Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MINILIK SALSAWI
Member+
Posts: 9612
Joined: 24 Aug 2012, 12:02
Contact:

ጂቡቲ የአፋር ክልልን በድሮን ደበደበች

Post by MINILIK SALSAWI » 01 Feb 2025, 02:47

“ የሟቾች ቁጥር 8 ነው። ቁስለኞች ከ10 በላይ ናቸው። ቁስለኞች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ” - ነዋሪዎች

“ ጥቃቱ የድሮን ጥቃት ነው፡፡ የሟቾች ”ቁጥር እስካሁን ባለኝ መረጃ  ስምንት ነው" - ኤሊዳዓር ወረዳ

በአፋር ክልል ኤሊዳዓር ወረዳ ሲያሩ ቀበሌ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት በአርሶ አደሮች፣ ሴቶች፣ ህፃናት  ሞትና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ በሰጡት ቃል፣“ 8 ሰዎች ተገድለዋል። ከ10 በላይ ደግሞ ቆስለው ዱብቲ ሆስፒታል ገብተዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው ከወደ ጅቡቲ አቅጣጫ በመጣ ድሮን ነው ” ብለዋል።

Image

መረጃ አቀባይ ነዋሪዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ ትላንት ሌሊት አካባቢ መጀመሪያ ሦስት ሰዎች ተገደሉ። ሦስቱንም ዱሮን ነው ያጠቃቸው። ከዚያ ዛሬ ጠዋት ሟቾቹን ሊቀብሩ የነበሩ ሰዎችን ዱሮን እንደገና መጥቶ ነው ያጠቃቸው።

መጀመሪያ ሦስት ወንዶች የሞቱ ሲሆን፣ እንደገና መጥቶ ሦስት ጊዜ ነው ጥቃት የተፈጸመው። ሦስቱ ከተገደሉ በኋላ ድሮን መጥቶ ሴቶችና ህጻናትን አታክ ተደረጉ።

አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ስምንት ነው። ቁስለኞች ደግሞ ከ10 በላይ ናቸው። ቁስለኞች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ዱብቲ ሆስፒታል ገብተው ነው የሚገኙት።

ጥቃት የተፈጸመበት አካባቢ ድንበር ነው ለጅቡቲ። ድሮኑ በየት አቅጣጫ እንደሚመጣ ይታውቃል። ይታያል ማለት ነው ከጅቡቲ እንደመጣ ይታወቃል።

‘ ጅቡቲን የሚቃወሙ ታጣቂ ኃይሎች አሉ ’ ብለው ነው ጥቃቱን የሚፈጽሙት። ከቁስለኞቹ ውስጥ የአስር አመት ህጻናት አሉ። ሴቶች አሉ። ዱብቲ ሆስፒታል እግሯና እጇ የተቆረጠች ልጅ አለች ” ብለዋል።

“ የድሮን ጥቃት ደርሷል ” መባሉን እንዲያረጋግጡልን የጠየቃቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኤሊዳዓር ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን አካል፣ “ አዎ። ጥቃቱ የድሮን ጥቃት ነው፡፡ የሟቾች ቁጥር እስካሁን ባለኝ መረጃ ስምንት ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።

“ ጥቃት የደረሰበት ሲያሩ ቀበሌ የጅቡቲ ድምበር ” መሆኑን ጠቅሰው ለተጨማሪ መረጃ በቦታው ያሉ የጸጥታ አካላት ምላሽ እየተጠበቀ መሆኑን አስረድተዋል።

“ በዚያኛው በኩል በስንት ኪሎ ሜትር እንደሆነ፣ በዚህኛው በኩል በስንት ኪሎ ሜትር እንደሆነ የጸጥታ አካላት ምላሽ እየተጠበቀ ነው ” ሲሉ ጠቁመዋል።

ከሟቾች በተጨማሪ በሴቶችና ሕጻናት ከባድ ጉዳት እንደደረሰ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል ስለዚህስ ጉዳይ ምን ይላሉ ? ምን ያክል ሰዎች ናቸው የተጎዱት? ስንል ላቀረብነው ተጨማሪ ጥያቄም የወረዳው አካል ምላሽ ሰጥተዋል።

Image

በምላሻቸውም፣ “ አዎ፡፡ እኛ በቦታው ስላልቆምን የጸጥታ አካላት ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ፤ ቁስለኛው ፣ምን ያህል እንደሆነ አጣርተው እስከሚያመጡ እየተጠበቀ” ነው ብለዋል።

ተጨማሪ ማብራሪያ የጠየቃቸው አንድ የክልሉ ፓሊስ አባል፣ “ ከመረጃ ውጪ ነኝ ” ሲሉ የስልክ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ኔትዎርክ የሌለበት ቦታ ነው ያለሁት። በእርግጥ መረጃ የለኝም። እያሉ ግን ሰምቻለሁ ” ከማለት ውጪ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

Fiyameta
Senior Member
Posts: 16076
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ጂቡቲ የአፋር ክልልን በድሮን ደበደበች

Post by Fiyameta » 01 Feb 2025, 12:33

I don't believe for a second that Djibouti would carry out such drone attacks in the Afar region of Ethiopia.

Cui Bono? (Latin) Who benefits?

I however strongly suspect that Abiy Ahmed has something to do with the incident because he has openly expressed his plans to turn the Afar region into a theater of war by mobilizing his aid-fed troops to the region, which he hopes will draw Eritrea into a conflict.

Case in Point: It was only a few days ago that the Banda Abiy hosted a conference in Addis Ababa attended by TPLF cadres, where a former TPLF fighter who claims to be the leader of an "Eritrean Afar movement" delivered a speech, asking Abiy to "liberate" the Afar people in Eritrea. IQ 63! HAHAHAHAHA :lol: :lol: :lol: :mrgreen:

It should be noted that, back in 2021 when Neo-colonial powers were congratulating each other at the news of TPLF mercenary forces marching towards Addis Ababa, their most glamorous Banda and mouthpiece who's on George Soros' payroll, Tsedale Lemma of Addis Standard was at the forefront of their short-lived jubilation. In recent months, she has been urging the Amhara people to ask Fano leave the cities and towns to avoid being targeted by Abiy Ahmed's drone strikes and bombardment of heavy artillery fire.

Don't be surprised if the glamorous Banda who lies for a living, once again, fabricates a claim about Eritrea's support to FRUD, the Afar rebels fighting against Djibouti's authoritarian regime. :P




Post Reply