Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 5942
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

አክሱም እና ክርስትና

Post by Naga Tuma » 13 Jan 2025, 17:27

የአክሱም ሃዉልቶች የተገነቡት አክሱም ክርስትናን ሳይቀበል በፊት ነበር።

ለመጨራሻ ግዜ የተገነባዉ ሃዉልት የንጉስ እዛና ነበር ይባላል። ንጉሱ የመጀመርያዉ ክርስትና ተቀባይ ነበርም ይባላል።

አካሱም ክርስትናን የተቀበለዉ በ4ኛዉ ክፍለ ዘመን ነበር።

ያኔ ጠንካራ የነበረ ንግስና ክርስትናን ተቀብሎ ከስድስት መቶ ክፍለ ዘመናት በኋላ ወደቀ።

ጠንካራ ሆኖ የነበረዉ በራሱ ጥረት ሀያልነት ነበር ወይስ ከሌሎች ድጋፍ በማግኘት ነበር?

የወደቀዉስ የራሱ ጥረት ቀንሶ ነዉ ወይስ የዉጪ ወይም ተዉሶ ተጽዕኖ ኣይሎ ነበር?

እንደዚህ ዐይነት ጥያቄዎች ናቸዉ የህዳሴን ጽንሰ ሀሳብ የሚወልዱት።

Renaissance 1.0 was an enlightened departure from superstition. The same is true about Renaissance 2.0 that I have been trying to enlighten.

That departure led to what I call the most transformative self reliance in human history. It is written in the Bible that the kingdom of God is within you.

I suspect that that departure was the source and foundation of the idea of separation of church and state in the U.S. The idea of separation of church and state doesn’t mean that they don’t work together in harmony. It means they have distinctly separate roles.

ጽንሰ ሀሳቡ በቀላሉ የሚወለድ እንዳልሆነ ኣዉቃለሁ። ከሞራ የተረፈ ሞረ ኣንባቢነት በቀላሉ የሚመጣ ኣይዴለም። ላራስ ሳይሆን ለሌሎች ማሰብ ቀልድ ኣይዴለም።

ከወጣትነት ዕድሜዬ ጀምሮ ነበር ስለ ሱፐርስቲሽን ከቤተሰብ አባል ጋር መከራከር የጀመርኩኝ። በሌሎች ጉዳዮች የምንስማማ በዚህ ጉዳይ ሳንስማማ ዘለቅን።

ከኢትዮጵያ ኮሌጅ ሳልመረቅ በፊት ነበር ጽንሰ ሀሳቡን ማሰላሰል የጀመርኩኝ።

ከኢትዮጵያ ሳልወጣ በፊት ነበር ስራ ቦታ የተዋወኩት ሰዉ የፕሮቴስታንት ቤት እንድሄድ የጋበዘኝ። መልስ ለመመለስ ግዜ ኣልወሰደብኝም። ሀይማኖት ከሆነ ለምን ተዋህዶ ቤት ኣትሄድም ብዬ ጠየኩት። ደፍሮ የጠየቀኝ ተከፍቶብኝ ከአጠገቤ ሄደ።

ሁለታችንም የአካዳሚ ስራ ላይ ነበርን። ያ ሰዉ ዛሬ ዬት እንዳለ እና በአካዳሚ ሙያዉ ምን ያህል እንደተሳካለት ኣላዉቅም።

ይህን ኣሁን እዚህ የምጽፈዉ የሬይነሳንስ ጽንሰ ሀሳብ ጥልቀት ምን ያህል ተስተዉሏል ለማለት ነዉ።

ይህ ሲስተዋል ነዉ በ4ኛዉ ክፍለ ዘመን ጠንካራ የነበረ እና ክርስትናን የተቀበለዉ የአክሱም ንግስና እንዴት ነዉ በ10ኛዉ ክፍለ ዘመን የወደቀዉ ብሎ መጠየቅ የምያስችለዉ።

በምያስገርም ሁኔታ ባህል ኣምቆ እስከዚህ ዘመን የዘለቀዉ የቃሉ እና የአባ ገዳ ሚናዎች የቸርች እና ስቴት ለየብቻ መሆንን በጣም ግልጽ ያደርጋል።

ቃሉ የአባ ገዳ ምርጫ ዉስጥ ኣይሳተፍም፣ ተጽዕኖ ኣያደርግም። አባ ገዳ ከተመረጠ በኋላ ግን የሚባርከዉ ወይም የሚመርቀዉ ቃሉ ነዉ። ይህ ማለት የሀይማኖት መሪ ግልጽ እና የተለየ ሚና ኣለዉ ማለት ነዉ።

ይህን ማስተዋል በዉስጥ የነበረዉ ጥንካሬ እና የተዉሶ ተጽዕኖን ማመዛዘን ያስችላል።