ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከተስማሙ ወዲህ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጉብኝት ሞቃዲሾ ገቡ -to finally kneel down and beg for mercy
Posted: 27 Feb 2025, 11:54
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ ሐሙስ የካቲት 20/2017 ዓ.ም. በሞቃዲሾ በሚያደርጉት ጉብኝት ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ይወያያሉ ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሞቃዲሾ ከሚገኘው አደን አብዱሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ጉብኝቱን አስመልክቶ ይህ ጉብኝት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ወሳኝ እርምጃ መሆኑን እንዲሁም ሁለቱ አገራት መሪዎች "በቁልፍ የሁለትዮሽ እና የጋራ በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ" እንደሚወያዩ ገልጿል።
ኢትዮጵያ ሶማሊያ እንደግዛቷ አካል የምትቆጥራት እና ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ነጻ አገርነቷን አውጃ ከምትገኘው ሶማሊላንድ ጋር የመግባቢያ ሰንድ ከፈረመች በኋላ በሁለቱ አገራት መካከል የተካረረ ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።
በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ የሁለቱ አገራት ወዳጅ በሆነችው ቱርክ አቀራራቢነት ከረገበ በኋላ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስዱ ነነበር።
ባለፉት ወራት የሁለቱ አገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በሞቃዲሾ እና በአዲስ አበባ በመገናኘት ቱርክ አንካራ ላይ የደረሱትን የትብብር ስምምነት ለማጽናት ውይይት ሲያደርጉ ቆይተዋል።
አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሊያ ከሚያደርጉት ጉብኝት ቀደም ብሎ ጥር 3/2017 ዓ.ም. የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት የሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት አድርገው ነበር።
ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈቀደ አንድ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ምንጭ "በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑካን ቡድን" በሞቃዲሾ የሥራ ጉብኝት እንሚያደርግ ቀደም ብለው ለፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ ገልጸው ነበር።
ምንጩ ጨምሮም "ይህ ጉብኝት የአንካራውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች አንድ አካል ነው" በማለት በቱርክ ዋና ከተማ የተደረሰውን ስምምነት ጠቅሰዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c80y5zx91d3o