Page 1 of 1

ቦርጨ ፊ ስርነ

Posted: 02 Feb 2025, 21:18
by Naga Tuma
ቦርጨ ማለትን በትክክል መተርጎም ያቅተኛል።

ዉጥቅጡ የወጣ ብል ትክክለኛ ትርጉም መሆኑን እጠራጠራለሁ። ብጥብጥ ብልም እንደዛዉ። ድብልቅ ብልም እንደዛዉ። ዝብርቅርቅ ብልም እንደዛዉ።

መላ ቅጡ የወጣ ብልም ትክክለኛ ትርጉም ኣይመስለኝም። የእንግልዛኛዉን ኬኦስ ብጠቀምም ትክክለኛ ትርጉም ነዉ ማለት ያዳግተኛል።

ቦርጨ ማለት ስርዓትን የማያዉቁ ህጻናት ድብልቅልቅ ማድረግ እንደ ማለት ነዉ። አዋቂ አጠገባቸዉ የሌለ ግዜ የምያደርጉት ስርዓት የሌለዉ ኣይመስላቸዉም። በዕድሜያቸዉ የታያቸዉን ይጫወታሉ። አዋቂ ደርሶ ስያስተዉል ለማስተካከል ይለፋል።

ስርነ ማለትንም በትክክል መተርጎም ያዳግተኛል። ስነ ስርዓት ያለዉ ማለት በቂ ትርጉም ኣይመስለኝ። ተገቢ የሆነ ነገር እንደ ማለት ነዉ።

ሁለቱም ቃላት ከሁኔታዉ የበለጠ ግልጽ ሊሆኑ ይችላሉ።

ቦርጨ፥ አባት እና እናት ይታወቁበት የነበረን ማንነት ትቶ የቃሉ መሠረት ኦርመ ወይም ባዕድ ማለት ለሆነ ማንነት ለዘመን መልፋት።

ስርነ፥ አባት እና እናት ይታወቁበት የነበረዉን ማንነት ይዞ መዝለቅ ነበር።

ቦርጨ፥ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለልማት የተቋቋመ ድርጅት ዉስጥ በመግባት ጥያቄያችን የልማት ሳይሆን የቅኝ ግዛት ነዉ ማለት።

ስርነ፥ ቃልቻ ቃሉን ቅኝ ገዛ ብሎ መልፋት ስህተት ነዉ።

ቦርጨ፥ ሸጎዬ እና ሸግዬ የሚል ማህበረሰብ መሃል ሄዶ በቃልቻ ቃሉን ቅኝ ገዛ ሰበካ ማጋጨት እና መገጫጨት።

ስርነ፥ ቃሉ እና ቃልቻ ልዩነታቸዉ ምንድነዉ ብሎ መጠየቅ። ሸጎዬ እና ሸግዬ ልዩነታቸዉ ምንድነዉ ብሎ መጠየቅ።

ቦርጨ፥ ታሪካዊ እና የኣፍርካ ኣንድነት ድርጅት መቀመጫ የሆነች ሃገር መክሰም ኣለባት ብሎ መጽሓፍ ማሳተም።

ስርነ፥ እንደዚህ ዐይነት ቦርጨ ለራሱም ጭምር መክሰም የሆነ መታዘዝ ነዉ።

ቦርጨ፥ አዲስ ሕገ መንግስት ይዘጋጅ ተብሎ ሃገር የፈለገች ግዜ መፍረስ ትችላለች ማለትን የመንግስት ዐዋጅ ማድረግ።

ሰርነ፥ ሕገ መንግስት ማለት የመንግስት ሕግ ማለት ነዉ። መንግስት እጸናለሁ ባይ እንጂ ልፍረስ ባይ ኣይዴለም።

ቦርጨ፥ በሪሳ በሃገር ፊደል መታተም የጀመረበት ሃገር ዉስጥ ከዓመታት በኋላ ሉተራን ኮ፣ ላቲን ኮ፣ ቁቤ ኮ እያሉ የሃገር ቋንቋን ከሃገሩ ፊደል ማፋታት።

ስርነ፥ የሃገር ፊደልን ለመጀመርያ ግዜ የፈጠሩት እነማን ነበሩ? ሃ ራብዕ እያልክ ያ ረብ በል እንጂ።

ቦርጨ፥ የፍጥረት በር የሆነች ጥንታዊ እና ታሪካዊ ሃገር ዉስጥ ዜጎችዋን ኦርመ ወይም ባዕድ እና ወገነ ወይም ወገን እያሉ በመከፋፈል ማጋጨት። እ አ አ በ1974 ሳይሆን በ2024።

ስርነ፥ የሃገር ምንነት ካልገባህ የኣንድ ሃገር ዜጎች ኣንድ ወገን የሆኑ የፖለትካ ማህበረሰብ ናቸዉ።

እስቲ እዚህ ዉስጥ የትኛዉ ነዉ ስህተት? ዕዉነት ወይም ዕዉነትነት ያለዉ ከሆነ የምታነበዉ መጽሓፍ ርፐንት የሚል ኣይዴለም?

እኔ ኣንድን የነፃነት ግንባር ለመቃወም ለሌላ የነፃነት ግንባር የሞራል ድጋፍ ኣድርጌ የማዉቅ ቢሆንም ቦርጨን ኣስተዉዬ የአቅሜን ያህል ስርነ ለማስያዝ መልፋትን ኣዉቃለሁ። ኣዕምሮ የሰጠኝ ቦርጨንም ማስተዋልን ጨምሮ ያለፋል።