Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4045
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

አስካሪ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Meleket » 29 Jan 2025, 05:25

አስካሪ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

“እናታለም” ጦብያ እንዲያው ሳትከስሪ፣
መጠጥ ስትጠምቂ በብቅል ስትሰሪ፣
በጎጃም ሲጠመቅ ሆድእቃን ቦርቧሪ፣
በጎንደር ሲጠመቅ ኣቅጣጫን ቀያሪ፣
በትግሬ ሲጠመቅ ጉግስ ላይ ገፍታሪ፣
በሓረር ሲጠመቅ በጥልቁ ጨማሪ፣
በሸዋ ሲጠመቅ ምላስን ኣሳሪ፣
በወሎ ሲጠመቅ ሃይቅ ላይ ነካሪ፣
በደቡብ ሲጠመቅ በጣም አስቀብጣሪ፣
ይህን ሁሉ መጠጥ ቢያገኘው መርማሪ፣
“ያባታለም” ኤሩው አንደኛው ጠርጣሪ፣
ድምዳሜው ነበር ሁሉም ነው አስካሪ

በኤርትራዊ ኣማርኛ በተጣፈ ግርድፍ ግጥም ለመዝናናት ያህል ነው። ተዝናኑ! ይመቻችሁ ያፍሪካ ቀንድ ፈርጦች!

Axumezana
Senior Member
Posts: 16431
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: አስካሪ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Axumezana » 29 Jan 2025, 12:01

ደብተራ አስካሪ መለከት!
It looks you have started to be proud of your ascari identity!

Meleket
Member
Posts: 4045
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አስካሪ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Meleket » 30 Jan 2025, 04:59

ወዳጃችን ኣዅሱመጫላ እንዴት ነህ ባያሌው? እላይ ያለችውን ግጥማችንን ቁምነገሯን ታጣጥም ዘንድ እስቲ ይህን ታሪክ እንጋብዝህ። ይትባርክ ግደይ የተባለ ሰው የጻፈው ነው። ይመችህ ባያሌው!
ክህደት በዘር ብቻ አይመጣም (ምዕራፍ ፯)

ከሓዲ ማን ነው? ሐቀኛና ሀገር ወዳድስ ማን ነው? በኢትዮጵያ ታሪክ ሲነበብም ሲነገርም ወይም ከሕፃን እስከ ሽማግሌ ሲጠየቅ ወይም መልስ ስጥ ሲባል “ከሐዲማ ትግሬው ደ/ች ሀ/ስላሴ ጉግሣ ነው” እየተባለ እና እየተነገረ እንደመጣ አንዳችም ማስተባበያ ሊኖረን አይችልም። መልሱ አዎን ብለናል ነው። የታሪክ መፃሕፍትንም አንብበነው ከሆነ ግን ከሀ/ስላሴ ጉግሣ በላይ በክህደት የተካኑ፣ የተከሰሱ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው፣ የዕድሜ ይፍታህ እስራት የተወሰነባቸውና በጫካ በዳንዲ በረሃ፣ በጂማና በጎሬ ተራራዎች በስብሰው የሞቱ ሌሎች ከሐዲዎች አሉ ወይስ አልነበሩም? ታዲያ ነበሩ ከተባሉ ለምን ስማቸው በከሐዲነት አልተነሳምና ኣልተመዘገበም? ለምን ሕብረተሰቡ እንደ ደ/ች ሃ/ስላሴ እንዲያውቃቸው አልተደረገም? ለምን ተሸፋፍኖ እንዲቀር ተደረገ? ለምንስ የደጃች ሃ/ስላሴ ጉግሳ ክህደት ብቻ እየጎላ የሌሎች እየደበዘዘ ዓመታትን አስቆጠረ? ይህን ለማወቅ ሰፊ ጥናት ማካሄድ ሊያስፈልግ ይችል ይሆናል። ይህን ብቻ ግን አይደለም ጥናት የሚያስፈልገው። ይጠና ከተባለ የኢትዮጵያ ታሪክ እንደ አዲስ መጠናት አለበት። ምክንያቱም ከዚህ በፊት የተጻፈው የቃል ታሪክና እየተነገረ ያለው፡ የራስ ወዳድነትና የታሪክ ሽሚያና ዘረፋ እንጂ፤ እውነተኛ የዚች ሃገር ታሪክ አለ ወይም ነበር ለማለት ያስቸግራል።

