Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 34733
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

So, What Do Africans Say At AU Summit?

Post by Horus » 13 Feb 2025, 17:10




Meleket
Member
Posts: 4045
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: So, What Do Africans Say At AU Summit?

Post by Meleket » 14 Feb 2025, 06:37

የኤርትራዊዉን ምሁር አስተዋጽኦ በመግለጽ፡ ከታሪክም ለመጥቀስ ያህል ነው!
Meleket wrote:
23 Feb 2019, 01:49
በአፍሪካ ሕብረት ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ አዲስ ስለታነጸው የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሃውልት ከተነገረ አይቀር፣ ከሃውልቱ ታሪክ ጀርባ ያለውን በሳል “የአምቼ” አእምሮ ስናስታውስ!

ዶክተር ተስፋዬ ገብረእግዚእ (1917-1967)

ዶክተር ተስፋዬ ገብረእግዚእ ከአከለ ጉዛይ ተወላጅ ከቀኛዝማች ገብረእግዚእ ስብሐትና ከወ/ሮ ማና ተስፉ ግንቦት 23 ቀን 1917 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ።

ትምህርታቸውን ኮተቤ በሚገኘው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቀጥሎም፡

ቤይሩት (ሊባኖስ) ከሚገኘው የአሜሪካን ዩኒቨርሲቲ የባችለር ዲግሪ በአስተዳደር ሙያ አግኝተዋል፡

በዩናይትድ ስቴትስ ካሊፎርኒያ ውስጥ በሚገኘው ስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት የማስተርስ ዲግሪ ተቀብለዋል፡

በዩናይትድ ስቴትስ በማሳቹሴትስ ክፍለ ሀገር ፍሌቸር ስኩል ኦፍ ሎው ኤንድ ዲፕሎማሲ የፍልስፍና ዶክተርነት ዲግሪ አግኝተዋል፡

ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ በተከታታይ
ከ1950 እስከ 1952 ዓ.ም. በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረዳት ሚኒስተር፡
ከ1952 እስከ 1958 ዓ.ም. ድረስ በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛና ኣምባሳደር።
ከ1958 እስከ 1964ዓ.ም. ድረስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደ.ኤታ፣
በመጨረሻም ከ1964 ዓ.ም. እስከ 1966 ዓ.ም. ድረስ የማስታወቂያ ሚኒስተር ሆነው አገልግልለዋል።

ዶ/ር ተስፋዬ ገብረእግዚእ ከመደበኛ ሥራቸው ውጭ በ1955 ዓ.ም. የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን እንዲያቋቁሙ ተመርጠው ቻርተሩን በመቅረጽና አስተዳደራዊ መዋቅሩን በመዘርጋት ድርጅቱ ዛሬ ለሚገኝበት ከፍተኛ የእድገት ደረጃ ፅኑ መሠረት ጥለዋል።

ደርግ በሚያዝያ ወር 1966 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ካዋላቸው በኋላ ያላንዳች ፍርድ በእሥራት ቆይተው ኅዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም. በግፍ ተገድለዋል።

“የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግጭት መንሥኤ እና መፍትሔ” ገጽ 244 በዶ/ር ደጃዝማች ዘውዴ ገብረሥላሴ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕረስ።

Post Reply