Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

በአብዲራህማን ማህዲ የሚመራው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ)፤ ከአሁን በኋላ "ከመንግሥት ጋር ግንኙት እንደማያደርግ"ወሰነ

Post by Za-Ilmaknun » 03 Mar 2025, 17:16

https://www.bbc.com/amharic/articles/c2ljk22x89wo

ኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ሊቀመንበር አብዲራህማን ማህዲ የሚመራው የፓርቲው ክንፍ፤ ከአሁን በኋላ "ከመንግሥት ጋር ግንኙት እንደማያደርግ" እና ቀጣይ የትግል ስልቱን በተመለከተ ለመወሰን "ከሕዝብ ጋር ውይይት ሊያደርግ" መሆኑን ለቢቢሲ ገለጸ።

ከስድስት ዓመታት በፊት የትጥቅ ትግልን በማቆም ወደ አገር የገባው ኦብነግ ይህንን አቋሙን ያስታወቀው ትናንት የካቲት 23/2017 ዓ.ም. በማኅበራዊ ትስስር ገጾቹ ባወጣው መግጫ ነው።"ኦብነግ፤ ሆነ ብሎ የሰላም ሂደቱን ካፈረሰ እና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ከዘጋ መንግሥት ጋር ከአሁን በኋላ ግንኙነት አያደርግም" ሲል ውሳኔውን ገልጿል።

ከስድስት ዓመት በፊት በኤርትራ አሥመራ ከተማ በተደረገው ስምምነት ኦብነግ ሲታገልለት የነበረውን "የኦጋዴን ሕዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ጥያቄ በተመለከተ ተከታታይ ውይይቶችን" በማድረግ መፍትሔ ለመስጠት መግባባት ላይ ተደርሶ እንደነበር የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ አብዲቃድር አዳኒ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ እንደሚያስረዱት በሕዝቡ ዘንድ የተፈጠረውን "ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ቅሬታዎች እንዲሁም መገለል" ጉዳይን ከመሰረቱ ለመፍታት ከስምምነት ላይ ተደርሶ እንደነበርም አስታውሰዋል።

"የኦብነግ ታጣቂዎችን ወደ ክልሉ የጸጥታ ኃይል ማስገባት" እና "በጦርነት ለተጎዱ የመልሶ ማቋቋም" ተግባራትን ማከናወንም ስምምነት ላይ ከተደረሰባቸው ጉዳዮች መካከል እንደሆኑም ገልጸዋል።

ይሁንና እነዚህ በወቅቱ ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ጉዳዮች "አለመፈጸማቸውን" ቃል አቀባዩ ይናገራሉ። ኦብነግ የነበሩት "18 ሺህ ታጣቂዎች በየቦታው መበተናቸውን" አክለው ተናግረዋል።