በጥናት እና በመረጃ የተደገፈ የሀገርን ቋሚ ታሪክ ይሠራ ከተባለ በግለሰቦች ሳይሆን ከሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ የለብ ለብ ሳይሆን ሰፊ ጊዜና ገንዘብ ተመድቦለት የደረሰበትን የታሪክ ጥናት ለፓርላማ አቅርቦ በማፅደቅ መሆን ያለበት ይመስለኛል። አለበለዚያ አንዱ የፃፈውን ሌላው ብሔረተኛ ወይም ወገንተኛ ተነስቶ ሲያፈርሰው ይኖራል እንጂ ሕብረተሰቡ የእኔ እና የአገሬ ታሪክ ነው ብሎ የመቀበሉ ድርሻ አጠራጣሪ እየሆነ የመጣበት ጊዜ ላይደርሰናል።

ለምሳሌየ1928ቱ የጣልያን ወረራ ጊዜ ደ/ች ሀ/ስላሴ ጉግሣ ነው ከአስመራ ጠላትን ጎትቶ ያስመጣው፤ ያስወረረን፤ እየተባለ ይነገራል፣ በታሪክም ከተጻፈ ጊዜ የለውም። ይህ ትውልድ በፅሁፍና በአፈ ታሪክ ደጋግሞ በአገር ክህደት የሚያውቃቸው ሃ/ስላሴ ጉግሣን ብቻ ነው። የተማረው ክፍልም ከሐዲ ማነው ተብሎ ሲጠየቅ ሀ/ስላሴ ጉግሣ ነዋ! እያልን እንደመጣን አንክድም። ለምን? የታሪክ መምህራኖቻችን አስረግጠው አስተምረውናልና ነው።

የዋናዎቹ ከሐዲዎች ግን በፅሁፍ ይቅርና እንዳሉ ጎልቶ ስማቸው ሲነሳም ሰማሁ የሚል ዜጋ አይኖርም። ለምን ግን ተደበቀላቸው? ለግል ታሪካቸው ሲባል ነው? አይደለም፣ የአካባቢያቸውን ብሔር ወይም ጎሣ ክብርና ዝና እንዳይበክልና እንዳያጎድፍ ሲባል እንጂ ስለ ክህደት ጉዳይ ከተነሣማ የደ/ች ሃ/ስላሴ አለቃና ዋና የክህደት ተዋናይ ጣሊያንን እየመሩ የመጡ - መምራት ብቻ ሣይሆን ኢትዮጵያ የጣሊያን ቅኝ ግዛት ሆና መተዳደር አለባት ብለው የህክደት ዋና መሐንዲስ ሆነው የከረሙት አፈወርቅ ገ/የሱስ ነበሩ።

አቶ አፈወርቅ ገ/የሱስ እ.ኤ.ኣ. በ1928–36 ዓ.ም. ኢትዮጵያ እምነቷን በእሳቸው ላይ ጥላ ሙሉ ባለስልጣን አምባሳደር አድርጋ ትልቁንና ከባዱን ኃላፊነት ሰጥታ ወደ ሮም በላከቻቸው ጊዜ በኢጣልያን ፋሽስት ሀገራችን በጋዝና በቦምብ ስትጋይ ምን ይሰሩ ነበር? ኢጣልያ ኢትዮጵያን 5 ዓመት ያህል ይዛ በነበረችበት ጊዜ አፈወቅር በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ በሃገራቸውና በወገናቸው ህዝብ ላይ ሲፈፅሙት የነበረው በደል፣ ክህደት ግፍና የጭካኔ ድርጊቶች ለምን አልተፃፈም? በኢትዮጵያ ሠራዊት ኃይል ከኢትዮጵያ ከተባረረ በኋላስ [እዚህ ላይ ደራሲው ዘባርቋል ፋሽስት ጣሊያንን እያሯሯጠ አዲስ አበባን ጭምር በቅድሚያ የተቆጣጠረውን የእንግሊዝን ኃይል ኣልገለጸም] በአቶ አፈወርቅ ገ/የሱስ ላይ ምን ምን ፍርድ እንደተፈፀመባቸው ለምን አልተገለፀም? ከጥቂት ጊዜ በኋላ አቶ አፈወርቅ ገ/የሱስ “አፈ ቂሣር አፈወርቅ” ተብለው በኢጣሊያ መንግስት ተሾሙ . . . አፈ ቂሣር ማለት ደግሞ በአማርኛ ዚመነዘር አፈ ንጉሥ ማለት ነው፣ በኋላ ግን ንጉሱ አዲስ አበባ ሲገቡ ጉዳቸው ፈላና የሞት ፍርድ ተወሰነባቸው።

