ስልጣንን ለማስረዘም የሚጣደፉት ሁለቱ የአብይ አሕመድ ኃይሎች
ከአገር ውስጥ ለፖለቲከኞች የአገራዊ ምክክር ( ፉግግር) ኮሚሽን ፤ በዲያስፖራው መስመር ደግሞ ሰሞኑን ብቅ ያለው ስደተኛ ፖለቲከኞችን የሚያጠምደው ቀንዳሙ ሆርን ፒስ ኢንስቲትዩት፤ የተሰጣቸውን አብይን በስልጣን የማቆየት ተልዕኮ ለማሳካት እየተጣደፉ ነው። .......... ሁለቱም ተቋም ነን ባዮች የሚመሩት በአብይ አድናቂዎች ሲሆን እምነት የማይጣልባቸው ልፍስፍስ ተቋማት ናቸው። .......... እነዚህ በአገር ውስጥና በውጪ የተመሰረቱት ተቋማት በብልፅግና የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገላቸው የሚዲያ ፍጆታውን ሞልተው እየተጮኸላቸው ቢገኝም በፖለቲከኞች ዘንድም ይሁን በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም። ..........አጀንዳ ሰበሰብን የሚለውን ዜና የሚያራግበው ኮሚሽን ካድሬዎችን ሰብስቦ ሲቸከችክ የሚውል ገልቱ ተቋም ከመሆኑም በላይ በሚጠራው ስብሰባ ላይ ወንበሩን የሚሞሉት አበል የሚከፈላቸው ካድሬዎች ናቸው። ........ ግልፅነት የጎደላቸውና በአብይ አገዛዝ ደጋፊዎች እጅግ የሚጨበጨብላቸው መሆኑ ደግሞ ከምስረታቸው ጥርጣሬ ጀምሮ በአሁን ጊዜ እምነተ ቢስ የከሸፉ ተቋማት መሆናቸው ተረጋግጧል። .......... አብይ አሕመድ በየጉሮኖው የመሰረታቸው ኮሚሽኖች ክሽፈታቸውን በተደጋጋሚ ያየነው ሲሆን የነዚህም ሴራ እና ስራ በሕግ ሽፋን ስልጣንን ለማፅናት የሚራወጡ ተቋማት ስለሆኑ በካድሬዎች ቢደነቆም በሕዝብ ፊት ግን ከሽፈዋል። #MinilikSalsawi
-
- Member+
- Posts: 9546
- Joined: 24 Aug 2012, 12:02
- Contact:
-
- Member+
- Posts: 9546
- Joined: 24 Aug 2012, 12:02
- Contact:
-
- Member+
- Posts: 9546
- Joined: 24 Aug 2012, 12:02
- Contact: