውለታን የዋሉ።
የአምላክ ስራ ሆኖ ስለጠፉ አሁን፣
እንዴት ታልሚያለሽ ጌታን ለመኮነን?
ባለም አደባባይ ክሶችን መስርተሽ፣
እንዴት ልትዘልቂው ነው ፈጣሪን ሞግተሽ?
ያይንሽንስ ብርሃን እንዴት ልትመልሽ?
የተጠቃሚነት መብቱ ይገባኛል፣
የራስ ባልሆነ ዓይን እንዴትስ ይቻላል?
ይልቅ ጠባይ አርገሽ ከኔ ከልጅሽ ጋር፣
በብርሃኔ ልምራሽ እንኑር በፍቅር።
አንቺም ዋዛ አይደለሽ ብዙ ሃብቶች አሉሽ፣
ይህ የዓይኔ ብርሃን አይቀርም ሳይጠቅምሽ።
እንዲህ እንዲህ አርገን እየተጠቃቀምን፣
በፍቅር መኖር ነው ለኛ የሚበጀን።
ያለሽ አንድ አማራጭ ዓይንሽ እንዲበራ፣
እሱ ራሱ መጥቶ ተዓምር ካልሰራ፣
ሌላ መላ የለም ሚሆን በፉከራ፣
ጭቃውን አብኩቶ አይንሽን ነካክቶ፣
እሱ ካልዳበሰሽ ተሰማይ መጥቶ፣
የትም አያደርስሽ ሽለላ ቀረርቶ።
ተከባብሮ መኖር እያለ አንድ መላ፣
ተጋግዞ መኖርም እያለ አንድ መላ፣
እስቲ ዕድል አንስጠው ተንኮል ለሚያሰላ፣
አዋቂ ነኝ ለሚል ለማንም ቱልቱላ፣
ሌተቀን ለሚያልም እኛኑ ሊያባላ።
እኔና አንቺ ሁሌም ከልብ ስንፋቀር፣
እምንሰራው ሁሉ እንደሚሆን ተአምር፣
መሰሪ ዲያብሎስን እንደሚያደርግ ኩምትር፣
በምን አማርኛ ለመግለጽ ልሞክር!!!!!!!
ፍንጭ፦ ይህ ጽሑፍ ዓላማው፣ የሰው ገንዘብ ሚመኝን ክፉ መካሪ መሰሪን ለመገሰጽ ነው።
simbe11 wrote: ↑12 Aug 2018, 20:54
You’re a big damn animal. We are not seeking something that does not belong to us. We know what we own and will keep seeking for our rightful eye (Asab).
And FYI Ethiopia is not an old lady but historic land with so many beauties
Meleket wrote: ↑14 Aug 2018, 00:22
“ርእዮቴ”
ውቢት ኢትዮጵያማ የቆንጆዎች ቆንጆ፣
አንዱ ልጇ ያንዱን ባይሰርቀው ኮረጆ።
አንዱ ልጇ አንዱን ባይሰቅለው ዘቅዝቆ፣
ታሪኳ ሚያኮራ የማያልቅ ተዝቆ።
አንዱ ልጇ አንዱን ባያፈናቅለው፣
እስቲ እሷን ሚመስል ወዴት ነው ሚገኘው?
ልጆቿ በሙሉ እጅግ የተዋቡ፣
ፍቅርን ከጡቶቿ እየተመገቡ፣
አሳድጓቸዋል አምላክ በጥበቡ።
እንዲህ እንዲህ ናቸው ልጆቿ ኢትዮጵያ፣
ደምቀው ሚታወቁ በፍቅር መለያ፣
ተስፋን የሚጋቱ በእምነት ኩባያ፣
እሷ እናታቸውም የብዙሃን መኩሪያ።
“የሰው ወርቅ አያደምቅ” ብለው ሚተርቱ፣
ጥረው ግረው ኗሪ ከጥንት ከጠዋቱ፣
ይህ ነበር መለያው ኢትዮጵያዊነቱ።
አለ አንዳንድ መሰሪ ነገርን ጎንጉኖ፣
እኩይ አስተሳሰብ በህዝብ ውስጥ በትኖ፣
ወንድማማቾችን ለያይቶ አቧድኖ፣
ቂምና ጥላቻን በልቡ ከዝኖ፣
ቅራኔን የሚረጭ ትዕቢት ተጀቧብኖ፣
ሰው ከሰው አባልቶ ሚኖር በተቃርኖ።
ወንድም በወንድሙ በትር እንዲያነሳ፣
ቤተስኪያን አቃጥሎ ሚፈልግ ሙገሳ፣
መነኮሳን ገድሎ ተንኮል የሚያገሳ፣
መስጊድን አፍርሶ ሚፈልግ ሙገሳ፣
ሸኾችንም ገድሎ ትዕቢት የሚያገሳ፣
ይህ አይነቱን በድን ተንቀሳቃሽ ሬሳ፣
ዶማውን ዶማ ልል ብዕሬን ባነሳ፣
ተመንግሎ እንዲሄድ የትውልድ ነቀርሳ፣
መዝገብገብ ባደርገው ርእዮቴ እንዲወሳ፣
ትውልድን ለመግራት ባበዛ ወቀሳ፣
ቱግ ቱግ አትበል “እንቶኔ’ የኛ አንበሳ።
አትቀየምቢኝ ‘ማነሽ’ የኛ አንበሳ።
ይች የጥምረት ቀየ ይቺ ቅድስት ቤቴ፣
አወቅኩ ባይ “ልሂቅ” ሲያማት በመስማቴ፣
ይሀው መለስኩለት ተልቤ ታንጀቴ፣
ይህንን ይመስላል የኔማ ርእዮቴ።
https://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=17&t=163060& 
-
Abere
- Senior Member
- Posts: 13633
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Post
by Abere » 21 Mar 2025, 13:00
በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል?!
ከላይ ከእራሱ ላይ እያደፈረሱ፥
የሚወርደውን ወንዝ እያተራመሱ፤
እንጠጣ ይላሉ እንድሁ በሜዳ እየተኮፈሱ።
የጋራ እና የግል ልዩነት አያውቁ፤
ሁሉ የእኛ ብለው እየተደለቁ፤
የሰረቁትንም እየደባለቁ፤
የእኛ ነው ይሉናል ደግሞ ሲሳለቁ።
የእናንተን ከእኛ ጋር ሳትደባልቁ፤
በሃቅ በሃቃችሁ ሳትነቃነቁ፤
የሰረቃችሁትን - ለእኛ ስታበቁ፤
ሰላም ይጀመራል እውነቱን ስታዉቁ።
ደባልቀን እንብላ መቺ ትፈለጉና፤
የእናንተን ለእናንተ የእኛንም ለእናንተ ነገሩ ሆነና፤
ተቆጠረ 50 አመት ከገባ ፈተና።
ፈተና ይታለፍ ይብቃ ከተባለ፤
ኩብለላ ትታችሁ ሀቅ መላሳችሁ፤
ኢትዮጵያዬ ማሪኝ ልካስሽ ብላችሁ፤
እማማም በእቅፏ አርጋ ትሳማችሁ፤
እባቡን ጨፍጭፋ ዓሳውን ታብላችሁ።
ኢትዮጵ ጥላቷ ይውደም!!!