ይግባኝ ብለውም ዕድሜ ይፍታህ ውሳኔ ተወስኖባቸውና በጅማ እስር ሲማቅቁ ኖረው ሞቱ?”
ዘረኛው ትምክህተኛውና ነውረኛው አፈወርቅ ገ/የሱስ በሚኒልክ መፃሓፋቸው ከፃፉት የስድብ ቃላት ጥቂቱን “ጎጃም ለ3 ወር ያህል በአንበጣ ትግሬ ተመደመደ፣ ችጋር ያባረረው ትግሬ ባሩድ የሸተተው አውሬ፣ አንድ ናቸው።”፤ “ምኒልክ የሰለሞን አንበሳ የጋላ ድልብ ሰለቸውና የትግሬን የአንበሳ ለምድ የለበሰ በሬ መስበር ወደደ፣ . . . ትግሬ በጠፋልኝ የማይል ኣልነበረም።” በማለት የዘረኝነት መርዛቸውን ረጭተው አልፈዋል። የአሁኑ የዘረኝነት እንቅስቃሴም የአፈወርቅ እርሾ መሆኑን መዘንጋት የለበትም። የእስከ መገንጠል አንቀጽ 39ም ያመጣው ጣጣ ይኼው የአፈወርቅ ገ/የሱስ ክስና ትምክህት አንዱ አካል ነው። ማን አለና ዘሩና ብሔሩ በጽሑፍ ሲሰደብ እና ሲዋረድ አሜን ብሎ የሚቀበልና ትክክል ነህ ብሎ መልስ የሚሰጥ? ማን ከማን ያንሳል? አንተ ችጋራም፣ እየተባለ ሲዋረድ ማን ነው የሕሊና ዕረፍት የሚሰጠው? አንት ድልብ እየተባለ ሲናቅ ወይም ዚንቋሸሽ እያየና እየሰማ ማን ይተኛል? ይህ ነው እንግዲህ የብሄር ጥያቄ ሊያስነሳና ሁሉም በቋንቋውና በክልሉ ተደራጅቶ እንዲኖር ያስደረገው። የእስከ መገንጠል ጥያቄ ከመሬት ተነስቶ ዛሬ የተፈጠረ ሳይሆን ከመቶ ዓመት በፊት ጀምሮ ሲንከባለል የመጣ የንቀትና አንዱ ብሔር የበላይ ሌላው የበታች እየተደረገ ስለሚታይ እኔስ ከማን አንሼ? የሚለውን የትግሬው እና የኦሮሞም የትግል እንቅስቃሴ መጀመሩ አይቀሬ ሆነ።

