Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 40067
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Somaliman: Addis Shoneilise Blvd. !!

Post by Horus » 28 Feb 2025, 21:49


Horus
Senior Member+
Posts: 40067
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Somaliman: Addis Shoneilise Blvd. !!

Post by Horus » 28 Feb 2025, 22:11


Horus
Senior Member+
Posts: 40067
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Somaliman: Addis Shoneilise Blvd. !!

Post by Horus » 28 Feb 2025, 22:36


Odie
Member+
Posts: 6112
Joined: 24 Jun 2024, 23:07

Re: Somaliman: Addis Shoneilise Blvd. !!

Post by Odie » 28 Feb 2025, 22:42


Dama
Member+
Posts: 6381
Joined: 22 Jun 2024, 21:05

Re: Somaliman: Addis Shoneilise Blvd. !!

Post by Dama » 28 Feb 2025, 22:52

Odie wrote:
28 Feb 2025, 22:42
:lol: :lol:

Somaliman
Member+
Posts: 7167
Joined: 09 Nov 2007, 20:12
Location: Heaven

Re: Somaliman: Addis Shoneilise Blvd. !!

Post by Somaliman » 28 Feb 2025, 23:09

Dama wrote:
28 Feb 2025, 22:52
Odie wrote:
28 Feb 2025, 22:42
:lol: :lol:
:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

Abere
Senior Member
Posts: 14818
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: Somaliman: Addis Shoneilise Blvd. !!

Post by Abere » 28 Feb 2025, 23:26

ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ!
ሆዳም ጥፍራም በዝቶ አፈረሰሽ ወይ?

አፈረሱሽ አሉ፤ ከተማሽ ከሰለ - ወዘናሽ ገረጣ፤
አንች ምን ታደርጊ ጥፍራሞቹ በዝተው የሰው ልጅ ሲታጣ።

ቁላ ሰላቢዎች - አኖሌ ተከዮች፤
ታሪክሽን ሊሰለቡ፤ ተከበበሽ በጅቦች።

ያፈረሰሽ ፈርሶ ይገናል ታሪክሽ፤
እንባሽ ይታበሳል፤ ከአቧራ ተነስተሽ፤
የዐፄ ዳዊት ደብር፤ የጣይቱ ጫጉላ አይዞሽ ትከብሪያለሽ፤
ቆሪጣ እና እሬቻን የዐመድ ምስ ግተሽ፤ ነጻ ትወጫለሽ።

እነ የበጅ አብሪ፤ እነ ነውር ጌጡ፤
የቆሪጥን ምስ እየቀላወጡ፤
በየኮሪደሩ ወሬ ሲያንዛርጡ፤
አብረው ተደምረው እንዳይወቀጡ።

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4486
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: Somaliman: Addis Shoneilise Blvd. !!

Post by Za-Ilmaknun » 06 Mar 2025, 19:42

ባይተዋር ከተማ፡ “ፒያሳ፣ ካዛንቺስ... ሰፈሬ አልመስል አሉኝ”

ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በምትካቸው ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ሊቆሙ አፈራቸው እየተማሰ ነው፤ ቀን ከሌት። ጥድፊያው ነጠላ ለመዘቅዘቅ ጊዜ አይሰጥም። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ይዳሰሳሉ



ይህ ጽሑፍ በሚድየም ድረ ገጽ ላይ Ethiopia’s Forgotten Heroes: The Price of ‘Progress’ በሚል በእንግሊዝኛ የታተመ ሲሆን፣ ለዚህ ዘገባ እንዲስማማ ሆኖ ወደ አማርኛ ተመልሷል።

የፀሐፊዋ አያት ፊታውራሪ አጥናፍሰገድ በፋሺስት ጣልያን ወረራ ወቅት በአርበኝነት ሲዋደቁ ነው የተሰውት። የአያታቸው አያትም በዓድዋ ጦርነት ተሰውተዋል።

ቤቱን “የፍቅር እና መስዋዕትነት ተምሳሌት” ሲሉ በጽሑፋቸው የገለጹትም ለዚሁ ይመስላል።

በፋሺስት ወረራ ዘመን ጣሊያኖች ቤቱን መቀመጫ አድርገው ይጠቀሙበት ነበር። ከድል በኋላ ቤቱ ለቤተሰቡ ተመለሰ።

ደርግ ከወረሰው በኋላ ቤቱን ለማስመለስ ቤተሰቡ ትልቅ ተጋድሎ አድርጓል። የፀሐፊዋ እናት ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካ ፀሐፊዋ ገልጸዋል።

“እናቴ ለ40 ዓመታት ቤቱን ከርቀት አዘውትራ ትመለከተው ነበር” ይላሉ።

“. . . በአዲስ አበባ በዘመናዊነት ስም ብዙ ታሪካዊ ሥፍራዎች እየጠፉ ነው። ከቀድሞው ጋር የሚያስተሳስረን አይተኬ ባህላዊ ሃብት ዋጋ እያጣ ነው። የከተማችን ነፍስ በእድገት ስም እየከሰመ ነው. . .” እያሉ ይቀጥላሉ ፀሐፊዋ።
https://www.bbc.com/amharic/extra/diyd5 ... es_amharic

Post Reply