Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8385
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

የአብይ አህመድና የኦህዴድ/የኦሮሞ ብልጽግና አመራሮች ድብቅ ስብሰባ በጅማ

Post by Wedi » 04 Feb 2025, 18:09

በትኩረት አንብቡት

የአብይ አህመድና የኦህዴድ/የኦሮሞ ብልጽግና አመራሮች ድብቅ ስብሰባ በጅማ

አብይ አህመድ በጅማ ከተማና አካባቢው የልማት ጉብኝት ባደረገበት ወቅት በተለያዩ ጊዜያት የኦሮሚያ ክልልን በርዕሰ መስተዳድርነት የመሩትን ኦህዴዶችንና ጥቂት የኦሮሚያ ብልጽግና አመራሮችን  በመያዝ  በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ሚስጥራዊ ስብሰባ አድርገዋል።

እነሱም

1 . ኩማ ደመቅሳ የቀድሞ የኦሮ/ክ/ር/መ/ር
2. ጁነዲን ሳዶ የቀድሞ ኦሮ/ክ/ር/መ/ር
3.አባ ዱላ ገመዳ የቀድሞ ኦሮ/ክ/ር/መ/ር
4.ሙክታር ከድር የቀድሞ ኦሮ/ር/መ/ር አሁን የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር
5.ሽመልስ አብዲሳ
6. አዳነች አቤቤ
7.ጫልቱ ሳኒ  የከተማ ልማት ሚ/ር
8.ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የቀድሞ ፕሬዚዳንት
9.ግርማ ብሩ የብሄራዊ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ እና የአብይ አማካሪ
10.ብርሃኑ ጁላ
11. ወርቅነህ ገበየሁ
12.ዶ/ር ግርማ አመንቴ ግብርና ሚ/ር

ከላይ በስም የተዘረዘሩት የኦሮሞ ባለስልጣናት በልማት ጉብኝት ስም በጅማ ከተማ ጥልቅ የሆነ እና ልዩ ግምገማዊ ስብሰባ አድርገዋል።
የስብሰባው አንኳር አጀንዳዎች ሁለት ነበሩ

1.ባለፉት ስድስት አመታት የሰራናቸው ስኬታማ ስራዎች ምንድን ናቸው ?
2.በቀጣይ አመትስ ምን መስራት ይጠበቅብናል ?

የሚል ሲሆን ከአማራ አኳያ ተከታዩ ነጥቦች ላይ ተነጋግረዋል ።

1.2.2 የአማራ ክልልን ሁኔታ በተመለከተ

➢ በለውጡ ከፍተኛ የውስጠ ፓርቲ ትግል ያደረጉትንና በለውጡ ሂደት ሚና አለን የሚሉትን እንዲሁም በክልሉ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ ድጋፍና ተሰሚነት የነበራቸውን አመራሮች ሕብረ-ብሄራዊነትን የማይቀበሉ በሚል አራግፈናቸዋል፡፡

➢ በየደረጃው ያሉና የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎችንና በደሎችን አጀንዳ የሚያደርጉ ቀሪ አመራሮችን ደግሞ የነጠላ ትርክት ሰለባ ናችሁ በሚል ከብልፅግና መርህ አንጻርእየገመገምን እናሰናብታቸዋለን፡፡

➢ አሁን በኃላፊነት ላይ ያሉት አብዛኛዎች የአማራ ክልል አመራሮች ከሕዝባቸው የተነጠሉና ከግል ፍላጎታቸው በላይ ስለማያስቡ እኛ የምንላቸውን ብቻ እየፈፀሙ ናቸው፡፡

➢ በሰራነው የተጠና የፖለቲካ ሥራ ጎጃምና ጎንደር ከቀን ወደ ቀን የጋራ ፖለቲካ ሊሰሩ ቀርቶ አብረው ሊቆሙ በማይችሉበት ደረጃ አድርሰናቸዋል፡፡ ይህ ልዩነት ይበልጥ እየሰፋና እየከረረ እንዲሄድ ተግተን መስራት ይኖርብናል፡፡

➢ ከጎጃምና ጎንደር ባሻገር የአማራ ክልል በአማራ ሕዝብ ጉዳይ በጋራ እንዳይታገል አድርገነዋል፡፡

➢ በተለይ አሁን በየደረጃው ያለው የአማራ ክልል አመራር እርስ በእርሱ የማይግባባና የማይተማመን አድርገነዋል፡፡ ስለሆነም ይህ ሁኔታ እንዲቀጥል ለንዑስ ማንነቶችና ለጎንደር አመራር ልዩ ተቋማዊ ድጋፍ በማድረግ የአማራ ክልል አመራር ልዩነት ይበልጥ እንዲሰፋና እንዲከር ማድረግ ይጠበቅብናል።

➢ ጽንፈኛው የጀመረው የትጥቅ ትግልም ለጊዜው ሕዝብ ያውክ ካልሆነ በስተቀር የትም የሚደርስ አይደለም፡፡

➢ በሰራነው አመርቂ የፖሮፖጋንዳና የሕግ ማስከበር ሥራ ጽንፈኛው ከሕዝብ እየተነጠለ ስለሆነ የሎጅስቲክ ምንጩ እየደረቀ ነው፡፡ እርስ በእርሱም እንዲዋጋ እያደረግነው ነው፡፡

➢ ለጊዜው አስቸጋሪ የሆነው የጎጃሙ ጽንፈኛ ቡድን ስለሆነ በተራዘመ ጦርነት ሕዝቡን በማሰልቸት ጽንፈኛው ተነጥሎ እንዲደመሰስ ከማድረግ ጎን ለጎን አመራሩን አድኖ በመምታት ጽንፈኛው መሪ አጥቶ እንዲበተን መስራት ይጠበቅብናል፡፡ በዚህ መሰረት የጎጃሙን ጽንፈኛ ቡድን ለብቻው በመነጠል ቀለበት ውስጥ በማስገባት ሙቀጫ ውስጥ እንዳለ አህል መውቀጥ አለብን።









eden
Member+
Posts: 9613
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Post by eden » 04 Feb 2025, 21:03

thank you for the summary


Post Reply