በተለይም የአፈወርቅ ገ/የሱስ መፅሐፍ የኢትዮጵያ አንድነትን የሚንድ ዘረኛ በወቅቱ ከገፀ ምድር መጥፋትና በእሳት መቃጠል ነበረበት። ነገር ግን እንኳን ሊጠፋ አንድም ምሁር የመፅሐፉን ርኩስነት አውግዞ የፃፈ የለም። ቀደም ሲል ተስተባብሎ ቢሆን ይህ የአሁኑ የብሔር ጥያቄም ባልተነሳ ነበር። የሕወሐትና የኦነግ ወደ በረሀ የመግባት ጉዳይም አንዱ ይኸው ሊሆን ይችላል። “ተናቅን፣ ተዋረድን፣ ሕዝባችን ተናቀ፣ ተዋረደ፣ ኢትዮጵያዊነቱ ገፈፉት፣ ዜግነቱን ነጠቁት፣ ሰብአዊ ክብሩን አዋረዱት” አሉና ከተመቸ ለአንድነቱ ካልተመቸ ደግሞ እስከመገንጠል መብት ሊኖረን ይገባል ሲሉ ተንቀሳቀሱ። ታዲያ ይህ ምን ያስነውራል? ተቃዋሚዎቹስ ብትሆኑ ጎሣችሁ ሲሰደብና ሲዋረድ፣ ምንም ሳይበድል ሲገረፍ፣ ሲናቅ ሰብዓዊ ክብሩ በአደባባይ እየተጣሰ ብትመለከቱ አርፋችሁ ትቀመጣላችሁን? ሁሉም በራሱ ላይ ካልደረሰበት ግን አይሰማውም። ለዚህም ነው በግራም በቀኝም፡ አሁንም ሆነ ቀድሞ የትግራይ ሕዝብ ያለ ስሙ ስም ተሰጠው፣ ተሰደበ፣ ተዋረደ ብሎ ሌላው ቢቀር ተራ የቃል ይቅርታን እንኳ የጠየቀው ባለመኖሩ ችግሩን እያሰፋ ያመጣው።

ከሐዲዎች አገሪቱን እና ህዝቧን የበደሉ ያሰቅዩ፣ የገረፉና፣ ያሠሩ እነ አፈ ቂሣር አፈወርቅና እነ ራስ ሀይሉ የጎጃምን ሕዝብ ካለ አቅሙ ለጣሊያን ግብር ክፈል እያሉ በአቁጫጭ በበረት አጉረው በማሰር ለጠላት የአመኑና ያመለኩ፤ አንድ ቀን እንኳ ስማቸውን ለማንሳት ሳይሞከር፣ ደ/ች ሃ/ስላሴ ትግሬ ስለሆኑ ብቻ የክህደቱን ሸክም ብቻቸው ተሸክመውት ኖረዋል።

ለመሆኑ ከአስመራ ወይም ከአዲግራት እየመራ ጣሊያንን ያስመጣ ነው በዋና ከሐዲነት ተጠያቂ የሚሆነው? ወይስ ከመሠረቱ ከሮማው ያውም በአምባሳደር ደረጃ ከነበረው አፈ ቂሣር አፈወርቅ ግፊትና ግምባር ቀደም አዝማች ሆኖ የመጣውና ያስመጣው ነው በግንባር ቀደም ከሐዲነት ተጠያቂ? እስኪ ቆም ብለን እናስብበት፣ ሌሎችስ ከአማራና ከኦሮሞ ከሐዲዎች፣ አንድ ሁለት ሣይሆን እጅግ በጣም ብዙ ከሐዲዎች የሉምን? ሁሌ ሲነገር ከሐዲ ከትግራይ ብቻ ነው ባንዳ ሲባልም ከኤርትራ ነው። ነገር ግን ብዙ ከሐዲና ባንዳ ከሁሉ ብሔር አለ። ለምሳሌ አልበርቶ ሰባኪ እንደጻፈውና እምሸው አለማየሁ እንደተረጎሙት በኢጣሊያ ፊሺስቶች ወረራ ዓመታት መፅሐፍ በ1936 ዓ.ም. ለሁለተኛ ግዜ በተዘጋጀው ስነስርዓት ላይ ራስ ገ/ሕይወት ሚካኤል፣ ደ/ች አመዴ አሊ፣ አያሌው ብሩ፣ ሀ/ሚካኤል መንገሻ በሮም የኢትዮጵያ አምባሣደር የነበሩት አፈወርቅ ገ/እየሱስ ለኢጣሊያ ታማኝነታቸውን ገልፀዋል። ከሁለት ሣምንት በኋላ በተዘጋጀ ሌላ ሥነ ሥርዓት ላይ ራስ ከበደ መንገሻ አቲኪሞ፣ ኣባ ጃቢርና፣ ፊታውራሪ ክንፈ ለጣሊያን መንግስት ቃለ ማህላ ፈፀሙ ገጽ 42

ራስ ሃይሉ የግራዚያኒ ወዳጅ የነበሩና እስከ መጨረሻው ድረስ የኢጣሊያ ታማኝ ሆነው የቆዩ መስፍን ናቸው። ከተግባራችው መካከል የምዕራብ ኢትዮጵያን ለኢጣሊያ በኃይል በማስገበር ተሳትፈዋል። በመጨረሻም “የኢጣሊያ ኮከብ” የሚል ሽልማት ተሸልመዋል። ሌላው ከሓዲ አባ ጆቢር (የጂማው) ነበሩ። በአርባዎቹ እድሜ የነበሩት ራስ ጌታቸውም ከኢጣሊያ በሚያገኙት ደምወዝ ምቹ ኑሮ ያጣጥሙ ነበር”

[ዘረኛው ማነው? ኢትዮጵያዊያን ፍረዱ! ከይትባረክ ግደይ ገጽ 117-122]


በቀጣይ የትኛው ባንዳ ወይም አስካሪ ከጣሊያን ፋሺስታዊ መንግሥት ምን ያህል "ደመወዝ" ይቀበል እንደነበር፡ ደራሲው ያካፈሉንን እናካፍላችኋለን። ያኔም እኛ የኤርትራውያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና የቋጠርናት ግጥም ይዘት ይበልጥ ያጣጥማሉ!

Axumezana
Senior Member
Posts: 16431
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: አስካሪ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Axumezana » 30 Jan 2025, 09:39

ደብተራ ኮፒ paste ስታደርግ ትኖራለህ!

Meleket
Member
Posts: 4045
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አስካሪ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Meleket » 30 Jan 2025, 10:55

ወዳጃችን ኣዅሱመጫላ ኣሁን ኮፒ ፔስት ያደረግነውን ግጥማችንን ማጣጣም ትጀምር ዘንድ ፈቅደንልሃል!
Meleket wrote:
29 Jan 2025, 05:25
አስካሪ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

“እናታለም” ጦብያ እንዲያው ሳትከስሪ፣
መጠጥ ስትጠምቂ በብቅል ስትሰሪ፣
በጎጃም ሲጠመቅ ሆድእቃን ቦርቧሪ፣
በጎንደር ሲጠመቅ ኣቅጣጫን ቀያሪ፣
በትግሬ ሲጠመቅ ጉግስ ላይ ገፍታሪ፣
በሓረር ሲጠመቅ በጥልቁ ጨማሪ፣
በሸዋ ሲጠመቅ ምላስን ኣሳሪ፣
በወሎ ሲጠመቅ ሃይቅ ላይ ነካሪ፣
በደቡብ ሲጠመቅ በጣም አስቀብጣሪ፣
ይህን ሁሉ መጠጥ ቢያገኘው መርማሪ፣
“ያባታለም” ኤሩው አንደኛው ጠርጣሪ፣
ድምዳሜው ነበር ሁሉም ነው አስካሪ

በኤርትራዊ ኣማርኛ በተጣፈ ግርድፍ ግጥም ለመዝናናት ያህል ነው። ተዝናኑ! ይመቻችሁ ያፍሪካ ቀንድ ፈርጦች!
Axumezana wrote:
30 Jan 2025, 09:39
ደብተራ ኮፒ paste ስታደርግ ትኖራለህ!

Axumezana
Senior Member
Posts: 16431
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: አስካሪ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Axumezana » 30 Jan 2025, 16:19

ደብተራ፤ ታምታታለህ!

አስካሪ ማለት በቅኝ ከሚገዛ አገር ቅኝ ገዢው በግድም በውድም የሚመለምለው ጦር መሆኑ ጠፍቶህ አይመስለኝም፤

Meleket
Member
Posts: 4045
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አስካሪ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Meleket » 31 Jan 2025, 07:22

ወዳጃችን አዅሱመጫላ ትርጉሙ ተምታቶብሃል። ቃሉ በአኵሱምኛ ኣይደለም የሚፈታው። የቃሉ ፍቺ “ቀኝ ከተገዛ አገር ግራ ከተገዛ አገር” የሚል አባባል የለውም። ይልቅስ ወታደር ወይም ፖሊስ ማለት እንደሆነ ነው መዝገበ ቃላቱ የገለጠው። አፍሪካ ውስጥ ለአውሮፓውያን ተስፋፊ ሃይሎች ያደረ ወታደር ማለት ነው። በመሆኑም ወታደሩ አጤ ዮሃንስና ጭፍራቸውም ጭምር ለእንግሊዛውያን ተስፋፊዎች በማደርና በመታዘዝ ሱዳን ድረስ ሰራዊታቸውን ለውጊያ ይልኩ ስለነበረ፡ በመዝገበ ቃላቱ ትርጉም መሰረት “አስካሪ” የሚለው ቃል ይመለከታቸዋል ማለት ነው። ኣይደለም እንዴ?

የመዝገበ ቃላቶች ትርጉሙ ይህን ነው
Askari
https://www.merriam-webster.com/dictionary/askari
1. a native soldier especially of eastern Africa in the service of a European power 2. a native police officer or guard of eastern Africa.

Askari
An askari or ascari (from Somali, Swahili, and Arabic عسكري, ʿaskarī, meaning 'soldier' or 'military', also 'police' in Somali) was a local soldier serving in the armies of the European colonial powers in Africa, particularly in the African Great Lakes, Northeast Africa and Central Africa. The word is used in this sense in English, as well as in German, Italian, Urdu, and Portuguese. In French, the word is used only in reference to native troops outside the French colonial empire. The designation is still in occasional use today to informally describe police, gendarmerie and security guards.[1] https://en.wikipedia.org/wiki/Askari


የናንተው Dechasa Abebe የምርምር ውጤትንም እዚህ https://www.ajol.info/index.php/ejossah ... iew/174229 ልታገኘው ትችላልህ ርእሱ እንዲህ ይላል Ethiopian and Eritrean Askaris in Libya (1911- 1932) ሰውዬው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ Center for African and Oriental Studies ረዳት ብሮፌሰር ናቸው። ጥሑፋቸው ላይ አንድ ሁለት ጥሑፎችን ጠቅሰውም የኢትዮጵያዉያን አስካሪ ጉዳይን እንዲህም አስኪደውታል

በ1903 ዓ.ም. ኢጣልያኖችና ቱርኮች ሊቢያ ላይ ሲዋጉ ተዋግቻለሁ፡፡ ብዙ አማሮችም እንደ እኔ ተቀጥረዉ መጥተዉ ይዋጉ ነበር፡፡ በዉጊያዉ ላይ ብዙ ጊዜ የቆየነዉ ሰዎች በ1905 ዓ.ም. ለዕረፍት ወደ አስመራ ተመለስን፡፡ በዚያን ጊዜ በአስመራ የነበሩት የኢትዮጵያ ቆንስል ልጅ ወሰኔ ዛማኔሌ ይባሊሉ፡፡ እኛን አማሮቹን ኑ ወደ አገራችሁ ግቡ ልጅ ኢያሱ ደመወዝ እየሰጡ በወታደርነት ያኖሯችኋል እያለ አባበለን፡፡ ከእኛ ከአማሮቹ ዉስጥ ምክራቸዉን ስለተቀበልነዉ ከአስመራ ወጥተን ወደ ደሴ አለፍን፡፡ ….. አለቃችን አቃ ገብሩ ናቸዉ፡፡ እሳቸዉን መሪ አድረገን ከአስመራ የወጣነዉ አራት መቶ ዓሥራ ሁለት ሰዎች ነን፡፡ (Merse Hazen, W. K. 1999 EC. የኃያኛዉ ክፍለ ዘመን መባቻ, The Dawn of the Twentieth Century. Addis Ababa. : 118)

እርስዎ ራስዎ ጎጃምን መልካም አድርጌ እገዛለሁ ይላሉ፤ ነገር ግን የጣልያን መንግስት ወዳጅዎ ስለሆነ ትሪፖሊ ሔደዉ ስንቱ ጎጃሞች እንደሞቱና ስንቱ አካላታቸዉን እንደተቆረጡ፣ ስንቱስ በጦርነቱ እንደሚያገለግሉት ቆይቶ ዝርዝራቸዉን ቢጠይቁት በደስታ ይሰጥዎታል፡፡ በከንቱ ትሪፖሊ እየሔደ ያለቀዉን የጎጃም ሕዝብ ቁጥር ሲያዉቁት በደስታ አለመኖሩንና ለጠላቱ መንግስት ሲያገለግል በብዙ ሺህ የሚቆጠር ጎጃሜ መሞቱን ሊረዱት ይችላሉ፡፡ (Tesfa Mikael, T. 2006 EC. ሀገሬ የህይወቴ ጥሪ, My Country: the Call of my life. Addis Ababa.: 23)


ለእንግሊዝ ካደሩ ኢትዮጵያዉያን መካከል “አስካሪውን” አጤ ዮሃንስን ከጠቀስን ዘንዳ በቀጣይ ለጣልያን ካደሩ ኢትዮጵያዉያን አስካሪዎች መካከል፡ ኢትዮጵያዊው ይትባርክ ግደይ በመጸሐፉ ያሰፈራቸውን ጠቀስ ጠቀስ እናደርጋለን፡ ምን ያህል “ደመወዝ” እንደነበራቸውም ጭምር መሆኑ ነው። ያኔ የግጥማችን ይዘት ለአንባቢ ፍንትዉ ብሎ ይታያል።

Axumezana
Senior Member
Posts: 16431
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: አስካሪ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Axumezana » 31 Jan 2025, 09:31

ደብተራው
ራስህን አታታልል፤
Ascari & mercenary are different !

Axumezana
Senior Member
Posts: 16431
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: አስካሪ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Axumezana » 01 Feb 2025, 04:26

ዝጀግና መዲደይ ታይ በለ!



Meleket
Member
Posts: 4045
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አስካሪ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Meleket » 03 Feb 2025, 03:34

አፍሪካ ውስጥ ለአውሮፓውያን ተስፋፊ ኃይሎች ያደረ አፍሪካዊ ወታደር አስካሪ ይባላል። ቅጥረኛ ነፍሰገዳይ (መርሰነሪ) ደግሞ በማንኛውም ስፍራ ለማንኛውም ኃይል በጥቅም የተገዛ ወታደር እንደማለት ነው።

አጤ ዮሃንስ ለእንግሊዝ መንግሥት ሱዳን ላይ የሰጡትን አገልግሎት በተመለከተ፤ የአውሮፓ ተስፋፊ ሃገርን ያገለገሉ አፍሪካዊ በመሆናቸው፡ አጤውና ወታደሮቻቸው "አስካሪ" ነበሩ። ቅጥረኛ በመሆንም የባንዳ ስራንም ደርበው ሰርተዋል።

በዝብዝ ካሳ አጤ ቴዎድሮስን ለመደምሰስ በተደረገው ዘመቻ ለእንግሊዝ መንግስት የሰጡትን አገልግሎትም እንዲሁ የአውሮፓ ተስፋፊ ሃገርን በውትድርናውና በስለላው ሙያቸው ያግዙ ስለነበረ "አስካሪ" ነበሩ።

ቅጥረኛ (መርሰነሪ) ወይም ቅጥር ነፍሰ ገዳይ የምንለው ደግሞ፡ አንድ ነገር እንዲፈጽም ወይም እንዲሰራ በክፍያ ወይም በጥቅም የተገዛ እንደማለት ነው። አፍሪካ ውስጥ ላይሆንም ይችላል። ለተስፋፊ የአውሮፓ ሃይሎችም ሊሆን ይችላል ቅጥረኛነቱ።

አፍሪካ ውስጥ አንድ ዘውግን በአንድ ሌላ ዘውግ እንዲገዛና እንዲጨቆን፡ የገዛ ዘውጉን አሳልፎ ለሌላ አፍሪካዊ ገዢ የሰጠ ኣካልስ ምን ይባል ይሆን። እስቲ ሁነኛ ስም ፈልስፉ? መቼም "ምስለኔ" የሚለው ቃል በቅጡ አይወክለውም፡ ምክንያቱም አንድ ገዢ የገዛ የዘውጉን አባል፡ በተለያዩ ስፍራዎች በሱ ስም እንዲያስተዳድር ሊሾም ይችላል። ይህ ተሿሚም “ምስለኔ” የሚል ስም ሲሰጠው ነበር።

መዲድ ያልከው ሰዉዬ፡ ሱማሌ ወይም ኤርትራ ልዑላዊ መሬት ውስጥ ገብተው ከነበሩት የወያኔ ወታደሮች አንዱ ከነበረ፡ ቅጥረኛና መርሰነሪ የሚለው ስም እሱንም ይመለከታል። ባንድ ወቅት ቅጥረኛ ወይ አስካሪ የነበረ አካል፡ ቆይቶ ታሪኩን በማሻሻል ጀግና የማይባልበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለም። መዲድ ያልከው ሰዉዬ፡ “በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የድንበር ውዝግብ ዘላቂ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ፡ የድንበር ላይ ህዝቦችም ሰላማዊ ጉርብትናን ያጣጥሙ ዘንድ፡ ሄግ ላይ የተወሰነው የድንበር ብይን አሁኑኑ ይተግበር” የሚል አቋምን የሚያራምድ ከሆነ ብቻ ነው ጀግና የሚል ስም ሊሰጠው የሚችል፡ ምክንያቱም ጀግና የሚባል ክቡር ስም ዬሚሰጠወ በህግ ልዕልና የሚያምን አካል ብቻ ነውና።

Meleket
Member
Posts: 4045
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አስካሪ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Post by Meleket » 04 Feb 2025, 06:53

ለዛሬ እስቲ የእነዚህን ኢትዮጵያዉያን አስካሪዎች ደሞዝ እንመልከት፡ ኢትዮጵያዊው ደራሲ ይትባረክ ግደይ መጸሐፍ አጣቅሶ ከዘረዘራቸው መካከል ናቸው።

አፈወርቅ ገብረኢየሱስ .................... የወር ደሞዝ በሊሬ 50,000
ራስ ሃይሉ................................የወር ደሞዝ በሊሬ 40,874
ደጃዝማች ሃይለስላሴ ጉግሳ.................የወር ደሞዝ በሊሬ 25,000
ሼክ ኢል ሆጀሌ...........................የወር ደሞዝ በሊሬ 25,000

Meleket wrote:
29 Jan 2025, 05:25
አስካሪ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

“እናታለም” ጦብያ እንዲያው ሳትከስሪ፣
መጠጥ ስትጠምቂ በብቅል ስትሰሪ፣
በጎጃም ሲጠመቅ ሆድእቃን ቦርቧሪ፣
በጎንደር ሲጠመቅ ኣቅጣጫን ቀያሪ፣
በትግሬ ሲጠመቅ ጉግስ ላይ ገፍታሪ፣
በሓረር ሲጠመቅ በጥልቁ ጨማሪ፣
በሸዋ ሲጠመቅ ምላስን ኣሳሪ፣
በወሎ ሲጠመቅ ሃይቅ ላይ ነካሪ፣
በደቡብ ሲጠመቅ በጣም አስቀብጣሪ፣
ይህን ሁሉ መጠጥ ቢያገኘው መርማሪ፣
“ያባታለም” ኤሩው አንደኛው ጠርጣሪ፣
ድምዳሜው ነበር ሁሉም ነው አስካሪ

በኤርትራዊ ኣማርኛ በተጣፈ ግርድፍ ግጥም ለመዝናናት ያህል ነው። ተዝናኑ! ይመቻችሁ ያፍሪካ ቀንድ ፈርጦች!

Post Reply